Sunday, July 21, 2013

Congresswoman Cynthia McKinney enjoying the Ethiopian history. News from NBUF Dallas Chapter

Photo news briefing by National Black United Front Dallas Chapter (NBUF)  NBUF is about self help not begging from corporates.  For more information visit "Dallasnbuf.com" and contact Thomas Muhammad and join us!

 Congresswoman Cynthia McKinney was in Dallas for National Black United Front 34th Annual National Convention
"Africans Must Unite At Home and Abroad Revisiting Principles of Pan-Africanism"  The convention was very successful! The convention was organized by NBUF African-Americans and many African immigrants in DFW this include Ethiopian community organizers and community leaders that are known by the DFW community and public for the last 30 years. 
 
Congresswoman Cynthia McKinney enjoying the Ethiopian history-her history, all Africans and all Black people history! 
ከላይ ፎቶ ላይ የምታይዋቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚያደንቁዋቸው ቆራጥዋ ክብር ሲንትያ ናቸው፡የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ለአሜርካን ምክር ቤት ከአትላንታ የተመረጡ እና ስድስት ጊዜ ባጠቃልይ በመደጋገም ሕዝቡ የመረጣችው ሲሆኑ። በቲሪቡናል ኮርት በመገኘት በተለያዩ አገሮች እና ሕዝብ ላይ ወንጀል የሰሩን አሜሪካንን ጭምር ወጥረው የያዙ ናቸው። ሲንትያ ሜኪኒ ለብሄራዊ የጥቁሮች የአንድነት ግንባር  የሰላሳ አራተኛ በአሉ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው በመጡበት ባለፈው ሳምንት ያረፉበትን የሐረርወርቅ ጋሻውን ቤት ውስጥ የሚገኙትን የኢትዮጵያን እና የሌላ የአፍሪካ አገሮችን ሰአሊዎች የሳሉትን እና የአፍሪካን ቅርጻ ቅርጽ ጭምር እየተመለከቱ በአፍሪካ ታሪክ በሚያውቁት ላይ በጨማሪ በተለይ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ እንዲገነዘቡ ያደረግዋቸው የታሪክ ቅርፅጾችን እና መጽሃፎችን ለምሳሌ ስለ አጼ ምንይልክ ስምተው ስለማያውቁ የንጉሱን አለባበስ እና ከባርሜጣቸው ስር የተፈተለ ሻሽ ማሰሩ ከሳቸው የተወሰደ መሆኑን ሲረዱ ጭምር ጣሊያንን ከመግረፍ ጭምር ሲረዱ የኢትዮጵያን ትሪክ የራሳቸው አድርጎ ነው ያቀፍት። ስለሆነም ከአንድ ወር በፊት ኢትዮጵያ ደርሰው የተመለሱት እህታችን ደህና መንግስት ቢኖር ኖሮ መጀመሪያ የእነ አጼ ምንይልክን ሃውልት እና የእነ ንግስት ጣይቱን ታሪክ በጎበኙ ነበር ሆነም ኩራታቸውን ፎቶ በመነሳት እያደነቁ የተነሱት ፎሮግራፍ እነሆ።

ከዚህ በታች ያለው ደግሞ 
                                       ሰዕል ከኢትዮጵያ የመጣ ፡ በኢትዮጵያ ሰአሊ የተሳለ ሲሆን የኤትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቄስ የማሪያም መሃበርተኞች መሃል ተገኝተው ምግብ እየበሉ የሚያሳይ ሲሆን የቆሎ ተማሪው፡ የኔ ቢጤው እና ልጃገረዶች ወንድ ልጆች ጭምር በሰዕሉ ላይ ይታያሉ። ይህ ሰዕል በዳላስ ሞርኒንግ ላይ በሁለት ሺ ስምንት በአሜሪካን አቆጣተር ከዚሁ ከግድግዳው ላይ በአድናቆት ጋዜጠኞች ለጥቁሮች አመታዊ የታሪክ ወር ፎቶ አንስተው ያወጡት ነው በኢንተርነት ላይ ማግኘት ይቻላል።   ኮንግረስ ውመን ሲኒትያ በጣም በመደስት እና በመኩራት አዲስ አበባ ካንድ ወር በፊት ሄድው ያላዩትን አኩሪ የኢትዮጵያን ትሪክ ኢትዮጵያውያን ጣሊኖችን ገርፈው ያባርሩበትን ልበ ቆራጥነት በማድነቅ ጣሊያኖቹ በመድፍ እና በጠመንጃ በነርቭ ጋዝ ሃይል ኢትዮጵያን ሊሰርቁ ያለመቻላቸውን ሲረዱ ምነው እንደነዚህ አይነት ጅግኖች በኖሩ ነው ያሉት ለአንድ ጥቁር ሕዝብ እና ለየአፍሪካ አሃጉሩን ነጻ አድርጎ አክብሮ የሚያስከብሩ ሴቶች እና ውእንዶች።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ፓሰርን መለእክት እያነበቡና በተፈጥሮ ውበትዋ እና በሚያምረው ጥቁረትዋ ተውባ በፓስተሩ ላይ ይምትታየውን ኢትዮጵያዊ የአርሲ ሴት እህቴ ስታምር እያሉ ጌጣጌጥዋ እና ዘመናዊ ጸጉር ቤት ሳትሄድ ጽጉርዋ በደንብ ተስተካክሉ በጉድሩ መልክ የተቀመጠውን እያደነቁ በጥያቄና መልስ አገሬ በሚልዋት ኢትዮጵያ እና በወዱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ኩራታቸው እየገነነ በቀኑ የሰሙትን እና ያዩትን ለመጀመሪያ ጊዜ መረዳአቸው ማወቃቸው መሆኑን እየመለሱ የተነሱት ፎቶግራፍ።
በጣም ብዙ የሰውን ልጅ ኑሮ እና መከራ ደስታ የአንዋንዋር ዘዴ ስልጣኔንም ጭምር አስተዳደርንም በማጠቃለል የሚያሳዩ ሰሎች እና ከእንጨት እና ከድንጋይ የተሰሩ ቅርጻ ቅርጾችን በመስራት የምእራብ አፍርካ ተወላጆች ወገኖቻችን የታወቁበት ነው። በመሆኑ ብዙ ሳይባል ከስ ዕሉ ብቻ ብዙ ታሪክ መማር ይቻላል ብሎም ከቅርጻ ቅርጾች። ታዲያ ሲnቲያ ሜኪኒ አብረውት የተነሱት ሰዕል ከምእራብ አፍሪካ የተገዛ ስእል ሲሆን ሰዕሉ የሚያሳየው መንደር ባህር አጠገብ ያለ መንደር ንዋሪው አሳ ለማጥመድ መረቡን እየጣለ እያለ ነው። 
በአሜሪካን ምክር ቤት አባልነት የታወቁት ጀግኒት ሲንቲያ እና የሐረርወርቅ ጋሻው ፡ ከሁዋላቸው የአሴ ቴዎድሮስ ሰእል እና የኢትዮጵያን ጀግንነት የሚያሳዩ ታሪካዊ ሰዕሎች ተገን አድርግው የተነሱት ፎትግራፍ።
ከተከበሩ የተለያዩ እንጨቶች የተስሩ የአፍሪካ ታሪክን እና የሴቶችን አገር መሪነት ለቤተሰብ ምሰሶ ስር መሰረት መሆንን እና ሌላም ሌላም ታሪክን ከሚገልጹት ቅርጻቅርጾች እንደሚታየው በግድግዳው ላይ ካሉት ጋር ክብርት ሲንቲያ ለማስታወሻ በአፍሪካ ታሪክ በኩራት የተነሱት ፎቶግራፍ።
በአውሮፓ፡ በአሜሪካ፡ በአፍሪካ፡ በመካከለኛው ምስራቅ፡ በእሩቅ ምስራቅ ጭምር በብዙ መጽሄቶች እና የቴሌቪዢን ብሎም በመንገድ ላይ በሚገኙ የማስታወቂያ ግድግዳዎች እና ባስ ላይ የወጣውን የሐረርውርቅን ሳያውቁ በፊት የሚያውቁትን ፓስተርዋን ይዘው የተነሱትን ፎቶ መነሻ በማድረግ በስብሰባ ላይ ሲገልጹ "የሐረርወርቅ ወታደር ነች።  ይሄውም ሞደል ስለሆነች ሳይሆን፡ በሞደልነትዋ ብሎም በአክትረስነት የምታገኘውን የሚዲያ መድረክ በመጠቀም ኢትዮጵያውያን እረሃብተኞች እየተባሉ ታሪክ እንደሌላቸው እየተደረገ በአሜሪካን ቴለቪዥን ሲስተጋባ እና ሲዛቡ ባቸው፡ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ናቸው። የታሪክ እናት እና አባት የነጻነት ፡ የታሪክ መእራፍ በሚል ጭምር የኢትዮጵያን ብሎም የሌላውን የአፍሪካን ትክክለኛ ማንንነት በማስተጋባት የፈጸመችው ጅግንነት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለኢዮጵያ ለመላው ለአፍሪካ፡  ለአፍሪካን አሜሪክን ነጻነት ለጥቁር ሐዝብ መብት ለአፍሪካ አንድነት ከልጅነትዋ ጀምሮ እስካሁንም ቀጥላበት እየከፈለች ያለችውን መስዋእትነት በቀላሉ የሚገመት አይደለም" ሲሉ ደምድመዋል።   
ክብር ሲንቲያ እና የሐረውርቅ ጋሻው ጊዮን ምግብ ቤት ሲንቲያ የሚወዱን በያይነቱ በመመገብ ላይ እያሉ.July 13, 2013., 6:PM Central time.
Yeharerwer Gashaw at home with Congresswoman Cynthia McKinney on July 11, 2013 at 5: 45 PM CT
.