Alemu Hailemariam Atlanta, GA.
Reunion for peace of Ethiopian Orthodox Church leaders took place in Atlanta, on June 23,2007. The reunion was organized by a committee of three women two men. The purpose of the meeting was to bring peace amoung the church leaders in Atlanta in order to form a peace and unity committee to bring our church leaders (Pope Merkoriwos and Pope Pawulos) from the Diaspora and Ethiopia to negotiation table in order for them to resolve their differences. The reunion for peace organizing committee members are Yeharerwerk Gashaw from Dallas, Tsehaie Bekele, Dr. Tezera Tsegaye, Mrs. Ayelech and Dr. Siyum Gelaye from Atlanta, GA. Thanks to Kibrt Yeharerwerk Gashaw for taking the initative as well as helping with all expenses, Dr. Tezera Tsegaye and his wife community activist Kibrt Tsehaie Bekele for organizing the committee and the meeting, Dr. Siyum Gelaye and his wife Kibrt Ayelech for serving on the committee. "Council of Peace and Unity of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's birth and foundation began in Dallas,Texas"
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተጠነሰሰው መሰረቱ ዳላስ ቴክሳስ ነው።
ሃሳቡም ጅምሩም የመጣው ከ ም እመናን በተለይ ከሴቶች እንደነበረ ከዚህ በታች የምታዩዋቸው ፎቶግራፎች ሕዝቡ አይትዋቸው የማያውቀው ጥሩና ትልቅ ምስክሮች ናቸው። ይሄንንም በደንብ ለመረዳት አንባቢው ሁሉ ይረዳው ዘንድ ከዚህ በላይ በኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላምና ዴሞክራሲ አማካኝነት የተቀመጠውን የእርቁን ዝግጅት ወይም የቀኑ ፕሮግራም እንደምታዩት ትልቅ ማስረጃ ሲሆን ቀጥሎም ከዚህ በታች ያለው ገለጻ በግልጽ የጉባኤውን መነሻ ያስረዳል።
ጅምሩ እንዲዚህ ነው። ይሄውም ሃሳቡን ወጥነው ወደ አትላንታ እና ወደ ሌላም ቦታ ለዚህ ጉዳይ ይጠቅማሉ ብለው ላሰቡን ሁሉ እንድንተባበራቸው የጠየቁን ወይዘሮ የሐረርወርቅ ናቸው። እሳቸው ያነሳሳቸው ስጋታቸውን እና ምን ለማድረግ እንደተነሱና ስጋታቸው የሁላችንም ሰጋት ሊሆን እንደሚገባና ቁጭ ብለን የምናዬው ሳይሆን በተግባር የሰላም ቆስቃሾች መሆን አለብን በሚል ትብብር ጠየቁን የአትላንታ ንዋሪዎችን። ሕልሜና ምኞቴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሚል ያስተላለፉት ጥሪና አላማው ከዚህ እንደሚከተለው ሲሆን በሶስት አስቀምጠውታል ይሄውም፡ አንዱና ዋንኛው ሁለቱን ፓትሪያርኮች ለማስታረቅ። ሁለቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሲኖዶስ ሕግ ብቻ በመመራት በመሃላቸው ሰላም እንዲፈጠር ። ሁለተኛ፡ በቁጥር አንድ የተቀመጠውን ግቡን እንዲመታ ለማድረግ መጀመሪያ አትላንታ ንዋሪ የሆኑትን የሃያማኖት አባቶች ማስታረቅ። አትላንታ የታረቁት የሃይማኖት አባቶች ፓትሪያርኮቹን የሚያስታርቅ አስታራቂ ጉባኤ ይመሰርታሉ ለዛ እንዲረዳ መጀመሪያ አስመራጭ ኮሚቲ ይመሰርታሉ። በዚህ መሃል የእኛ የመመናኑ ሚና ፈጽሞ በአስታራቂ በኮሚቲውስጥ በመግባት ሳይሆን ለሚደረገው የሰላም ጥሪና ሰብሰባ የስብሰባውን ስራ የሚሰራ ኮሚቲ በሃይማኖት አባቶች አማካኝነት በእነሱ ምርጫ የመሰረትና ስራው ላይ መተባበር ይሆናል የኛ ድርሻ። ይሄ የስራ ኮሚቲ ምን እንደሚሆን ወይም እንደሚመስል በተግባር ሲተሮገም ወደ ፊት በዝርዝር አቀርባለሁ በሚል በዚህ መልክ ነበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሰላምና የእርቅ የንድነት ጉባኤ እንደፈጠር ወይዘሮ የሐረርወርቅ ወደ አትላንታ የመጡትና አይታረቅም የተባለውን ቄሳውስት ሁሉ አስታርቀው ወደ ዳላስ የተመለሱት።
ለእርቁም ይሁን ለስብሰቡ እንዲረድዋቸው ወይዘሮ የሐረርወርቅ መጀመሪያ ያነጋገሩት ከአትላንታ ወይዘሮ ጸሃይ በቀለንና ባለቤታቸው ዶክተር ተዘራ ጸጋዬ ሲሆኑ እነዚህ ባልና ሚስቶች በአትላንታ በቤተክርስቲያንም ይሁን በመረዳጃ ማሕበራችን፡ በለንደን፡ በካናዳና ከዛም እዚህ አትላንታ ቤተክርስቲያን እንዲገዛ ግንባር ቀደም በመሆን ላደረጉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርቲያን ስታስታውሳቸው ትኖራለች። ዘአዘር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ በሚለውም ትልቅ አስተዋስዎ ያደረጉ ናቸው ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ በአትላንታ የኢትዮጵያ ቀንን በመመስረት?? ጭምር ለሕዝቡ ሲያገለግሉ የኖሩ ሲሆን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰላም እንዲወርድ ወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋሻው ያቀረቡት የተባበሩኝ ጥሪ በመቀበል እጎናቸው ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በመቆም በአትላንታ ለተደረገው ስብሰባ ሃላፊነቱን ውስደው የስብሰባውን ቦታ በማዘጋጀትና የወይዘሮ የሐረርወርቅን የሰላም ጥሪ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች መሃል እርቅ እንዲወርድ ጥረት ለቄሳውስቱ በማስረዳት ጭምር ትልቁን ሚና በአትላንታ የተጫወቱ ናቸው። በተጨማሪ ዶክተር ስዩም ገላዬና ባለቤታቸውንም በጉዳዩ በማሳመን አብረዋቸው እንዲሰለፉ በማድረጋቸው በስብሰባው እለት ከላይ በፕሮግራሙ እንደተቀመጠው ስብሰባውን የሚመራ ሊቀመንበር ሲመረጥ የሃይማኖት አባቶች በሙሉ በአንድ ድምጽ ሃሳቡን የጠነሰሰችው ከዳላስ መጥታ እዚህ እኛን ያሰባሰበችው ወየሐረርወርቅ መሆን አለባት ባሉት መሰረት ወይዘሮ የሐረርወርቅ ስብሰባውን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ምክትል የተደረጉት ዶክተር ስዩም ገላዬ ነበሩ። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተጠነሰሰው መሰረቱ ዳላስ ቴክሳስ ነው። ያልንበትን እንግዲህ አንባቢያን እንደተረዳችሁ አልጠራጠርም። አድራሻውን አትላንታ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአንድነት ጉባኤን አርማውንም ልብ በሉ ከዚህ በታች።
ይሄንን ሪፓርት ለመን እንዳቀረብኩላችሁ በሚቀጥለው መጣጣፍ አቀርባለሁ።
አለሙ ሃይለማሪያም ከአትላንት ቸር ይግጠምን አሜን።
ይቀጥላል።
Dr. Tezera Tsegaye in a grey suit/Tsehbate Yemane Brhan Asrat in black and Ms. Ayelech.
Abune Selama,Melake Selam Efraim Kebede, Deacon Leaule Qale.
Tsebate Yemane Brhan Asrate speaking.
Abune Philipos, Abune Selama,Mlake Selam Efrem Kebede
YeEthiopiawerk (Yeharerwerk) seen here chairing the meeting.
YeEthiopiawerk speaking.
YeEthiopiawerk (Yeharerwerk) Gashaw with Pope Philpos, Pope Selama, Tsebate Yemane Brhan.
Mrs. Tsehaie (Tsehay) Bekele the organizer of the Atlanta meeting, seen here in a grey and white suit .
D. Leaule Qal seen here speaking to YeEthiopiawerk.
A gift to YeEthiopiawerk Gashaw by Pope Philipos/Pope Selama
Pope Philipos and Tsebate Yemane Brhan speaking.
Leaule Qal Sold out the Atlanta Ethiopian Community by giving cradit to Abune Paulos as the founder of Council of Peace and Unity of the Ethiopian Orthodox Church on his press release below.
ነሐሴ 11/2004 ዓ/ም
Aug 17/2012
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በአምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማውን ከፍተኛና ትልቅ ኃዘን ይገልጻል። እንደሚታወቀው ቅዱስነታቸው ለቤተ ክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻል፣ መጠናከርና መስፋፋት የሚጠቅሙ በርካታ መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን አባትና የሥራ ሰው ነበሩ። በመሆኑም ቅዱስነታቸው በአገልግሎት ዘመናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ሐዋርያዊ ተግባራት ምን ጊዜም ሕያውነታቸውን ሲያስታውሱ ይኖራሉ። ቅዱስነታቸው ብሔራዊውን የአብነት ትምህርትና ዘመናዊውን ዕውቀት አገናዝበው የተማሩ ታላቅ ሊቅ ስለነበሩ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ቅዱስ አባት ነበሩ፤ ይልቁንም ባለንበት ዘመን ቤተ ክርስቲያናችንን በዓለም መድረክ ወክለው ባከናወኗቸው ብዙ ሥራዎች ዘወትር ሲታሰቡ ይኖራሉ። ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን እኒህን ታላቅ አባት በድንገት በማጣቷ ልባዊ ኃዘናችንን በድጋሚ እንገልጻለን። በእውነቱ የቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዜና ዕረፍት ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ኃዘን ነው። P. O. BOX 505, Stone Mountain, GA 30086 E-mail: copauoeotc@yahoo.com 2
ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በቅዱስነታቸው አባታዊ ቡራኬና በቅዱስነታቸው በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ ሦስተኛውን ዙር የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሳለ ይህንን ቤተ ክርስቲያንን አንድ የሚያደርግ ታሪካዊ ሒደት ለፍጻሜ ሳይበቃ የቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት መስማቱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳዝኖታል፤ ሊያስከትል የሚችለው ውጣ ውረድም ከወዲሁ አሳስቦታል። ቅዱስነታቸው የጀመሩትን የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጥረት የመጨረሻ ፍሬ ሳያዩ በድንገት በማለፋቸው ኃዘናችን ወሰን የለውም። የሰላምና አንድነት ጉባኤው በቅዱስነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የጉባኤውን የኃዘን መግለጫ የሚያደርሱ ልዑካንን ሰይሞ ለመላክ በአንድነት ወስኗል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን አሁን ካለችበት አሳሳቢ የልዩነት ፈተና ይበልጥ ወደ ባሰና ወደ ከፋ ችግር እንዳትሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ተቀዳሚ ሥራው በማድረግ ለዘመናት በአንድነቷ ጽንታ የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ታሪኳን ለመመለስና ለማደስ ተገቢውን ሥራ በአንድነት እንዲሠራና እስካሁን ድረስ የቆየውን የልዩነት ምዕራፍ እንዲዘጋ፣ በቅዱስነታቸውና በቅዱስ ሲኖዶስ በጎ ፈቃድ የተጀመረውን የሰላምና አንድነት ሒደትም ለፍሬ ያበቃው ዘንድ ጉባኤው ከታላቅ አደራ ጋር ይማጸናል።
በመሆኑም የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መላው ካህናትና ምእመናን ወምእመናት ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ያስተላልፋል።
1ኛ/ በቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማንን ጽኑ ኃዘን እየገለጽን ከምንም በላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዋነኛውና አንገብጋቢው ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ማድረግ መሆኑን በአጽንኦት እንገልጻለን፤ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ባለፈው ሐምሌ ወር ሦስተኛውን ጉባኤ አበው ለማካሄድ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነበር። ይሁን እንጂ በግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የላክነው ደብዳቤና ባለ ሰባት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳቦች ልከን በነበረበት ጊዜ በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም የሚገኙት አባቶቻችን በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመገኘት ሙሉ ፈቃዳቸው መሆኑን በጽሁፍ ገልጸውልን ነበር። ነገር ግን በአዲስ አበባ በኩል በሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረቡትን ሰባቱን የመፍትሔ ሐሳቦች አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በወርኃ ሐምሌ መግቢያ ላይ ተነገጋሮባቸው በአፋጣኝ መልስ እንደሚሰጠን በደብዳቤ ተገልጦልን ነበር። ያንን መልካም ዜና በጉጉት እየተጠባበቅን ሳለን ይህ ድንገተኛ ኃዘን ቤተ ክርስቲያንን ገጠማት፤ አሁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሦስተኛውን የዕርቀ ሰላም ውይይት በወርኃ ጥቅምት P. O. BOX 505, Stone Mountain, GA 30086 E-mail: copauoeotc@yahoo.com 3
ከሚካሔደው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በፊት ለማካሔድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። በመሆኑም በመላው ዓለም የተበተነችውን ቤተ ክርስቲያን አንድ ለማድረግ፣ በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ የሚገኙት አባቶችም በቅርቡ በሚዘጋጀው የሰላምና አንድነት መድረክ ተገናኝተው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ተነጋግረው፣ ችግሩን በውይይት በመፍታት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ያደርጓት ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል።
2ኛ/ ቤተ ክርስቲያን ለወደፊቱ ተለያይታ እንዳትቀር በሀገር ውጭና ከሀገር ውስጥ ባሉት አባቶች መካከል ያለው ልዩነት በአንድነት ሳይፈታ ሌላ ፓትርያርክ የመተካቱን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወዲሁ በከፍተኛ አትኩሮት እንዲያስብበት፤ ይልቁንም የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት በማጽት የቀድሞውን የአንድነት ታሪክ ትመልሱት ዘንድ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ስም ከልብ ይማጸናል።
3ኛ/ በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትም ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠበቅበትን የበኩሉን አስተዋጽኦ በአግባቡ እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን።
4ኛ/ በመላው ዓለም ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ማኅበረ ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን አንድ በማድረጉ ታሪካዊ ሒደት ላይ በጾም፣ በጸሎትና በሚያስፈልገው ማናቸውም ነገሮች ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ይሠሩ ዘንድ በትሕትና እንማጸናለን።
በመጨረሻም አምላከ አበው እግዚአብሔር የቅዱስነታቸውን ነፍስ ከማኅበረ አበው ኄራን እንዲደምርልንና ለመላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለቅዱስነታቸው ቤተ ሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን።
የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ያሳየን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ።
Here name shuffling readers think about this. Filing 01/06/2011
CompanyName: | ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH PEACE AND UNITY COUNCIL, INC. | ||
Status: | Unknown | Filing Date: | 01/06/2011 |
Entity Type: | Corporation | File Number: | 4923870 |
Filing State: | Delaware (DE) | Qualifying State: |