ፎቶ እና አጭር ገለጻዎች በአህመድ ኑር። ሎሬት ጽጋዬ ደፋር ጀግና አገሩን እና ሕዝቡን የሚያስቀድም ሴትም ትሁን ወንድ በጣም ያደንቁ ነበር በሕይወት እያሉ። ታዲያ የኢትዮጵያ ወርቅ በዲሲ ስብሰባ ላይ ሎሬት ጸጋዬ በክብር እንግድነት የተጠሩበት ላይ እንድትገኝ ጋብዘናት ነበር ለሎሬት አልነገርናቸውም እንደምትመጣ። ታዲያ ልክ ስብሰባው ሲጀምር ብቅ ስትል ሎሬት ጸጋዬ የተሰማቸውን ደስታ እንዳነሳሁዋቸው ፎቶግራፎች ማየት ማመን ነው ብዬ ለመግለጽ ውይም ለማሳየት ቃላቶች ያጥሩኛል። ብዙም አልቆዩም ንግግራቸውን ሲከፍቱ ሎሬት ጸጋዬ እንዲህ ብለው ጀመሩ "ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ወርቅ እንደምታስታውሱት ኢትዮጵያ ገብታ ነበር ። ኮሎኔል መንግስቱን ለመን ወደ ጦሩ አይመለሱም ስልጣንዎን ለሲቪሉ አስረክበው የእርሶ በስልጣን መቆየት ለአገሪቱ እና ለሕዝቡ አንድነት አስጊ ከሆነ? ብላ የተናገረች ጥያቄም ያቀረበች ወጣት እና ጀግና ናት። ወንዶቹ መለዮአቸውን ጥለው መጥታ አነሳችላቸው!" በሚል አድናቆታቸውን ለተሰበሰበው ሲገልጹ ሎሬትን በጣም ጥሩ አድርጌ ስለማውቅ መልእክት በውጪም ለምንገኘው ኢትዮጵያዊያን ዎንዶች ጭምር የአገራችንን አንድነት አስከብሩ ተባብራችሁ ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ናት የሚል ጥሪ እንደነበረ አባባላቸው ልረዳ ችያለሁ። ይሄውም ወንዶቹ መለዯቸን ጥለው መጥታ አነሳችላቸው የሚለው ጥቅሳዊ አባባላቸው ለሰራዊቱን ብቻ ስመልክቶ አልነበረም ባጠቃላይ የኢትዮጵያዊነት ውንድነትን ወንዶቹ አውልቀው ጥለው ወኔ አጥተው መጥታ ከአሜሪካን አገር ድረስ ወኔያቸውን አነሳችላቸው ለማለት ነው። ከዚህበታች ያሉት አምስት ፎቶግራፎች በስብሰባው እለት እመስከረም ምግብ ቤት ውስጥ እና ከእራት በሁዋላ በውጪው ለመታሰቢያ ያነሳሁዋቸው ፎቶግራፍ ነው። የሐርር ወርቅ፡ አንድ በጣም ልዩ የሆነ ሎሬትን በተለዬ የአገር ታሪክ ሚዛን ላይ አስወምጣ የምታደንቃቸው ከሌላ ኢትዮጵያዊ ያላገኘቸው ጉዳይ ስለ ሎሬት ጸጋዬ እንዳለ አጭውታኛለች። ይሄውም ሎሬት ጸጋዬ እና ቤተሰባቸው አዲስ አበባ በሄደችበት ጊዜ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብሎ ወደ ቀኝ አጠፍ በሚል መንገድ ላይ በስተቀኝ በሚገኘው ቤታቸው እራት ይጋብዝዋታል። እዛም በጣም ያስደነቃት እስዋ እንዳለቸው አኩሪ እና አስደሳች እራት ይቀርብላታል። ምግቡም ትልቅ የክብር ምግብ ከመሆኑም በላይ ከአልማዝ የበለጠ ስጦታ እንደነበረም ገልጻልኛለች በጊዜው ከሃያ ዓመት በፊ ማለት ነው። መግቢያው ወይም መጀመሪያው የእራቱ ሰላጣ ሳይሆን፡ በጣም ጥርት ያለ እጅ የሚያስቁረጥም ቆሉ ነበር። ዋናው ምግብ የስጋ እና ዶሮ ወጥ ሳይሆን፡ የብዙሃኑ ምግብ የሆነችው ትክን ብላ በደንብ የተሰራች የሽሮ ወጥ ጣእምዋ እና ትዝታዋ ፈጽሞ የማይረሳ በሕይወትዋ በልታው የማታቀው አይነት ይጋብዝዋታል። ሌላው ዘፈን ወይም ቴሌቪዢን እያዩ እንግዳ ማስተናገድ እንደማትወድ ስትናገር በመስማታቸው፡ ጉዳዩ ስላስደሰታቸው እንደ ሙዚቃ የቀረበላት የኢትዮጵያ ታሪክና ግጥሞች እናም ጥቅሶች ነበሩ። ሎሬት እራሳቸው እያነበቡላት ምግቡን በልተው ሲጨርሱ። በመጨረሻም "አድባር!" የሚለውን ታዋቂውን ድርሰት ግጥም ስጦታ አበርክተውላት እራቱ ይፈጸማል። |