ይሄ ብሎግ ፤ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት ጋር በመተባበር የአገራችንን ጉዳይም አስመልክቶ እንዳስፍላጊነቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያቀርብ መህኑን ለህዝቡ እየግለጽኩኝ ፤ በሕብረተሰባችን በተለይ በዳላስ ስር ሰዶ በትግሬ ነጻ አውጪ እገዛና የድብቅ አመራር እየተበጠበጠ ያለውን የዳላስ ፎርት ወርዝና በሌላም አካባቢ ሰላም ላጣው የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና ሰላም፤ ወደ ተለመደ የእርስ በእርስ መተማመንና ፤ የልብን ሃሳብ የመካፈል ልምድ መልሶ ለማስፈን ይረዳ ዘንድ ፤ በተለይ ውቅቱ የዳላስ ንዋሪን ስለውነትን ትክክለኛ መረጃ የሚሰጠው ወገን የራበውና የጠማው ጊዜ በመሆኑ ብዙ ኢትዮጵያውያን በጠየቁት መሰረት ይህ ሕዝብን የሚወክል አንድ ብሎግ በዚህ መልኩ በሕብረተሰባችን ስም ዲኤፍደብልዩ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብሎግ በሚል ስም ሊከፈት ችልዋል። መታወቅ ያለበት በጥብቅ ይህ ብሎግ ለየኢትዮጵያ ሕዝብ አገልግሎት መስጫና ፤ ውነቱን ብቻ የሚጎዳውንም የሚጠቅመውንም በማቅረብ፤ ሕዝቡ እራሱ ወይም ሕብረተሰቡ የሚያመቸውንና ፤ ትክክለኛ መስሎ የሚታየውንና የሚጠቅመውን መፍትሄ በሕብረት እንዲነጋገርበትና እፍጻሜ ላይ እንዲያደርስ ይረዳው ዘንድ ብቻ ለማድረግ የተከፈተ በሎግ መሆኑን ነው። የተወሰነ ስብስብ ፤ወይም የግለሰቦች የግልጥቅም ማራመጃና ፤ የእርስበእርስ መካካቢያም አይደለም።
የኢትዮጵያ ብሂራዊ የስዴት መንግስትን አስመልክቶ፤ ምናልባት ያላወቃችሁ ብትኖሩ ፤ የመላው ኢትዮጵያ ድርጅትን ለማፍረስ እንቀናጅ ብለው በሻጥር ፤ ቀስተዳመናና የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ሊግ በሚል ጠጋብለው፤ ተቀናጀን ካሉ ከስድስት ወር ብሁዋላ ፤ሰርጎ ገቦችና ፤ አስመሳይ አባላት የመላው ኢትዮጵያን ድርጅት ሲያፈራርሱት ፤ የትግሬ ነጻ አውጪ ወይም ወያኔ፤ ኢትዮጵያን በግላጭ ይሄው አገኘሁዋት እንደተመኘሁዋት፤ በሚል ከበሮ እየደለቀ ጮቤ ሲመታ ከነድጋፊዎቹ ፤ በአገር ቤትም በሰው አገርም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሴቱም ወንዱም አንገቱን ያልደፋና ተስፋ ያልቆረጠ ኢትዮጵያዊ አልነበረም። በዚያን ቀውጢና የቁርጥ ጊዜ ነበር ሜዳላይ የተጣለውን የኢትዮጵያን ክብርና የሕዝብዋን የአንድነት መለዮ ከነሰንደቅ አላማው ብድግ አድርጎ፤ ከፍ በማድረግ ሕዝቡንና ኢትዮጵያን የሚወክል መንግስት የተቅዋቁዋመው። የኢትዮጵያ ብሄርዊ የስዴት መንግስት፤ በአለም ምንግስታት ፤ በአሜሪካን መንግስት ጭምር ከ2008 ከተመሰረተ ጀምሮ ታዋቂነት ያገኘሲሆን፤ በሕግ ፤ በሜሪካን አገር በመንግስትነት የተመዘገበ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወክሎ የሚንቀሳቅስና የሚያገለግል መንግስት ነው። Ethiopian National Government In Exile ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ሴት የተመሰረተ መንግስት ሲህን፤ በኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያን ሴቶች የአገር ባለቤትነትን መብት አስጠብቆ፤ ሴቶችን የምትወክል አንበሳ/የአንበሳነት አርማው ላይ ከተለመደው የወንድ አንበሳ እኩል፤ ያስቀመጠና ያስመዘገበ ብቸኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው። በፓለቲካ ድርጅት ስም ሲሰራ የነበረውን ከ1986 ጀምሮ በአውሮፓ አቆጣጠር፤ ቀጥሎም በመንግስትነት ከተመሰረተ ጀምሮ ፤ ቀደም ሲል የነበረውን ግንኙነት በማጠናከር በመንግስትነት ፤ ከብዙ መንግስታት ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱን ቀጥልዋል። በርካታም ስራዎች ተሰርተዋል፤ ውጤትም አስመዝግብዋል። ለኢትዮጵያ የፓለቲካ እስረኞችና ስዴተኞች ትልቁ ብቸኛው አጋራቸው ሆንዋል። ለሴቶችም የአገር ባለቤትነትን መብትንም አስጠብቅዋል አጎናጽፍዋል። ይህ የስዴት መንግስት፤ የኢትዮጵያ ሴቶችን ፤ የመጀመሪያ አድርጎናል የስዴት መንግስት ከአገራችን ውጪ በመመስረታችን። በበለጠ ለመረዳት ድህረ ገጹን ይመልክቱ www.ethiopiannationalgovernmentinexile.org/ .
በቅርብ የመክፈቻችን መነጋገሪያ የሚህነውን የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጋርላንድ ቴክሳስን አስመልክቱ ለመጀመሪያ በብሎግ በምናቀርበው አርስታችን እስክንገናኝ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ ለዳላስም ንዋሪው ጭምር መልካም የሳምንት መጨረሻ እንዲያደርግልን ለሁልላችንም አምላክን እንለምናለን።
የሐረርወርቅ ጋሻው
ዲፍደብልዩ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብሎግ፤ መስራች አዝጋጅና አቅራቢ።
Subscribe to:
Posts (Atom)