Tuesday, September 27, 2011

"ደመራ" በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

          ደመራ
  (በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባሕላችን አንጻር
(
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
 mailto:nigatuasteraye@yahoo.com  መስከረም ፳፻፬ ዓ.
 ደመራደመረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው:: ትርጉሙ ጭመራ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው:: ጥሪት (ካፒታል) እንዳይጎድል እንዳይቀነስ ይልቁንም እየበዛና እያደገ እንዲቀጥል ጠብቆ መያዝ የሚያስችል ደመራ ነው:: ስሙ እንደሚያመለክተው ማስታወሻነቱ ለተጠራቀመ፥ ለተሰበሰበና ለተጨመረ ነገር ነው:: በዓሉ አካቶ የያዛቸዉ ሥርዓቱ የሚከናወንባቸው ቁሳቁሶች፥ የደመራው እንጨቶች፥ ችቦዎች፥ አሽክቶችና፥ ሌሎችም በበዓሉ ዙሪያ የሚታዩት፥ የሕዝቡን ስሜት አንድ ላይ ሰብስቦ ስለያዘ ደመራ ተባለ:: የደመራ ተቃራኒው ቅነሳና ከፈላነው:: በአገራችን በተፈጠረው ታሪካዊ ክስተት ምክንያት፥ በነገረ መለኮት ከኛ ጋራ አንድ ከሆኑት አኀት አብያተ ክርስቲያናት በማይካፈሉት ሁኔታ በተለየና በደመቀ ሥርዓት በመላ ኢትዮጵያ ይከበራል
• በሃይማኖታችን፥
• በታሪካችንና በባሕላችን
አንጻር በመዳሰስ ይሕችን ጦማር እደመድማለሁ:: ካህኑ የመጀመሪያዋን የደመራ መብራት "ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ" በሚለው በሊጦኑ ቃለ ቡራኬ ባርኮ፥ ከደመራው እንጨት ጋራ እንዲደምራት ሕዝቡን በአስተዳደር ለሚመራው ሰው ያቀብለውና የደመራውን እንጨት ይለኩሰዋል:: ከዚያ በኋላ በተዋረድ ያገር ሽማግሌ ሁሉ ችቦውን እያቀጣጠለ በደመራው ላይ ይጨምረዋል:: በዚህ ሥርዓት የሚከበረውን የደመራ በዓል በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባህላችን አንጸር በመጠኑ እገልጻለሁ:: ዛሬ ባለንበት ዘመን ይህችን እሳት ባርኮ ሰጭው መንፈሳዊው ካህን ማነው? እሳቷን ከካህኑ ተቀብሎ በደመራው ላይ የሚለኩሳትስ ብቃት ያለው የአገር መሪ ማነው? ከዚያስ በተዋረድ እየለኮሰ ደመራውን የሚያቃጥል ሽማግሌ ማነው? በማለት ከሊቃውንት አበው የተማርኩትንና የሰማሁትን :: በመጀመሪያ በሃይማኖታችን አንጻር እነሆ! 1
ደመራ በሃይማኖታችን አንጻር የአምልኮታችንን ሥርዓት ተንተርሶ "The Wisdom Compass to Eternal Life" በሚል ርእስ አቤል ጋሼ ጌታችን ያስተማረውን ጸሎት መሠረት በማድረግ በቀመር መልክ ብቅርቡ ባቀረበው መጽሐፍ ብዙውን ዳሶታል:: አቤል ጋሼ በገጽ ምዕ 10 ገጽ 135 ላይ "While we keep reciting ‘Have mercy on us’ twelve times corresponding the name of the Father, the son and the Holy Spirit" ብሎ የጠቆመውን ከደመራ ጋራ ያለንን መንፈሳዊና ባሕላዊ ግንዛቤ ለመግለጽ እሞክራለሁ:: አምልኮታችንን ጀምረን የምንፈጽመው ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፪-፭ እንደገለጸው፥ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ አይቶ እንደነገረን፥ (ምዕራፍ ፬ እና ፭) የእግዚአብሔርን ዙፋን በተሸከሙት ኪሩቤል የአምልኮት ዘይቤ ነው:: እነዚህ ኪሩቤሎች በላያቸው ላለው ፈጣሪ አምልኮት ሲያቀርቡ ሶስት ጊዜ "ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበርክ ያለህ፥ ወደፊትም የምትኖር" እያሉ ነው:: የቀደሙ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትም ይህን መሠረት በማድረግ "ንሕነሰ ነአምን ከመዝ እስመ ሥሉስ ቅዱስ እሩያን እሙንቱ በተዋሕዶተ መለኮት ወፍጹማን በ፫ቱ አካላት ዘውእቶሙ ፩ዱ አብ ቅዱስ፥ ወ፩ዱ ወልድ ቅዱስ፥ ወ፩ዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" (ሃይ ምዕ፷፪፡፲፭):: እያሉ የነገረ መለኮቱን መሠረት አስተማሩ:: ማለትም፥ "እኛም እንደ ሱራፌልና ኪሩቤል፥ ኢሳይያስ ባየው፥ ዮሐንስም በገለጸው መንገድ በአካል ሶስት፥ በመለኮት አንድ እያልን እናምናለን፥ አምነንም እናመልከዋለን፥ እናስተምረዋለን":: በኪዳን ተጀምሮ በቅዳሴው የሚፈጸመው አምልኮታችን የሚከናወነው በዚህ መሠረት አንድም ሶስትም እያልን ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ "ሕጻን ሳለሁ፥ እንደ ሕጻን አስብ ነበር እንደ ሕጻንም እቆጥር ነበር" እንዳለው ሕጻናት ነገሮችን ማጤን የሚጀምሩት የራሳቸውን ጣቶች በማየት፥ የሚዳስሱትንም ለመቅመስ ጣቶቻቸውን በመጉረስ ነው:: ቁጥር መማር የምንጀምረው በጣቶቻችን ነው:: በጸሎታችን የሰማዩንና የምድሩን ሁኔታ ከዳሰስን በኋላ የምንደመድመው በጣቶቻችን ላይ ባሉት አጽቆች (phalanxes) ቀመር ነው:: Mutation (የተፈጥሮ ባሕርይን መቀየር) ከሚባለው አጋጣሚ በቀር ያንዱ እጅ ጣቶቻችን ከአምስት አይጎሉም፥ አይተርፉም:: አውራ ጣታችንን ቆጣሪ በማድረግ በአራቱ ጣቶቻችን ላይ ያሉትን አጽቆች እንቆጥራለን
12 :: አራቱ ጣቶቻችን እያንዳንዳቸው ሶስት አጽቆች አሏቸው:: በያንዳንዷ ጣት ላይ ያሉት አጽቆች ስብስብ መጠን ለማግኘት ስንደምራቸው ፲፪ ቁጥር እናገኛለን:: እኒህ በጣቶቻችን ላይ ያሉት ፲፪ አዕጹቅ ቁጥሮች ለአምልኮታችን ሥርዓትና የባሕላችን መሠረቶች ናቸው:: ዛሬ በየብስ፥ በባሕርና በአየር ውስጥ ተቆልፎ የኖረበትን የፍጥረት ምሥጢር የሰው ልጅ እየበረገደ የገባውና በመግባት ላይ ያለው በደመራ በተጀመረ ቁጥር ነው:: ን አጽቆች ለ4 ጣቶቻችን ብናካፍላቸው የምናገኘው ውጤት ሥላሴ ማለትም 3 ነው:: 12 ን አጽቆች ባንዷ ጣት ላይ ላሉት ለ3 አጽቆች ብናካፍላቸው የምናገኘው ጸወርት መንበር የሚባሉትን 4ቱን ኪሩቤል ነው:: እንደገና 3 እና 4 ብንደምር የሳምንቱን ዕለታት ልክ ቁጥር 7 ን እናገኛለን:: ፊደሎቻችንም የተዋቀሩት በሳምንቱ ዕለታት ላይ ነው:: በግዕዝ () ተጀምራው የሚያልቁት በሳብእ () ቁጥር ነው:: ፩፥ ፫፥ ፬፥ ፯ ና ፲፪ ቁጥሮች ለብዙ ነገሮች ምልክቶች ናቸው:: 2
በአራቱ ጣቶቻችን ያሉት ፲፪ አጽቆች፥ አንድ ቀን የተባለው ብርሃን የያዛቸውን አስራ ሁለት ሰዓቶች ያስታውሱናል:: አንድ አመት የሚሰጡንን የአስራ ሁለት ወራት ጥርቅም ይሰጡናል:: የክርስቶስን ምድራዊ አካል ምንጭ ለማግኘት የምንቆጥራቸውን የ፲፪ቱን ነገደ ፳ኤል ቁጥር ይሰጡናል:: በመቀጠልም ከክርስቶስ ቀጥለው ክርስትናን ያስፋፉትን የሐዋርያትን ፲፪ ቁጥር ይጠቁሙናል:: የቤተ ክርስቲያናችን የጸዋዕ ማኅበራት፥ በስላሴ፥ በመድኃኔዓለም፥ በእመቤታችን፥ በመላእክት በጻድቃንና በሰማእታት ስም የሚመሰረቱት በ ፲፪ ቁጥር ነው:: በራዕየ ዮሐንስ ላይ እንደተገለጸው፥ የያንዳድዱ አጥቢያ (ሰበካ) ቁጥር በአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል፥ በ፲፪ ሐዋርያት፥ በ፲፪ ወራትና በ፲፪ ሰዓተ መአልት (ቀን) ልክ ነው:: አካለ መጠን የደረሰ ሁሉ በያለበት አጥቢያ (ሰበካ) በ ፲፪ እየተመደበ ይደመራል:: ሁሉም የጽዋዕ ማኅበራት ለያንዳንዳቸው መምሕር ይመደብላቸዋል:: እያንዳንዱ አባል ከዓመቱ ውስጥ ካሉት ወራት አንዱን ይወክላል:: ከነገዶች ውስጥ አንዱን፥ ከሐዋርያትም አንዱን ይወክላል:: በዚህ መንገድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት አባል የሆነ ሁሉ በዚህ ቁጥር እየተካተተ (እየተደመረ) የጽዋው ተካፋይ ይሆናል:: እያንዳንዷ በ፲፪ ቁጥር የተዋቀረችው የጽዋዕ ማኅበር አባላት ከመካከላቸው በእምነትና በመንፈስ ላቅ ያለውን መርጠው ሙሴ የሚባል ለማኅበሩ መሪ ይሰይማሉ:: እያንዳንዷ የጽዋዕ ማኅበር የመረጠችው ሙሴ (መሪ) ደግሞ፥ የሚመራትን የጽዋዕ ማኅበር በመወከል አንድላይ ተሰብስበው ይደመሩና የራሳቸውን የጽዋዕ ማሕበር፦ ማሕበረ በኩር ብለው ይሰይማሉ:: ለማሕበረ በኩሩ መምሕር ሆኖ የሚሰየመው በሙያና በችሎታ ከሊቃውንቱ መካከል ተመርጦ የደብሩ አለቃ ነው:: የደብሩ አለቃ ዋና ኃላፊነት እየዞሩ የጽዋዕ ማኅበራቱን አባላት የሚያስተምሩትንና የማኅበረ በኩሩን አባላትና ሙሴዎች አንድላይ እየሰበሰበ ማስተማር ስለሆነ በጥንቃቄ ይመረጣል:: የመሳፍንቱ ሥርዓት ተጽእኖ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባያዘናጋት ኖሮ የያንዳንዷን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መምራት የነበረበት ይህ ማኅበረ በኩር የተባለው ጉባዔ ነበር:: በተራ በየቤቱ በሚደረገው ጉባዔ ተረኛው ቄጠማውን ጎዝጉዞ፥ ውሐውን ቀድቶ ይጠብቃል:: የአምልኮቱ ማዕከል ዮሐንስ የታረደው በግ እያለ የገለጸው ክርስቶስ ነው:: ሁሉም ነጭ ልብስ ለብሰው ስለታረደው በግ ፍቅር፥ ክብር ውዳሴና አምልኮ ለማቅረብ ይሰበሰባሉ:: በሙሴያቸው አስተናባሪነት ካህኑ በራዕየ ዮሐንስ ላይ የተመሠረተውን ሥርዓት በመጠበቅ ጉባዔውን ይመራል:: ከዚያም የማኅበሩ ሙሴ ባለወር፥ ባለሳምንት ብሎ ጉባዔው የተሰየመበትን ስም እየጠራ "የጉባዔው ወዳጅ ማነህ እኔነ ነኝ የምትል" ብሎ ያውጃል::ተረኛው ተዘጋጅቶ በመጠበቅ ላይ ነውና እኔ ነኝ ብሎ ወደ መሐል ይቀርብና ይቆማል:: "እኔ አለሁ ብለህ እንደቆምክ መድኃኔለም ይቁምልህ" ይለዋል:: ጽዋውን በመቀባበል በጽዋዕ ውስጥ ያለውን ጠበል ሁሉም ይካፈለዋል:: ከዚህ በኋላ ጽዋውን የተቀባበሉ አካላት በጉባዔው ፊት ይወድቃሉ:: መምሕሩ "እንደዚህ እንደወደቃችሁ ኃይለ አጋንንትን ያውደቅላችሁ" ብሎ አቤል ጓሼ እንደገለጸልን ሰዓታቱን፥ ወራቱን ነገደ እስራኤልን፥ ሐዋርያትን በመጨረሻም ስላሴን አራቱ ኪሩቤልን አጠቃሉ ደምሮ በያዘው ፲፪ ቁጥር "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ይልና ያለፈውን ይቅር ይበለን ከሚመጣውም ጠብቆ በሚቀጥለው ጉባዔያችን ያገናኘን ብሎ የአምልኮቱን ሥርዓት ይዘጋዋል:: ነፍሳቸውን ይማርና ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰበካ ጉባዔውን ሲነድፉት፥ በዚህ ቅዱስ ታሪክና ባሕል የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደር ለማዋቀር ነበር፡፡ 3
ደመራ በታሪክችንና በባህላችን አንጻር ደመራውን የጀመረችው በሶስተኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ እሌኒ የምትባለው የቆስጠንጢኖስ እናት ክርስቲያን ንግሥት ናት:: የጀመረችበት ምክንያትም የክርስቶስ ተቃራኒዎች፥ የክርስትና ንክኪ ያለውን ፍንጭ ሁሉ ለማጥፋት ባደረጉት ጥረት፥ ከክርስትና ፍንጮች አንዱና ዋናው የክርስቶስ መስቀል ስለነበረ፥ በጉርጓድ ቀበረውት ነበረና፥ ፈልጋ ለማግኘት ነው:: እሌኒ ሕይወቷ የተመሠረተው በክርስትና ፍቅር ላይ ስለነበረ መስቀሉን ለማግኘት በብርቱ ጣረች:: መስቀሉን ለማግኘት የተጠቀመችበት ስልት፥ እሳት አንድዳ ጢሱ እንዲመራት በመጸለይ ነበር:: የሚቃጠል ነገር ሰብስባና ደምራ በማንደድ ጢሱን ተከትላ በመሄድ መስቀሉን አገኘችው:: የታሪኩ መነሻ እሌኒ እንደሆነች በያመቱ ስንናገረው የኖርነው ነውና፥ በዚህች ጦማርም መሸፈን ስለማልችል በእሌኒ ዙሪያ የሚነገረውን ታሪክ እዚህ ላይ ገትቼ፥ ከራሳችን ታሪክ ጋራ ወደተያያዘበት መስመር እሻገራለሁ:: የታሪኩ መሠረት ይህ ሆኖ ሳለ ንግሥት እሌኒ በጀመረችበት ቦታ፥ እኛ በምናደርገው ሥርዓት ዓይነት ሊከበር ቀርቶ የሚያስታውሰውም የለም:: ታዲያ ለምን እኛ ብቻ በዚህ መልክ እናከብረዋለን? የሚል ጥያቄ ማስከተሉ አይቀርም፥ ተገቢም ነው:: መልስ የሚጠበቀው ከዚያ ወዲህ በየዘመኑ ወደ አገራችን ከገቡት ባሕርያቸው ከደመራ ይልቅ ወደ ከፈላ ካዘነበሉት አብያተ ክርስቲያናት አይደለም:: የደመራውን ታሪክ የማስተማርና በደመራው ዙሪያ ለሚነሱት ጥያቄዎችም የመመለስ እዳ፥ ሸክምና ግዴታ ያለባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት:: የጥምቀቱን በዓል ከዓለም ክርስቲያኖች ለየት ባለ መንገድ እንደምናስታውሰው፥ በንግሥት እሌኒ ሕሊና ውስጥ ይነድ የነበረውን የክርስቶስን ፍቅር በያመቱ ደመራ የሚል ስም ሰጥተን በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች በማያስቡበት በተለየ መንገድ እናከብረዋለን:: በዓላት በምክንያት የሚጀመሩ፥ የታሪክ መነሻዎች ናቸው:: ባንድ ወቅት የተጀመሩት ሳይረሱ የሚታረመውን እያረሙ፥ የሚጨመረውን እየጨመሩ ዓለም እስክታልፍ የሚቀጥሉ ሕዝቦች፥ በቅኝ ገዥዎች አዕምሯቸው ሳይዝልና ሳይዘነጋ እስከ መጨረሻ ጠንክረው የሚጓዙ እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ኅብረተ ሰቦች ናቸው:: ይህ በዓል ከተጀመረበት ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ በገጠሙን ክፉ ቀናቶች ሁሉ ሳያቋርጥ ከኛ ደርሷል:: በዓላት ሁለት መንገዶች አሏቸው:: ከሁለቱ አንዱ ከጣዖትና ከባዕድ አምልኮት ጋራ የተያያዘ ቅዱስ መጽሐፍ የሚያወግዘው ነው:: ከሰይጣን አምልኮት በራቀ መንፈስ ባሕልን ታሪክን አዝለው በመመላለስ የሚታወሱ ሁሉ በዓላት፥ ይዘታቸው እየሰፋ የሚቀጥል መጻሕፍቶች ናቸው:: ይህ አይነት የSocial Memory መጽሐፍ የሌለው ሕብረተ ሰብ በኛ ግንዛቤ እንስሳት ብቻ ናቸው:: ከዚህ ቀደም ቅበላ (http://www.medhanialemeotcks.org/pdf/ISAT.pdf) በሚል ርእስ እንደገለጽኩት፥ በሐዘንና በደስታ፥ በልቅሶና በሳቅ፥ በመሸበርና በመረጋጋት በምትናወጠው ዓለም የሚኖር ሰው፥ በዓሉን የሚያከብረው በሚገጥመው ሁኔታ ነው:: አንድ ጊዜ የተዘጋጁ መጻሕፍት በውስጣቸው የያዙትን ምዕራፍ በሚገጥሟቸው ተመሳሳይ አዳዲስ ክስተቶች እያሰፉ በመደጋገም እንደሚታተሙ ሁሉ፥ በዓላትም እንደዚሁ በየአመቱ የሚገጥማቸውን እየጨመሩ ስለሚሄዱ የሕብረተ ሰቡ ትዝታ ወይም የ Social Memory መጻሕፍት ናቸው:: 4
ለደመራው በዓል መነሻዋ እሌኒ ብትሆንም፥ እሌኒ ደመራ ብላ አልሰየመችውም:: ይህ በዓል ደመራ ተብሎ አሁን በምናከብረው ሁኔታና መንፈስ እጅግ ሰፍቶ ከመከበሩ በፊት፥ ወደ እኛ ተሻግሮ መጥቶ ሲከበርና ሲታወስ ቢኖርም፥ የመስቀል በዓል እንጅ ደመራ እየተባለ አልነበረም:: እሌኒ የሰራችውን ታሪክ በማስታወስ ሲከበር የቆየው የመስቀል በዓል፥ በአጼ ገላውዴዎስ ዘመን አዲስ ታሪካዊ ክስተት ገጠመውና ሊቃውንት አበው፥ ከታሪካችን ጋራ ደምረውና አስፍተው ደመራ ብለው ሰየሙት:: ከሊቃውንት አበው መምሕሮቼ እንደሰማሁት፥ ግራኝ መሐመድ ኢትዮጵያን በወረራት ዘመን፥ የአገሪቱ መሪ አጼ ልብነ ድንግል በዚያ ዘመን ገናና ይባል የነበረውን የፖርቹጋሉን መንግሥት እርዳታ ጠየቁ
• ፩ኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሮማ ካቶሊክ ሥር፥
• ፪ኛ ኢትዮጵያንም በራሱ ቅኝ አገዛዝ ሥር ለማድረግ ከሮማው ፓፓ ጋራ ሲሸርብ ዘገየ:: የፖርቹጋሉ መንግሥትም ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ፦ :: ከዚህም ጋራ የዘመኑ የጉዞ ሁኔታ ለመዘግየታቸው ተጨማሪ ችግር ነበር ይላሉ:: በዚያም ሆነ በዚህ፥ አጼ ልብነድንግል ከጠየቁበት ወቅት እጅግ ዘግይተው፥ ጦርነቱ ከበረደ በኋላ መልእክተኞቹ ደረሱ:: አጼ ልብነ ድንግል ሞተው፥ በጦርነቱ የደቀቀው ሕዝብ በአጼ ገላውዴዎስ መሪነት በመቋቋም ላይ ሳለ፥ በሸርና ሸፍጥ የተላኩት የፖርቹጋል ሰዎች ዘግይተው ከኢትዮጵያ ደረሱ:: ጦርነቱ እንዳለቀና የነሱም እርዳት እንደማያስፈልግ ሲረዱ ወደ አገራቸው በመመለስ ፈንታ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ በመኖር በሕዝቡ መካከል እየገቡ፥ አሁን ቻይናዎች በአገራችን ላይ እንደሚያደርጉት ማለት ነው፥ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን እየተጋቡ በመዋለድ ኑሯቸውን ማስፋፋት ጀመሩ:: በአገሪቱ ባሕል ሃይማኖትና ፖለቲካ እየገቡ የሕዝቡን አንድነት የሚፈታተን ሸርና ደባ መሥራት ጀመሩ:: በዚያን ጊዜ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈጠረው ሁኔታ በዘመናችን የተደገመ ይመስላል:: ከአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መወገድ ጀምሮ ደርግ እስኪፈርስ ድረስ በውጭ ጠላት ባይሆንም እርስ በርስ በተካሄደው እልቂት ያለቀው ሕዝብ አገሪቷ ያመረተችው ምርጥ ዜጋ ነበር:: አገሪቱ እነዚህን ሁሉ አጥታ፥ ህዝቡም ተዳክሞ ባለበት ወቅት፥ ዘረኛው ያቶ መለሰ መንግስት አገሪቱን በግላጭ ተቆጣጠራት:: እንደዚሁ ሁሉ በግራኝ መሐመድ ካለቀው የተረፈው ሕዝብ ከግራኝ መከራ በኋላ ሳያርፍ እንደገና ፖርቹጋሎች ከፈጡሩበት መከራ ውስጥ ገባ:: ከኤርትራ ጋራ በንጉሡና በደርግ ዘመን በተደረገው ግጭት ካለቀው ሕዝብ ይልቅ በአቶ መለሰ መንግሥት ያለቀው ወገን ይበዛል እንደሚባለው መሆኑ ነው:: በፖርቹጋሎችና በኢትዮጵያውያን መካከል ጥላቸውና መናናቁ እጅግ በማየሉ በቅጽል ስምና በተረብ መዘላለፍ ተጀመረ:: ኢትዮጵያውያን ለፖርቱጋሎች ትኋን የሚል ስም ሰጧቸው:: ፖርቱጋሎች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ቁንጫ የሚል ስም ሰጧቸው:: በመናናቅ እርስ በርስ የተሰጣጧቸው የቅጽል መግለጫዎች ትርጉም አላቸው:: ኢትዮጵያውያን ፖርቹጋሎችን በትኋን ጠባይ የገለጿቸው፥ ትኋን የሰው ደም መምጠጥ የምትጀምረው ጨለማ ተንተርሳ፥ ቀስ ብላ እየተጠራራች ከየስርቻ በመውጣት ነው:: ደሙን የመጠጠችው ሰው ካያት ሮጣ አታመልጥም:: የመጠጠችውን ደም ተሸክማ ስትንገዳደገድ ትደፈጠጣላች:: ጥላው የምትሔደው ክርፋት በቶሎ የሚለቅ አይደለም:: ፖርቹጋሎችን እንዲህ ናችሁ ለማለት ኢትዮጵያውያን ትኋኖች ብለዋቸዋል:: ቁንጫ ለመባላት ቀንም ሌትም አትመርጥም:: ይዞ ለመግደልም የማትጨበጥ ፈጣን ናት:: የሚሸት ነገር የላትም:: ኢትዮጵያውያኖችንም አይያዙም፥ አይጨበጡም፥ ጠላታቸውን ለማጥቃት ቀንና ሌሊት አይመርጡም ለማለት ፖርቹጋሎቹ ኢትዮጵያውያንን ቁንጫዎች ብለዋቸዋል:: በዚህ መልክ መሰዳደቡና መተራረቡ አድጎ ጸቡና ጥላቻው እየከረረ ሄደ:: እንዲያውም በአድዋ አካባቢ የነበሩት ፖርቹጋሎች ድርጅታቸውን የበለጠ አጠናክረው "መንግሥታችሁ በፖርቹጋል ምንግሥት ሥር ካልሆነ ተቆርጣችሁ የቀራችሁ ናችሁ" እያሉ በመስበክ በሌላው 5
ክፍለ አገር ሕዝብ ላይ ከፈጸሙት የመከፋፈልና እርስ በርሱ የማገዳደል ደባ በአድዋ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት እጅግ የከፋ ነበር ይባላል:: ይህንም ለማስታወስ በአድዋ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ "ዓኾ ዓኾኋይ ሆይ ሆያዬ ንጎናይ በርሆ" በማለት ደመራውን በመዞር በያመቱ ያስታውሱታል:: ይህም ማለት፥ "እናንተ ተቆርጣችሁ የቀራችሁ እያሉ ይዘልፏቸው ስለነበረ፥ እኛ ኢትዮጵያውያን የተቆረጣችሁ እየተባልን በገዛ አገራችን ስንሰደብ ብንኖርም፥ ዛሬ በዚህ ችቦ የነጻነት ብርሃን በራለን" እንደ ማለት ነው ብለው ሲናገሩ ሰምቻለሁ:: የትግርኛውን ቋንቋ ስለማላውቀው አበላሽቼ እጽፈውና እተረጉመው ይሆናል:: ይቅርታ እየጠየቁ የማቃናቱን ኃላፊነት ባካባቢው ለተወለዳችሁ ወገኖቼ እተወዋለሁ:: ንጎናይ ማለት ቆራጣ ማለት ነው ሲሉ ሰምቻለሁ:: ከዚህም ጋራ ለአገራቸውና ላንድነታቸው ጸንተው የቆሙ የትግራይ ሰዎች በአማረኛ አሽከት በትግርኛ ጸጎጎት የምትባለውን የመጣበቅ ባሕርይ ያላትን ሐርግ በራሳቸው ላይ ያስራሉ:: ሐረጓን ያንድነታቸውና የጽኑ መተማመናቸው ምልክት አርገው ተጠቅመውባትል:: በአሽክቷ የተጠቀሙበትን ምሥጢር መስከረም ፲፮ በያመቱ ጽንዒ እያሉ ያስታውሱታል:: የፖርቹጋሎች ሁኔታና አዝማሚያ ኢትዮጵያውያንን እያሳሰባቸው መጣ
":: ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይህን ነገር ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሕዝባቸው ሳይጎዳ እነዚህን ትኋኖች እንዴት እንደሚገላገሏቸው አጠኑና የመስቀሉን በዓል እንዴት እንደሚጠቀሙበት ዘዴ አመነጩ:: ምሥጢር ማደላደል በሚባለው ጉባዔ ላይ በየኔታ ፍስሐ መሪነት፥ ነፍሶቻቸውን ይማርና የኔታ አንዳርጌና የኔታ አምዴ የቅኔ መምሕራን ሲነጋገሩ እንደሰማሁት፥ በዚያ ዘመን የነበሩ ሊቃውንት እንዴትና በምን መንገድ ፖርቹጋሎችን ላንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጠራርገው ለማጥፋት ሲያስቡ፤ በመጽሐፈ መሳፍንት ምዕ ፱ ከቁጥር ፳ ላይ ተመዝግቦ እንደምናነበው "ለትጻዕ እሳት እምቤተ አቤሜሌክ፥ ከመ ትብላእ አብያተ ሴኬም፡ ወትሜሎም:: ወለእመ አኮ እሳት ትጻእ እምቤተ ሴኬም ወትሜሎም ከመ ትብላዕ ቤተ አቤሜሌክ" የሚለው ንባብ ትዝ አላቸው:: ይህም ማለት "እኛ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራችን የተደጋገመ ግፍ እየተፈጸመብን ነው:: ይህች ከኢትዮጵያውያን ቤት እየተጫረች የምትወጣ የዘንድሮው የመስቀል በዓል እሳት፥ በሸርና በሸፍጥ በእርዳታ ስም መጥተው የወረሩንን ፖርቹጋሎችን ትብላ፥ ለአገራችን ለነጻነታችን መታገላችን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ ረድኤቱን ከነፈገንም፥ ለዘላለም በፖርቹጋሎች ሥር ተጠቅተን ከመኖርና ለልጆቻችንም የተገዥነትን ውርስ ከማውረስ ይሕች ከየቤታችን የጫርናት እሳት እኛኑ ትብላን" ብለው ቆርጠው ተነሱ:: የመስቀል በዓል ፖርቹጋሎችን የማይደምር የግላችን ነው:: የምናከብረው ሌሊት ነው:: በበዓላችን የማይደመሩት ፖርቹጋሎች እንቅልፍ ላይ ይሆናሉ:: እናንተ ቱኋኖች ከአገራችን ውጡ፥ እያልን በምናበራው ችቦ ቤታቸውን እያቃጠልን በኛ ላይ የሚያደርጉትን ግፍና፥ በቅኝ ግዛት ለመቀጠል ያላቸውን ረዥም እቅድ ይህችን የመስቀል በዓል በመጠቀም ላንድና ለመጨረሻ ጊዜ መግታት አለብን" ብለው ያቀዱትን በየደብሩ ለሚኖረው አካለ መጠን ለደረሰ ወንድ ልጅ ሁሉ ትድረስ ብለው ካህናቱ በቆራጥ መንፈስ አሰራጩት:: መልእክቱ የደረሳቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉም በመተባበርም ተግባራዊ አድርገውት አደሩ:: ካህናቱ ለወገን መጎሳቆል ተቆርቁረው ወስነው ባንድ ልብ እንሙት ብለው መነሳታቸው ያስደነቀው አንድ ሰው፥፥
"
እንዲህ በየደብሩ መላክ ነበር እንጂ
ካህን ሞተ ተብሎ አይነግሩም አዋጂ " ብሎ እንደገጠመ ይነገራል:: በነገራችን ላይ የኔታ አንዳርጌ ከላይ የጠቀስኩትን ታሪክ መሠረት በማድረግ በደመራ ሌሊት መወድስ ዘርፈውበት፥ እኛ ተማሪዎችም የሳቸውን ቅኔ እንደ ምሳሌ (ሞዴል) በመጠቀም የሳምንቱ የቅኔ መቁጠሪያችን ሆኖ መሰንበቱን አስታውሳለሁ:: 6
ኢትዮጵያውያን ከወገኖቻቸው አንድ ሰው ሳይጎዳ በመስቀሉ የችቦ እሳት አገራቸውንና ነጻነታቸውን ከፖርቱጋሎች ነጥቀው መለሱ:: ይህንም ለማስታወስ በደመራው በዓል "ትኋን ውጪ ቁንጫ ግቢ" ይባላል:: ኢትዮጵያውያን የፖርቹጋሉን መሪና የሮማውን ፓፓ ሸፍጥ አከርካሪውን የሰበሩበት ጥበብና ጀግንነት ፖርቹጋሎችንና ሮማውያን አሳፍሯል፥ አስቆጥቷል፥ ቂምም አትርፏል:: የትኋኗ አለማምለጥና ስትደፈጠጥም የምታስከትለው ክርፋት፥ ለኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ቅኔ ሰምና ወርቅ ሆኗል:: የማይለቅ ክርፋት የተባለው የትኋኗ ሽታ፥ በዚያን ጊዜ የደረሰባቸው ጉዳት፥ በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ልብ የቀረጸው ቂምና በቀል ነው ይላሉ:: "ጥንተ አብሶ" ይሉሐል ይህ ነው:: እያንዳንዱ ዜጋ ለወገንና ለጋራ ጥቅም ለሰባዊ ልዕልና ቅድሚያ በመስጠት የሚቀርብለትን ጊዜያዊ ጥቅም ንቆና ተጸይፎ በመተው ፍላጎቱን ካልገታ፥ አገር እየበደለ ሕዝቡን እያስለቀሰ ለመኖር ከውጭም ይምጣ ከውስጥም ይፈጠር በጥቃቅን ነገር በሹመት በገንዘብ መፈተኑ አይቀርም:: ይህ አይነት ፈተና ሁለት ሰዎች ብቻ በሚኖሩባት ገነት ከተከሰተ፥ በየተለያዩ የጎሳ ስሞችና ቋንቋዎች በምንኖርበት ባሁኑ ወቅትማ፥ እንደ ፖርቹጋሎች ለሚከፋፍል ለሚለያይ መንግሥት፤ ድኅረ ገጾችን፥ የመገናኛ መስመሮችን እያፈነ በጨለማ ዘግቶና አፍኖ ለመግዛት ምን ያህል ምቹ እንደሚሆንለት በአጼ ገላውዴወስ ዘመን ከነበሩት ወገኖቻችን የበለጠ መገንዘብ ይኖርብናል:: ኢትዮጵያውያን ካህናት ከፖርቹጋሎች ጋራ ወግነው ያስቸግሩ ስለነበሩ ወገኖች "ስማዕ እግዚኦ እለ ኪያከ ይስእሉ:: እግዚኦ እለ ዘንስእለከ ኢንሰተት አላ በስክየት ዲበ ጸላኢነ ነሀሉ:: ሀበነ ዘወትር ጸሎተነ እምኂጠተ ጸላኢ ንትአቀብ:: . . . . ተወከፍ ሲሩያነ በምሕረትከ አንጽሕ አብዳነ አጥብብ ወኅጉላነ"(ዘነግሕ):: በማለት ጸለዩ:: ማለትም፥ "አቤቱ በቅን ሕሊና የሚለምኑህ ስማ፥ የምንለምንህ እኛም ተሸንፈን እንዳንወድቅ እርዳን:: በወቀሳም በከሰሳም የምንከሰስበት እንዳይኖር ብንከሰስም እንድንረታ እርዳን:: ከጣላት ሸፍጥና ማታለል ነቅተን እንድንጸልይ እርዳን:: በስሕተታቸው ተጸጽተው የተመለሱትን ወገኖች ተቀበላቸው:: አርቆ የማሰብ ችሎታ ያጠራቸውንም ወገኖች ሕሊናቸውን ብሩህ አርግላቸው:: ወደ ጠላት ጎራ በመግባት ከመካከላችን የጠፉትንም ወገኖች ንቃቱንና ማስተዋሉን ስጣቸው" በሚለው ላይ አስምረውበታል:: ሊቃውንቱ ሰዓቱንና ወቅቱን ከታሪኩ ጋራ በማገናኘትም "መዝገበ ጽልመት እንተ ብነ በሥምረተ አቡከ አብራህከ ለነ ዘአውጻእከነ እማዕምቅ ውስተ ብርሃን:: ወወሀብከነ ሕይወተ እሞት:: ወጸጎከነ እምግብርናት ግዕዛነ:: ዘበመስቀልከ አቅረብከነ አምላክ:: አላ ብርሃነ ሀበነ"(መንፈቀ ሌሊት):: እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ:: ማለትም፥ "በጨለማ ውስጥ ለነበርን ለኛ ባባትህ በጎ ፈቃድ የደኅንነት ብርሃን አበራሕልን:: ከጨለማ አዘቅት አውጥተህ ወደ ብርሃን አፋፍ አወጣህን:: ከሞት አድነህ ሕይወትን ሰጠኸን:: ከመገዛትም ነጻ አወጠሀን:: በመሰቀልህ ያቀረብከን አምላክ ሆይ ብርሃንህን ስጠን":: በግራኝ መሐመድ የተጎዳውና የተጎሳቆለው ወገን፥ እንደገና ከፖርቹጋሎች ጋራ ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዳይሞትባቸው፥ "ዕቀብ ኩልነ ዘእንበለ ጻሕብ ወዘእንበለ ተመውዖ ወዘእንበለ ማዕቀፍ:: አድኅን አእጋሪነ እምዳህጽ ወአዕይንቲነ እምአንብእ ወነፍስተነ እሞተ ኃጢአት ወደምረነ ምስለ እለ ድኅኑ ብከ በጸሎተ ኩሎሙ እለ እምዓለም አሥመሩከ" የሚለውን ንባብ ያቀፈውን ሊጦን ጸለዩ:: (ሊጦን ዘሠርክ) ይህም ማለት፥ "አምላካችን ሆይ! በፍልሚያ ውስጥ ገብተን ስንዋጋ ተደናቅፈን ከመሸነፍ ጠብቀን:: ጠላቶቻችንን ስናሳድድ አንዳልጦን ከመውደቅ አድነን:: እንባ ከማፍሰስም ተዋርዶ ከመሞት አድነን:: ባንተ ታምነው ባንተ መከላከል ከሚድኑት ጋራ ደምረን" 7
ከዚያ በኋላ ከነቢዩ ዳውት ድርሰት (መዝ ፶፱፡፩-) ላይ ያለውን "
ቀሰፍከነሂ ወተሣሀልከነ
አድለቅለቃ ለምድር ወሆካ
ወፈወስካ ቁስላ እስመ አንቀልቀለት
አርአይኮሙ ዕጹባተ ለሕዝብከ
ወአስተይከነ ወይነ መደንግጸ
እግዚኦ ገደፍከነ ወነሠትከነ፥ " የሚለውን በክስተት መልክ ከተቀባበሉ በኋላ ከዚያ ቀጥሎ ያለው ንባብ
"
ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት
ወይድኀኑ ፍቁራኒከ
ወወሐብኮመ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ " የሚለውን ዲያቆኑ መስቀሉን ይዞ ከፍ ባለ ድምጽ አሰምቶ እንዲያዜም አደረጉ:: ይህም ማለት የችቦውን ዘዴ እንደመከላክያ ጋሻ አርገን እንድንጠቀምበት አስተማርከን:: ከጣላቶቻችንም ጋራ ፊት ለፊት ተጋጥመን ጠላት ከሚወረወርብን ጦር እናመልጥ ዘንድ የችቦውን መብራትና የምንጠቀምበት ሰአት ገለጽክልን የሚለውን መንፈስ የያዘ ነው:: የታሪኩ መነሻ በተብራራ ሁኔታ ለሕዝብ አልተነገረም እንጅ ይህ እስከ ዚህ የገለጽኩት ሁሉ በያመቱ በየደመራው በዓል ላይ አመታዊ ሥርዓት ሆኖ ይካሄዳል:: አምና ለዘመነ ሉቃስ "የተወደደችውን የጌታን ዓመት እንስበክ" በሚል ርዕስ ባቀረብኳት ጦማር (http://www.medhanialemeotcks.org/pdf/ethiopian_new_year_zemene_lukas.pdf) ስለ መንፈሳዊው አባት ሚና ስገልጽ፥ "አምላኩን ወዶ ለማስወደድ፥ ሃይማኖቱን አክብሮ ለማስከበር፡ በህዝባዊ ፍቅር ልቡ የነደደ፥ ቅዱስ ተብሎ የተሰየመ አባት፡ የምሕረት ምንጭ በሆነው አምላክ ስም፡ በሚያቀርበው የምሥራች ቃል:: ዘመኑን ባርኮ ለሥጋውያን መሪዎች አውደ ምህረቱ ይለቅ ነበር" እንዳልኩት፥ በደመራው በዓልም፥ የሚቃጠልበት የእሳት ምንጭ በካህኑ እጅ ያለው ችቦ ነው:: መጀመሪያ "ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ" ብሎ የሚጸልየው ያካባቢው ካህን የመጀመሪያዋን እሳት በእጁ ባለው ችቦ ላይ ይጭራታል:: ካህኑ ካቃጣላት ችቦ ላይ የአገሪቱ ሥጋዊ መሪ በራሱ ችቦ እሳቱን እንዲለኩስ ይፈቅድለታል:: የአገሪቱ መሪም እሳቱን በካህኑ እጅ ላይ ካለው ችቦ በችቦው ለኩሶ በደመራው ላይ መለኮሱን ይመራል:: በተዋረድ የተከበሩ የአገር ሽማግሌዎች ይቀጥላሉ:: ከዚያ ጎረምሳው፥ ኮበሌው ወጣቱ እሳቱን በችቦው እየተቀባበለ ወደ ደመራው እየወረወረ የጀግንነት ምልክቱን ብትር ከፍ አድርጎ ይዞ ሆ! እያለ ደመራውን ይዞራል:: ቁርጥ የሚባል ስም ተሰጥቶት ጥሬ ሥጋ መብላት የተጀመረውም በዚሁ ዘመን ነው:: በሌሎች ክፍላተ ሐገሮች የሚደረገው ተመሳሳይ መሆኑንና አለመሆኑን ባላውቅም፥ ባደግኩበት አካባቢ ቁርጥ ሥጋ ወንዶች ብቻ ሲበሉ እንዳየሁ ሁሉ፥ በደመራው በዓልም ዳቦት(ችቦ) አብርተው ከቤት የሚወጡት ወንዶች ብቻ ናቸው:: ወንዶች ብቻ የሆኑበትን አባቶች ሲናገሩ እንደሰማሁት፥ "ብርሃን ዘበ አማን ዘያበርህ ለኩሉ ሰብዕ" የተባለው በጨለማ ለነበረው ዓለም ያበራው፥ ያለ ወንድ ዘር ወንድ ሆኖ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው:: እመቤታችን "እመ ብርሃን (የብርሃን እና) ምሥራቅ (መውጫ)" እንጅ ብርሃን አይደለችም:: ይሁን እንጅ በማሕጸኗ አድሮ ወልዳው በሄደችበት ሁሉ ታቅፋ ያቋረጠችውን ዘመን በደመራው በዓል ይታወሳል:: በደመራው በዓል አጋጣሚ ሆኖ የቤቱ ባለቤት በሞት ወይም በሆነ ነገር በቤት ውስጥ ከሌለ፥ በእናቱ እቅፍ ያለ ወንድ ሕጻን በእናቱ እጅ ችቦውን (ዳቦቱን) እያበራ ከቤት ይወጣል:: ሴት ብቻ ከሚኖሩበት ቤትም፥ ከጎረቤት ወንዶች ልጆች አንዱ አብርቶ እንዲወጣ የሚደረገውም ይህን ለማስታወስ ነው:: 8
ከፖርቹጋሎች ጋራ በተፈጠረው ታሪካዊ ክስተት ላይ፥ በዚያች ሌሊት ችቦ እያበራ ወጥቶ ፖርቱጋሎችን የደመሰሱት ወንዶች ብቻ ስለሆኑ፥ የመታሰቢያነቱ ገጽታ ተለጥጦ መልኩን እንዳይለውጥ ሴቶች ችቦ አብርተው ከመውጣት ተቆጥበዋል:: ይህ በእሌኒ የተጀመረ በዓል፥ በኢትዮጵያውያን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሐረግ እየዘመተ በቅኝ ገዥዎች ሳይቆራረጥ በደማችን በምግባችን በስሜታችን ሳይቀር ተቀርጾ ለረዥም ዘመን በመቀጠሉ፥ የታሪክና የባሕላችንን ምዕራፍ እያሰፋ እስከኛ ዘመን ደርሷል:: ትውልድ በውጭም ሆነ ባገር በቀል ወራሪዎች ተወሮ፥ ተበታትኖና ቋንቋውን ታሪኩንና ባሕሉን እንዲረሳው ካልተደረገ፥ ታሪኩ በግልጽ እየተነገረው በያመቱ የደመራው ሥርዓት ከቀጠለ፥ እየተፈራረቀ የሚገጥመውን ሁሉ እያባዛና እየደመረ ባህሉንና ታሪኩ እየሰፋ ይሄዳል:: ይህ የደመራው በዓል ይዘቱን ሳይለቅ፥ ከታሪካችን ጋራ ያለው ጥምረት ለትውልዱ በግልጽ እየተነገረ እንዲቀጥል፥ ጠንካራ መመሪያ የመስጠቱ ኃላፊነት የመንፈሳዊና የፖለቲካ መሪዎች ቢሆንም፥ ከመንግሥት ይልቅ በላቀ ሁኔታ ኃላፊነቱ የሚመለከታቸው ወላጆችንና፥ ሽማጎሌዎችን ነው:: 

የመጀመሪያዋን የደመራውን እሳት የሚለኩሳት ማነው?
 "ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ" የሚለውን ሊጦን ጸልዮ ባርኮ የደመራዋን እሳት ለአገሪቱ መሪ የሚያቀብላት ካህን ማነው? ከካህኑ ተቀብሎስ የደመራውን እሳት በማቃጠል የሚመራው የአገሪቱ መሪስ የትኛው ነው? ሥርዓቱን ተከትለው በእጃቸው ያለውን የደመራ ችቦ እያቀጣጠሉ ወደ ደመራው መጨመር የሚችሉትስ ሽማግሌዎች የትኞቹ ናቸው? መተርጉማን አባቶች በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፮ ላይ "ስድስቱ መሳብክት እለ እብን በዘ ያጥህሩ ቦቶን" ተብሎ በሚነበበው አረፍተ ነገር፥ ታሪክን ሃይማኖትንና ባህልን ይገልጹበታል:: ክርስቶስ የቃናውን ውሐ ወደ ወይን የለወጠባቸው ጋኖች የተሠሩት "ዕብነ አልማስ" በሚባል ማዕድን ከቀለጠ ድጋይ ነው:: ይህ የከበረ ማዕድን ድንጋዩን ሰብስበው ሲያቀርቡለት ያቀልጠዋል:: በሱም ድንጋዩን እያነጡጡ፥ እየላጉ፥ በፈለጉት ቅርጽ ይሠሩታል:: ሰውም ከምንቼትነትና፥ ከቶፋነት እየተላቀቀ ወደ ጋንነት ለመድረስ ማንጠጫ፥ መላጊያና መቅረጫ "ዕብነ አልማስ" አለው:: ለተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የመጀመሪያውና ቀዳሚው "ዕብነ አልማስ"፥ መለኮቱን ከሥጋችን የደመረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ተከታዮቹም ቅዱስ አትናቴዎስ "ቅትራተ ሐጺን ዘኢያንቀለቅል" ብሎ የገለጻቸው ሕዝቡ በእምነታቸው በሞራላቸው አምኖ የሚሰማቸው ካህናት ናቸው:: ቀጥሎም "በሃይማኖት በታሪክና ባባሕል ምስክርነታቸው በእውቀትና በሞራላቸው በቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተሰለፉ ያገር ሽማግሌዎች ናቸው" ይላሉ ሊቃውንት አበው:: ሲያብራሩትም፥ ሕጻን ሃይማኖት ታሪክና ባህል ይዞ አውቆና ተምሮ ከናቱ ማህጸን አይወጣም:: ክርስቶስ እንዳለውም በሥጋ አልሚ ምግብ በዳቦ ብቻ ሰው አያድግም:: Fast Food Nation እንዳይሆን ማለት ነው:: ትውልድ ሃይማኖቱን፥ ታሪኩንና ባህሉን ለይተው በተረዱ ባባትና እናት፥ በሐገር ሽማግሌዎችና በመንፈሳዊውያን መሪዎች እየተነጠጠ፥ እየተላገና እየተቀረጸ ማደግ አለበት:: ከካህናትና ከፖለቲካ መሪዎች በመቀጠለ የነ አብርሃምን የነ ይስሐቅንና የነ ያዕቆብን ምሳሌ የያዙ ዕብነ አልማሶች የሚባሉት ያገር ሽማግሌዎች ነበሩ:: በፖርቹጋሎች ምክንያት ምዕራፉን አስፍቶ ከኛ ዘንድ የደረሰው 9
የመስቀሉ በዓል፥ እምነትና ሞራል ተንተርሰው፥ እውነትን እየፈለጉ ያለፉትን ከእሌኒ በፊት የነበሩትንና በዓለም ያሉትን ሁሉ አርበኞች ዕብነ አልማሶች እያልን እንድናስታውሳቸው አድርጎናል:: ለምሳሌ "ተዘከሮሙ እግዚኦ ለኩሎሙ አበዊነ ወአኀዊነ ወአኃቲነ እለ ኖሙ ወአዕረፉ በርትዕት ሃይማኖት ወደምር ነፍሳቲሆሙ ውስተ ሕጽነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ" ማለትም፥ "ሳይወላውሉ በቀናች እምነት ጸንተው ለወገናቸው ለነጻነታቸው መስዋዕት እየከፈሉ ያለፉትን አባቶቻችንን፥ ወንድሞቻችንን እናቶቻችንና እኅቶቻችንን በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ ሕጽን አንድ ላይ ሰብስብልን" እያልን በቅዳሴያችን እንጸልያለን:: እነ አብርሃምን ዕብነ አልማሶች የምንልበትን ምክንያት፥ በኢትዮጵያ መንበር ላይ ቆሞ የሚቀድስ ካህን ሁሉ ክህነቱን ከመቀበሉ በፊት ከሊቃውንት ሊማረውና ጠልቆ ሊረዳው ይገባዋል:: "በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ" ተብሎ ለአብርሃም ወንጌል የተሰበከለት፥ "ወበጽሖሙ ሌሊተ ምስለ ደቂቁ ወቀተሎሙ ወዴገኖሙ እስከ ባኮር እንተ እምጸጋማ ለደማስቆ"( ዘፍ ፲፬፡ ፲፭) ማለትም፥ "አብርሃም አርበኞቹን አሰልፎ በእምነት ተሰልፎ ድልን ከተጎናጸፈ በኋላ ነው:: እነ ያዕቆብንም ቅዳሴው የሚያነሳሳቸው "ወለዛቲ ምድር እንተ ወሀብኩ ለአብርሃም ወለይስሐቅ ለከ እሁበከ ወለዘርእከ እምድኅሬከ" (ዘፍ ፴፭፡፲፪-፲፬):: ከሚለው ባሻገር "ወአቀመ ያዕቆብ ሐውልተ ውስተ ውእቱ ብሔር ኀበ ተናገሮ"(፴፭፡፲፬) ማለትም፥ "ያዕቆብ እግዚአብሔርን ባናገረበት ቦታ ላይ የድንጋይ ሐውልት አቆመ" የሚለውን ገጸ ንባብ መሠረት በማድረግ ነው:: ያዕቆብ እግዚአብሔርን ባናገረበት ቦታ ሐውልት ያቆመበት ምክንያት፥ ቦታውን ቤተ-ኤል (የእግዚአብሔር ቤት) ለማለት እንጅ፥ እንደ ዘመናችን ፓትርያርክ፥ እንደ ማክዶናል ፋስት ፉድ እየተገላበጡ ትላንት ሌላ ዛሬ ሌላ ከሚናገሩትና ከሚያደርጉት ጋራ በመገለባበጥ የራስን ቅርጽና ዝና በህዝቡ ልቡና ለማስረጽ አይደለም:: ያዕቆብ የተከለው ድንጋይ ያነበበውን ሁሉ እስከኛ ዘመን ድረስ እየናጠጠና እየላገ ያለና የሚቀጥል ነው:: በዚህ ታሪካዊ ባሕርያቸው እነ ያዕቆብን መጽሐፈ ቅዳሴያችን ይጠቃቅሳቸዋል:: ቅዳሴያችን "ወለነኒ አድኅነነ እምኩሉ አበሳ ወመርገም ወእምኩሉ ጌጋይ ወእምኩሉ ክሕደት ወእምኩሉ መሐላ በሐሰት ወእምኩሉ ግዘት ወእምተደምሮ በዕልወት ወርኩስ ምስለ ዓላውያን ወአረማውያን" በማለት ከከሐዲዎች ከሸፍጠኞችና ከአስመሳዮች ጋራ ከመደመር እራሳችንን እንድንጠብቅም በጽኑዕ ያሳስበናል:: ይሁን እንጅ ያገር ሽማግሌዎች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እራሳቸው እየተነጠጡ ካላደጉ፥ የሰውነታቸው እርጅና የጸጉራቸው መሸበት ብቻ የአገር ዕብነ አልማስ ሊያደርጋቸው አይችልም:: ይልቁንም በእርጅናቸውና በሽበታቸው ጎጠኝነትን፣መንደርተኛነትንና፣ ሸፍጠኛነትን በመስበክ የሚከተላቸውን ትውልድ ፈጣን ምግብ (Fast Food Nation) የሚያደርጉ የሕብረተሰብ ነቀርሳዎች ስለሆኑ፥ ትውልዱ የሚያደርጉትንና የሚናገሩትን በጥንቃቄ ሊያጤነው ይገባል:: "ፍልሰታ" በሚል ርዕስ ያቀረብኳት ጦማር ይመልከቱ::(http://www.medhanialemeotcks.org/pdf/Filseta%20Final.pdf) ጊዜ ሲበላሽ የሀገር ሽማግሌዎች ከደመራ ሆታ ባሻገር የደመራውን ምሥጢር ለመረዳት የተሳናቸው ሕጻናት ይሆናሉ:: ይህን ሳያስተውሉ ስለደመራው በዓል የሚሰብኩ፤ የደመራውን ችቦ ባርከው እሳቱን የሚለኩሱ ካህናትም፥ ከሆታው ባሻገር ያለውን የደመራውን ምሥጢር ከሊቃውንት አበው ሰምተውት ካላወቁ፥ ከሕጻነ አዕምሮ ገና ያልተላቀቁ ይሆናሉ:: ለደመራው ምሥጢር ተቃራኒ የሆኑትን ቅነሳንና ከፈላን ለሚያርምዱ አጫፋሪ በመሆንም ሆባዮች ይሆናሉ:: (በግዕዝ ሆባይ ማለት ዝንጀሮ ማለት ነው) ችቦ አብርቶ ትኋንን ውጪ፥ ቁንጫን ግቢ ለማለት መጀመሪያ በደመራው እንጨት ውስጥ መወከልን ይጠይቃል:: ቀጥሎም የሚያበራው ችቦና የሚያቃጥለው የደመራው እሳት፥ ተቃራኒ በመሆን ለመክፈልና ለመቀነስ የመጣውን የፖርቱጋሎች ስሜት የተሸከመውን የሚያቃጥል፥ ከሰልና አመድ የሚያደር፥ በእምነታቸው 10
በሞራላቸው ጸንተው ለቆሙት ኢትዮጵያውያ ግን የሚያበራ፥ የሚያሞቅና የሚያደምቅ እሳት መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል:: ከችቦውና ከደመራው ጋራ አብራ የገባች በአጥርና በዛፍ ስር የምትበቅል በአማርኛ አሽክት
"
እዚያው ጤሶ ጤሶ እዚያው ነዶ ይለቅ
ይባላል(ትድምርት ዘእንበለ ፍልጠት) በትግርኛ ጸጎጎት የምትባል ጥልቅ ትርጉም ያላት ሐረግ አለች:: ይሕች ሐረግ መረሳት የሌለባት በዚያ ዘመን ትልቅ ሚና የተጫወተች ናት:: ፓርቹጋሎች አንድነታችንን አፍርሰው ሊለያዩን አይችሉም በሚል ጽኑዕ ውሳኔ የተስስማማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት እንደ ልዩ መግባቢያ ሆና አገልግላለች:: እኔ ካገር ቤት የመጨረሻውን ደመራ አክብሬ ወደ ደብረ ሊባኖስ እስከሄድኩበት ዘመን ድረስ ልጆች ሆነነ በራሳችን እናደርጋት ነበር:: እናቶችና ሽማግሌዎች ደግሞ ለቁርጥማት መድኃኒትነት አላት እያሉ በደመራው አመድ ላይ ጎዝጉዘው ይቆሙባት ነበር:: የደመራው እንጨት እርጥብና ደረቅ ነው:: "በርጡብ እጽ ለእመ ኮነ ከመዝ እፎ በይቡስ" እንዳለው ክርስቶስ፥ ርጥቡ እንጨት ባሕርዩን፥ እሱነቱን ያልቀየረ፥ በቀላሉ ለእሳት ያልተጋለጠ ወገን ነው:: ቢጎዳም ለወገን ነው:: የሚወክለው ቁርጠኛውን ዜጋ ነው:: ደረቁ እንጨት ባሕርዩን የቀየረውን፥ እራሱን ከወገኑና ከታሪኩ አግልሎ አድር ባይና ወላዋይ የሆነውን፥ በአስመሳይና በሸፍጠኛ ባሕርዩ ከፖርቹጋሎች ጋራ የወገነውን ዜጋ ይወክላል:: አጓጉረውና እርጥቡን ከደረቅ፥ " የሚለው ሽለላ (ቅራርቶ) የመነጨውም ከዚህ ነው :: የደመራው በዓል ይህን አስደናቂ ምሥጢር ያዘለ ከሆነ፥ "ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ" ብሎ ይህን ምሥጢር በቃሉ ያስተማረ፥ በተግባሩ ያከናወነ የደመራዋን እሳት ችቦ የሚባርካት በዘመናችን የትኛው ካህን ነው? ከካህኑ ለኩሶ ደመራውን በመጀመሪያ የሚያቀጣጥለው መሪስ የትኛው ነው? ወጣቱንስ በየመንደሩና በየቤቱ በዚህ ኢትዮጵያዊ እምነት ታሪክና ባሕል የሚቀርጽ፥ የሚልግና የሚያስተካከል የትኘው ያገር ሽማግሌና የቤተ ሰብ ሐላፊ ነው? ዛሬ ከመቸውም ዘመን በከፋ ሁኔታ የተዋሕዶውን ሃይማኖት አፍርሰው፥ በፖርቹጋላዊ ከፈፋይ መንፈስ ለመተካት የሚታገሉ አስመሳዮች ደፍረው ወደ ቤተ መቅደሳችን የገቡበት ዘመን አይደለምን? ከሃይማኖቱ፥ ከታሪኩና ከባሕሉ ይልቅ ለመንደርተኝነት ቅድሚያ በመስጠት ከሀዲዎች መሆናቸውን እያወቁ ድጋፍ ለመስጠት ሽንጣቸውን ገትረው የተነሱ ሽማግሌዎች የተከሰቱበት ዘመን አይደለምን? በአገሩቱ ላይ የሚካሄደውንስ የፖለቲካ ዘይቤ ስንመለከተው በአድዋ ላይ ሥር ሰዶ የነበረው "ዓኾ ዓኾኋይ ሆይ ሆያዬ ንጎናይ በርሆ" በማለት ኢትዮጵያውያን ያባረሩት ፖርቹጋላዊ የፖለቲካ መርሆ፥ ዛሬ መልኩን ለውጦ በነ አቶ መመለሰ አማካይነት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረበት ዘምን አይደለምን? እነዚህ ካላይ በጥያቄ ያቀረብኳቸው መጠይቆች፥ እውነትም የወቅቱ መጠይቆች ናቸው ብለን ተስማምተን ከተቀበልናቸው:: የቀደሙ ሊቃውንት አበው በመጽሐፈ መሳፍንት ምዕ ፱ ከቁጥር ፳ ላይ የሰፈረውን "ለትጻዕ እሳት እምቤተ አቤሜሌክ፥ ከመ ትብላእ አብያተ ሴኬም፡ ወትሜሎም:: ወለእመ አኮ እሳት ትጻእ እምቤተ ሴኬም ወትሜሎም ከመ ትብላዕ ቤተ አቤሜሌክ" የሚለውን ተመርኩዘው፥ ማለትም "እኛ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራችን የተደጋገመ ግፍ እየተፈጸመብን ነው:: ይህች ከኢትዮጵያውያን ቤት እየተጫረች የምትወጣ የዘንድሮው መስቀሉ በዓል እሳት፥ በሸርና በሸፍጥ በእርዳታ ስም መጥተው የወረሩንን ፖርቱጋሎችን ትብላ፥ ለአገራችን ለነጻነታችን መታገላችን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ ረድኤቱን ከነፈገንም፥ ለዘላለም በፖርቱጋሎች ሥር ተጠቅተን ከመኖርና ለልጆቻችንም የተገዥነትን ውርስ ከማውረስ ይሕች ከየቤታችን የጫርናት እሳት እኛኑ ትብላን" ብለው ቆርጠው የተነሱበትን ያባቶችን መንፈስ ልንቃኘው ይገባናል:: 11
የጥንት ኢትዮጵያውን ችቦውን አንድ ላይ አስረው፥ እንጨቱን አንድ ላይ ደምረው ያቃጠሉት፥ ዛሬ እኛ እንደምናደርገው በጎሳ በቋንቋ፥ በሃይማኖት፥ ከውጭ ሠርሥሮ በገባ ሃይማኖትና በተለያዩ የፖለቲካ ትርጓሜ በመለያየት አልነበረም:: ደመራውን ችቦውን ትንሿን አሽክት እንኳ ሳይቀር ላንድነታቸው ምልክት በመጠቀም ነበር:: እግዚአብሔር "ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ" እያሉ የደመራውን እሳት የሚያበሩ ካህነት፥ "ትኋን ውጭ፡ ቁንጫ ግቢ" እያሉ የደመራውን ችቦ የሚያበሩ ሽማግሌዎች፥ የካህኑንና የሽማግሌዎችን ምኞት በሆታ የሚያስተጋባ ትውልድ እንዲፈጠር እንጸልይ:: ለዚህ ዓመት የደመራ በዓል ያደረሰን አምላክ፥ ለከርሞውም በሰላምና በጤና ጠብቆ ያድረሰን:: ለሌሎች ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ጦማሮች የሚከተለዉን ድህረhttp://www.medhanialemeotcks.org/ -ገጽ ይመልከቱ::
page 12

Wednesday, September 7, 2011

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት በግፍ አደጋ የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት ሕክምና በአሜሪክን አገር እንድታገኝ ጠየቀ።

መልካም ኢድ ለእስልምና ተከታዩ ውገናችን ሁሉ።


አጭር ዜና።

በሊቢያ በፈላ ውሃ የተቃጠለችውን ኢትዮጵያዊት አስመልክቶ የሕክምና እርዳታ ከተለያየ አቅጣጫ እንዲደረግላትና ከተቻለም ወደ አሜሪካን ዳላስ ቴክሳስ መጥታ ሕክምና የምታገኝበትን መንገድ ጭምር እርዳታ አድራጊ ሆስፒታሎችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት እያነጋገረና እያስተባበረ ስንብትዋል።  ከአዲሱም የሊቢያ ጊዜአዊ መንግስትና ከሃኪሙዋም  ጋር ግንኙነት ፈጥሮአል። የአሜሪካን መንግስት ቪዛ እንዲሰጣትም ሃሳብ የስዲቱ መንግስት አቅርብዋል፡ እያመቻቸላትም ይገኛል።

በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምንወደው ማሳሰቢያ በስማዋ ለሕክምናም ይሁን ለሌላ ወጭ ብለው ገንዘብ ለሚጠይቁ: ሕክምና እንጂ ገንዘብ አሁን አያስፈልጋትም።

አየለ ጉተማ
ከኢትዮጵያ የስዴት መንግስት ሕዝብ ግንኙነት
አትላንታ ጆርጂያ።

Friday, August 19, 2011

የቀድሞ ስራዊት አባሎች የሰራዊቱ እፍረቶች፡ ተፈራ ወርቅ አሰፋና ዮናስ ሊበን የተባሉት ለአመታት ሲክዱትና "ሃስት ነው የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን በዳላስ አላፈረስንም" እያሉ አሁን እውነት ነው ብለው በራሳቸው ላይ ሃሰተኞችን በቤተክርስቲያኑ እያመጣ በማናዘዝ በታወቀው በተአምረኛው የቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ መሰክረዋል።

እግዚአብሄርን የሚከተል በሱ የሚመራ የእውነት ተራራ ላይ ቆሞ ሃስተኞች በውሸት እስሳተጎሞራ ባህር ውስጥ ሲቀቀሉ ያያል!


ክርስቶስ፡ በሃሰት ወገን ላይ ለግል ጥቅም በኮሚቴ ተቀናጆ ከመፍረድና ከመመስከር ይሰውረን። ለተቸገረው ወገናችን ችግር ደራሽ እንጂ ከአፉ ነጥቀን ከመጉረስም ለልጆቻችንም ከማጉረስም ይጠብቀን። ለዘላለሙ አሜን!

 በቅዱስ ሚካኤል ደብር ጁላይ ሰላሳ አንድ አምላክ የሰራውን አንባቢያን ልብ በሉ። በተለይም የዳላስ ፎርት ውርዝ ንዋሪው ኢትዮጵያውያን ውነቱን ውሸት ነው ተብሎ ሲታለል የቆየው። በግላችሁ ለመፍረድ አትቸኩሉ የአምላክ ፍርድ የማይነቃነቅ የማይሞት ፍርድ ስለሆነ በውሸት የፈረዱባችሁና የመሰከሩባችሁ፡ አድማም የመቱባችሁና ለሃሰተኞችም ሻማ ያበሩ ሁሉ በአምላክ ፍርድ ቤት እነሱው በራሳቸው ላይ ፈርደው መስክርው ሲቀጣቸው ያሳያችሁዋልና። በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጋርልላድ/ዳላስ ጁላይ ሰላሳ አንድ የተሰማው ድምጽ የዮናስና የተፈራ ወርቅ ሲክዱት የኖሩት መረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶ አልነበረም በሚል፡ አዎን የመረዳጃ ማሕበሩ ከሁለትሺ ሰባት ኦገስት ሃያ ዘጠኝ እስከ መስከረም ሁለትሺ ስምንት ድረስ ፈርሶ  ነበር ብለው በራሳቸው ላይ በሊቁ የዱስ ሚካኤል ደብር እንዲመስከሩ ክርስቶስ የወሰነው ፍርድ ነው። የአምላክን ስራ እዩት በእውነት ተፈራ ውርቅና ግብረአብሮቹ ኮንፍልሊክት ኦፍ ኢንትረስት ከቤተክርስቲያናችን ሰዎች ይውጡልን ብለው የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ልክ እንደመረዳጃ ማህበራችን ሙርከኛ ለማድረግ ያላደረጉት ጥረት የለም። ከናካቴው ሚካኤልን ለማፈራረስ ምእመናኑንም ለመከፋፈል ምን ያላደረገው ነገር አለ ተፈራ ወርቅ? የአምላክን ደግነትና ፍርድ በብሎግ ትንተና ገለጻ ተወስቶ የሚታይ ሳይሆን፡  መጸሃፍ ቅዱስ አቅፎ ተንበርክኮ በመጸለይ የሚታይ ስለሆነ እግዚአብሄር እነዚህን ሕዝቡን ሲዋሹት የኖሩትን አጭበርባሪዎች በስሙ ነጋዴዎችን ደጋፊዎቻቸውን ምስክር አድርጎ በራሳቸው ላይ በሁለት ምላስ እንዲመሰክሩ ያደረጋቸው ሚስጢር አለው። ስለሆነም የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ለሁለት የድብቅ አላማ ሆነ ብለው ካፈረሱት በሁዋላ አምስት ጊዜ ደብዳቤ ሕብረተሰቡ ሳያውቅባቸው በትህትና ተጽፎ መረዳጃ ማሕበርንና የሬዲዮን ስርጭቱን ወይም ፕሮግርም እንዲሁም ዝግጅቱን እናድን ሲባሉ በስልክ እንክዋን መልስ ሳይሰጡ በማን አለብኝነት ልባቸው አብጦ በሃሰት "መረዳጃ ማሕበሩ አልፈረሰም ስማችንን በሃሰት ለማጥፋት ነው። የሪድዮን ፕሮግራሙን አዘጋችብን፡ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ልታፈርስ ነው፡ የጋራ መርድጃውንና እኛን ቴረሪስቶች ናቸው ብላ ፍርድ ቤት ከሰሰችን አድኑን አውግዝዋት፡ ወደ መረዳጃ ማሕበሩ ወደፊት መጥታ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዳትሰጥ ወስነናል በሃሰት ስማችንን የሐረርወርቅ ስላጠፋች፡ አግልለናታል ከመረዳጃው ሕዝቡም ያግልላት ብለን ፈርደናል ፍርዱም በምረዳጃው አስቀምጠናል" በሚል አርባ ሁለት ሰዎች ያሉበት የውሸት ምስክሮች ኮሚቴ በማቁዋቁውም በእኔ ላይ ኮሚቴ አቁዋቁመው ጠቅላላ ጉባኤ በሚል ያንን ሁሉ "ወይዘሮ የሐረርወርቅ በተገኙብት!!!!!!!" በሚል የፈረዱትን በሬዲዮ በመፈራረቅ ከማንበብና ከመፈረጅ በሃሰት ቅንብርብር፡ ለምን ልክ አሁን እንዳመኑት የመረዳጃው ማሕበር መፍረሱን መረጃውን ጭምር እንዳስረከብክውቸው ጥፋታችንን እናርማለን መረዳጃው መልሶ ያጣውን ሕጋዊነቱን በእስቴት ኦፍ ቴክሳስ መልሶ እንዲያገኝ እናደርጋለን ቢሉ ኖሮ? መልስ ለእኔ እንደመስጠት ለጻፍኩዋቸው ደብዳቤዎ ለምንስ በሬዲዮ ወጥተው ኮሚቲ ፈጥረው ኮሚኒቲውን ልታፈርስ ነው አሉ? ምናለበት ሕዝቡን ቢያከብሩት  ለጥቅሙ ለሰላሙ ለአንድንቱ ቢወዱት?  

Friday, August 5, 2011

ዘውገ ቃኘው የሚባለው በሕዝብ በቅርብ የተመረጡትን የሶሻል ክፍል ሃላፊ ለመደብደብ በመጋበዙ/ድንበሩን በማለፉ ሕግ ፊት ሊቀርብ ነው።

በመጀመሪያ እግዚአብሄር ይመሰግን ለሁሉም ቸርነቱ! አሜን!

 ዘውገ ቃኘው ከኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር የአማርኛ የሬዲዮ ስርጭት ከወጣ ወደ መረዳጃ ማሕበሩ መግባትና ችግር ለሚያጋጥማቸው ወገኖች መዋል ያለበት ገንዘብ ከእስፓንሰሮች የሚገኘው ገቢ ወደ እሱ ኪስ በቀጥታ መግባቱ ሊቆም ስለሆነ በቅርብ በቦርድ ውስጥ የተመረጡን እህት በለመደው የስም ማጥፋት ዘመቻው መሳሪያዎች የሆኑትን ሴቶች ይዞ በመጠቀም "የኢትዮጵያን ሕዝብ እስቱፕድ ብላ ስብሰባ ላይ ሰድባለች ከቦርድ ትውረድ" በሚል እያስተጋባና ፊርማም በማሰባሰብ ላይ እየተንቅሳቀሰ ነው።  በራሳቸው አይምሮ የሚመሩና ለሕብረተሰባችን ጥቅም በበጎ ፍቃድ የሚያገለግሉትን እህቶቻችንን ሁሉ ጥቅሙ ከተነካ ሴቶች ላይ የማይለጥፈው አጸያፊ ስም የለም። ለዚህም በተለመደው የስም ማጥፋት ዘመቻው በራሪ ወረቀቶች በመበተንና ግለሰቦችን ለማጥቃ ግለሰቦችን ለስድብ በማዘጋጀት እሱን እያሞገሱ ለሕብረተሰባችን ችግሩን ቀራፊዎችን ግን እንዲሰድቡለት በሬዲዮን በማድረግም ትልቅ ታዋቂነትን አግኝትዋል። የሬዲዮ ስርጭቱ በሶቻል እሬዲዮ ጣብያ ከግል ጥቅም ነጻ ላይ በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ እየተክፈለ በሕዝብ ስም የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ለዘውገና ለግልጥቅም ተጋሪዎቹ እንጂ ሕብረተሰቡ እስከዛሬ ሊጠቀምበት በሚገባ አልቻለም። አሁን ሬድዮን ፕሮግርሙ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለማዋል አዲሱ ቦርድ እይሰራ በመሆኑ ዘውገና የጥቅም ተጋሪዎቹ ጭንቀት ላይ ናቸው።  የኝህ የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ በተለይ በችግር ላይ በስራ ማጣት የወገን አለኝታነት እረሃብ እያዛጋ ያለውን ስራ በማጣት ከእነ ልጆቹ እየተቸገረ ላለው ከሬዲዮ እስፓንስሮች የሚመጣውን ገንዘብ ጭምር እንዲሰጠው እንዲረዳበት እየሰሩ ያሉት ዘውገን አስጭንቆታል ስለዚህ ዋሽቶ ፊርማ በሴቶች አሰባስቦ እኝህ ሴት ሁለተኛ በጋራ መረዳጃው ገብተው ለሕብረተሰቡ ነጻ አልግሎት እንዳይሰጡ የሚል በመረዳጃ ማሕበሩ በተለመደው እንዲቀመጥ ለማድረግ እየተሽቀዳደመ ይገኛል ለሕዝብ የሚጠቅሙን ስዎች እርዳታቸውን እንዲያቆሙ ማድረግ የሚጎዳው ሕብረተሰቡን ብቻ ነው፡፡

እህታችን ክብርት ወይዘሮ ስነ ያሉት  በትክክል ከዚህ ቀጥሎ እንደተቀመጠው ነው " How dare you treat me this way as if I am stupid and don't know what Im doing"  ይህንን ያሉት ለዘውገ ሳይሆን አፍ እላፊ ለተናገርው የዘውገና የግብረአበሮቹ አክል ለሆነው ለአንዱ ሲሆን ወደ ፊት ስለዚህ ግለሰብም ሕዝብ ካላከበረ እስከዛሬ ስሙን እየለወጠ ባደረሰው ማንነቱን ግልጽ እናደርጋለን ለሕብረተሰባችን። 
ፊርማ ለዘወገና ለግበረአበሮቹ የምታሰባስቡ እህቶች በተለመደው ባልሰማችሁትና ጠይቃችሁ ባልተረዳችህት ስለሆነ ከመሳሪያነት ብትቆጠቡ ለራሳችሁም ለልጅቻችሁም ጥሩ አራያ ትሆናላችሁ። ተሳዳቡ በተባላችሁ ቁጥር በሬዲዮና በፊርማ የምታደርጉት ሕገ ወጥ መሆኑን እንድትረዱት ያስፈልጋል በሕግም ብትጠየቁ ዘውገና በትሩ ተፈራ ወርቅ አያድንዋችህም።

ሌላው ሃቅ ፊታቸው ላይ የተደቅነውና ሲያስፈራራቸው ፎቶግራፍ የተነሳው ተፈራ ወርቅ አሰፋ ነው። ተፈራ ወርቅ ባዲስ መልክ በደንብ ሕዝቡን ለመከፋፈል ታድሶ አዲስ አበባ ደርሶ የመጣ የትግሬ ነጻ አውጪ ተቅጣሪ ሲሆን ከዚህ በታች የምታዩት ፎቶግራፉ የተሰጠውን ስራ ከአድስ አበባ እስራ ላይ ሲያውል ነው ይሄውም ሕብረተሰቡን በማሳሳት አንድ የሚያደርገንን በቦታው ተገንቶ አቅጣጫ እያስለወጡ መከፋፈል። ተፈራ ወርቅ የዘውገ አለቃ አዲስ የተመረጠውን ሕዝባዊ ቦርድ ከመቀመጫው እየተነሳ የተሳደበው አልበቃ ብሎት ቦርዱ ጠረቤዛ ስር ሄዶ በመዳፈር ድንፋታውን አፉን ከፍቶ ሲያስተላልፍ የፈሩት ሰዎች ፎቶ እንዳንሱት እነሆ። ይሄ ግለሰብ ጋሻ ኢንሹራንስ በሚል ለመንግስት የሕዝብ ስም እየሰበሰበ በኒያላ ኢንሹራንስ ስር በተቀናጀው የዲያስፓራው መቆጣጠርያ የሕዝብ መረጃ አቀባይ ሲሆን የመረዳጃ ማሕበሩን ዌብ ሳይት የሕዝቡ ኢንፎርሜሽን የሚያገኝበትና የሚሰበስብበት በመሆኑ ለምን ፓስወርዱን ለወጣችሁ? እንዴትስ ለተሰበሰበው ሕዝብ ኢንፎርሜሽናችሁን ለመጠበቅ ሲባል አዲስ የተመረጥነው የመረዳጃው ማሕበር ቦርድ አባላት ግዴታ ፓስወርድ መለውጥ ነበረብን ትላላችሁ? በሚልና ሌላም ሌላም ቃል በመጠቀም ሲያስፍራራቸው የተነሳው ፎትቶራፍ ተመልከቱት። የዚህን ግለሰብና የበትሩ ገብረእግዚአብሄርን ጋሻ ኢንሹርራን ጽህፈት ክፍል ኪራይ ሲከፍል የኖረው የጋራ መረዳጃ ማበሩ ነው። 

ከሁዋላው ይልማ ዘርይሁንና ሌሎቹን ግብረአበሮቹን በደንብ ተመልከቱ። እነዚህ ናቸው ነገሩ ያልገባቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ ነእሩ እንጂ በኢትዮጵያ ቀን በአል አሳበው ቦርዱን ሕዝብ ሳይመጣ ተሰባስበው በድምጽ ብልጫ አውርደው ቦርዱን ሊቆጣጠሩ አስብው የመጡት ስላልሰራላቸው ተቃጥለው ፕላን ቢ አድርገው የመጡት በሕዝብ ለኢትዮጵያ ቀን በአል አዘጋጅነት የተመረጠውንና ብዙም ስራ ሰርቶ የጨረሰውን አስፈርሰው እራሳቸውን ሰላሳ ሶስት ሰዎች አድርገው በኩዴታ ወስደው የሄድት ከእነዚህም ውስጥ በትሩ ገብርእግዚአብሄር፡ ተፈራ ወርቅ አሰፋ አፉን ከፍቶ ከላይ የሚታየው፡ ይልማ ዘርይሁን፡ ብርሃን ዳኛቸው የተባለችው፡ ዘውገ ቃኘው ይገኙበታል። ዝግጅቱን በመቀማታቸው የሚጎዱት ሃምሳ ሰባት ልጆችና ወጣትች ከፓራማውንት መስከረም ላይ የሚሰራ ፊልም ላይ እድሉን በኢትዮጵያ ቀን ሰበብ ተመቻችቶ የነበረውንና ለተቸገሩት ኢትዮጵያውያን የተገኘውን እድል ሁሉ ሜዳላይ ወርውረው ለግል ጥቅማቸው አመታዊ ገቢያቸውን ከእስፓንሰሮች ጭምር የሚያገኙትን ቅድሚያ በመስጠት። እነዚህ ግለስቦች ማቦች መታገል ያለበት ሕብረተሰቡ መሆን ይኖርበታል።

Sunday, July 31, 2011

ትናንት እድሩ እንዳይቁዋቁዋም ወረቀት ሲበትኑ የነበሩት የመረዳጃና የሬዲዮን አዘጋጆች ከጥቅም ተካፋዮቻቸው ጋር፡ ዛሬ ደግሞ ከመረዳጃ ማሕበሩ ስለተመነጠሩ፡ የእድር ተቆርቁዋሪ በመምስለ እድሩን እነሱ በሚፈልጉት ካልሆነ ለማፍረስ እየተርዋርዋጡ ነው። እድሩን አድኑት! እድሩ መፈጠሩ ጥሩ ነው እንደውም ሃሳቡን ያመጡት ቀደም ብለው ቢጀምሩት ጥሩ ነበር ዘግይትዋል ።



አምላክ የአለም ፈጣሪ ለእንዚህ ጥለውት ለሚሄዱት ከንቱ አለም በውጪና በአገር ቤት የሚኖረውን ሕዝብ እየጠቆሙና መረጃውን በመሰብሰብ ደሞዝ የሚከፈላቸውን የሴጣን ቁራጮች ያንተን ስም በሃቅ እንዲጠሩ አድርጋቸው አሜን!
እድሩን በቁጥጥራቸው ስር እንዳለ ለመኖር ትናናት ወረቀት እየበተኑ አይቁዋቁዋም ያሉት እነተፈራ ወርቅ፡ በትሩ ግርማ ንጉሴን ዘውግ፡ ዛሬ ደግሞ ሊፈርስ ነው በሚል አዲስ የተቁዋቁዋመው ቦርድ እድርተኞች ጨምሮ አስፋፍቶ ሊሰራ ባለበት ወቅት እድርተኛውን ሊያፈርሱልህ ነው በሚል እያወናበዱት ይገኛሉ።
እድርተኞች እድሩን ከመፍረስ አድኑት። እናንተን እንደ መያዣ ይዘው እነበትሩና ተፈራወርቅ ዘውገ ወደ መረዳጃ ማሕበሩ ለመመለስና የለመዱትን ፍሮድ ለመቀጠል ነው ይሄ ሁሉ መርዋርዋጥ። ፍሮዱ ተሰርትዋል ያግልጽ ነው እነዚህ ሰዎች ሊያጠፉ እንጂ ሊያለሙ የመጡ ሆነው አያውቁም። ለምሳሌ ከጥቂቱ ሃምሳ አራት ሺ ዶላር የመረዳጃው፡ እድር ሳይቁዋቁውም የነበርው በሁልትሺ ሰባትና ስምንት ከእድሩ መቶሺ፡ ዌል ፋርጎስ በየጊዜው አስራ አምስትሺ፡ ከሴፍኮ አስራአምስትሺ በድጋሚ ከካትቶክ ቻሪቲ ወዘተ ፍሮድ አዎን ፍሮድ ተሰርተዋል ከእድሩም ከመረዳጃ ማሕበሩም በማጭበርብር። ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሰ የበሉ፡ ገንዘቡን ለዲኤፍ ደብልዩ ጠረቤዛ የከፈሉት ሳይቅር መመለስ አለባቸው የህዝብ ገንዘብ። እስቲ የትኛው ሰው ነው ፍሮድ አልሰሩም ብሎ የትኛው እድርተኛ ነው ፍሮድ አልስሩም ብሎ ሊያስረዳኝ የሚችል መቼ እሱስ አውቆት ሁላችንም ተጭበርብረናል ሕብረተሰቡ በሙሉ። 
ፍሮዱ እድርተኛው የፈጸመው ሳይሆን በመረዳጃ ማሕበሩ ስም የተፈጸመ ስለሆነ ያለፈውን ያሁኖቹ ለማረም እየሞከሩ ይመስለኛል። እነዚህን አሁን ቦርዱን የተረከቡትን ሕብረተሰቡ ወዶዋቸዋል አምኖባቸዋል ይተማመንባቸዋልም ነገር ግን እድርተኞችን ማስፈራሪያ አድርገው እነተፈራወርቅና በትሩ ከተቀመጠበት ድምጹን አጥፍቶ በእጁ ቀጥል አቁም አይነት ምልክት እየሰጠ በቦርዱ መሃል ሳይታወቅ በስህተት የገባውን ግለሰብ በመምራት የተለመደውን የሽሽግ የቦርዱ ሊቀመንበርነቱን ስራ ላይ ለማዋል ብዙ ሞክርዋል።
ዛሬ እሁድ ነው የእረፍት ቀኔ ነው ሆኖም የሕዝብ ጉዳይ ከራሴ የበለጠ አስቀድሜ የማየው በመሆኑ እንደተለመደው፡ ለጠየቃችሁኝ ጥያቄ እድሩ ፍሮድ ሰርትዋል ወይ ? እድሩስ በመረዳጃ ማሕበሩ ስር አብሮ ተጣምሮ ያለ አይደለም የሚል ባለፈው እሁድ በተደረገው ስብሰባ ላይ ገልጠሻል ወይ?
እንዴት ነው እድሩና መረዳጃው አብሮ አይደለም አልሽስ የተባለው? የሚል ጥያቅን የጨመሩ ጥያቂዎችና ሌሎቹም እንዳብራራላችሁ ጠይቃችሁኛል። አመሰግናለሁ ይሄ ትክክለኛ አቀራረብ ሲሆን ለአጭበርባሪዎች ፍሮድ ለሚሰሩትም ግለሰቦች እንዳይስፋፉና እንዳይንሰራሩ ሕዝብ እንዳይከፋፍሉ ስለሚያደረግ ይሄን አይነት ግልጽ ጥያቄ መለመድ ይኖርበታል በጣም አመሰግናለሁኝ ስለጠየቃችሁኝ ውነቱን ለመረዳት ከእኔ። ሁሉም ጠይቆ ቢረዳ ስለህብረተስቡ ጉዳይ ንቃት ይኖረን ንበር እንጂ መሳሪያ ተጎታች መጠቀሚያ አንሆንም ነበር።
ለዛሬ ልላችሁ የምችለው ተመሳሳይ ነገር ተፈረወርቅ፡ በትሩና ዘውገ ግብረአበሮቻቸው ግርማ ንጉሴ ለእናንተ እንዳሉት ሁሉ ላልደወሉልኝም ማለታቸው አይቀሬ ስለሆነ ሕዝቡን በማክበር ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ባጭሩ አቀርባለሁ ሰፋ አድረጌ ግን ሃቁን ከነማስረጃው አቀርባለሁኝ እንዳስፈላጊነቱ በቅርብ።
እነዚህ ግለሰቦች እንደሩ እንዲኖር በትክክሉ የማይፈልጉ ናቸው። ከአዲስ አበባም በሃምሳ ሁለት ገጽ የቀረበላቸው መመሪያ በዚህ መልክ በእየ ድርጅቱና ሕዝቡ በሚሰባሰብበት እየገቡ ሕዝብን መበታተን ስለሆነ እነ ዚህ ግለሰቦች ደሞዝ ከኤንባሲው የሚያገኙበትን ስራቸውን እየሰሩ ነው ያሉት ቁዋሚ ስራቸው ሕዝቡን በውጪ ያለውን የትግሬ ነጻ አውጪ የኢትዮጵያን ሕዝብ በክልል ከፋፋዩን አላማ ማስፈጸም ስለሆነ ይሄንንም ወደ ፊት በዚሁ ብሎግ በከፊል እየተደረገ ይወጣል ታዩታላችሁ ለማታውቁት ማለት ነው እንጂ ብዙ ወገን ያነበበው ነው። ጥሩ ምሳሌ በትሩ የመለስ መልክተኞች በመጡ ጊዜ ሆነ ብሎ እስሙም እንደሱው በስውር በድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱት ጭምር የተጫወቱትን ቲያትር አንዱ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። ግንቦት ሰባት በትሩ የገባውም ግንቦት ሰባት የሚለውን የማፈራረሻ ዘዴ ለማጥናት ነው ያለውን ክፍተት።
እድሩን እነዚህ  ግለሰቦች እንዳይቁዋቁዋም በድብቅ ስብሰባ እያደረጉ ስማቸውን ሳያስቀመጡ ወረቀት ሲበትኑና በየዋህ ሰዎች ነገሩ ባልገባቸው በጊዜው በእውነት የጋራ ማረዳጃ ማሕበሩን ለማዳንና በእድር እንዳይተካ ታሰቦ መስልዋቸውና ቀባሪ ለሌለው መረዳጃ ማሕበሩ መቅበሪያ እንዲሆን በማሰብ በግርማ ንጉሴ አማካኝነት ይሰራጭ የነበረውን አንዴ ኮሚኒቲ ፎር ሴል በሌላ ጊዜ ማር የተለወሰ መርዝ ወዘተ በሚል በኤርፓርት ሳይቀር በስብሰባ እያሳተፋቸው አሳምኖ በሰጣቸው መሰረት አምነው ተቀብለው በግልጽ ቤተክርስቲያንና ታክሲ ወይም ኤርፓርት ጭምር ሲበትኑ ነበር። እንደውም አቶ ንጉሴን እድሩ እንዲቁዋቁዋም በጣም ይጥሩ ከነበሩ ታክሲ ነጂዎች ጋር መጣላታቸው ግልጽ ነው። ይሄ  ሁሉም ያየው ሲሆን ለዚህም መሳሪያ ካደረግዋቸው መሃል በጣም ሰው ሲቸገር እሮጦ የሚደርሰውን አቶ ንጉሴ ጋረድንና ወይዘሮ ቲና ካሳይን መጥቀስ ይቻላል ለማለት ነው።
ሆኖም የሚበተነው ወረቀት ላይ ለሕብረተሰቡ ተቆርቁዋሪዎች በሚል ብቻ በማስቀመጣቸው ወይዘሮ ቲናም ሰዎችን ስለምትረዳን አቶ ንጉሴም በቤተክርስቲያኑም ቢሆን አገልጋይ በመሆኑ ም እመናኑ የግራማ ንጉሴና የዘውገ ፡ የአመሃ መልክት በሚገባ ሲተላለፍ እነሱ ቆመው ያዩ ነበር ለሕዝቡ ለመሰራጨቱ ግባቸው። ከናካቴው እነሱ እራሳቸው ጉዳዩን እንደማያውቁ ሲቀበሉም ነበር።
በሚስጥር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ሴንትራል ኤክስፕሬስና ሮያል ቲንሺ ጽህፈት ቤት ውስጥ  እኔም በስብሰባቸው ላይ ተገኝቼ ተንኮላቸውን አየሁት።
 አመሃ የተባለው የቦረድ አባል ማለትም እራሱን ዶክተር አመሃ ነኝ በሚል ዶክተር ሆኖ የማይስራ  አንዱ እድሩ እንዳይቁዋቁዋም አድፋጭ ህዝቡን ለመከፋፍል የመከፋፈያ የነገር ደማሚት ቀባሪዎች መሃል ሲሆን አገሬ ኢትዮጵያም ይሄንን ስለሚያውቅ ከዛም መረዳት ይቻላል። ሆኖም እድሩን ለእድሩ የተነሱት ሲያድኑት፡እኔ ደግሞ የመረዳጃ ማሕበሩንና የሬዲዮን ስርጭቱን ከመነጠቅና ወደ ግል ጥቅም ለአዲስ አበባው መንግስት መሳሪያ እንዳይሆን አድኛለሁ በጊዜው።  የእነሱ እኔን ሬዲዮን አዘጋጅ፡ ቴረሪስት ብላ የመረዳጃ ማሕበሩና እኛን ከሰሰችን የክስ ወረቀት ደርሶናል ድረሱልን ብሎ በውሸት መብረቅ መተርከክና የጋራ መረዳጃ ማህበሩን በእነሱ አነጋገር ኮሚኒቲውን ልታፈርስ ነው ብለው በቡዋረቁት ጉዳዩ የሞተ ወይም ለፍርድ ቤትም ጊዜው ያለፈበት ቢመስላቸውም፡ ሃቁ ሃቅ ስለሆነ በሆቴል ካንጋሩ ፍርድ ቤት ስብሰብ እኔን ለመጉዳት አርባ ሰዎች ኮሚቲ ብለው ፈጥረው ቢዋዥቁም ፍንክቺም አላልኩኝም። ለዚሁም ባለፈው እሁድ በጁላይ ሃያ አራት በመረዳጃ ማሕበሩ ጥሪ በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ተገኝቼ መረዳጃ ማሕበሩን ለሁለት የድብቅ አላማቸው አፍርሰውት እንደነበረና በሁለትሺ ሰባት እነዚህ በእኔ ላይ የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ያወረዱት ውርጂብኝና ፍረጃ ፡  መረዳጃ ማህበሩንና ሬዲዮኑን ልታዘጋ ያሉት ውሸት መሆኑን ገልጬ ሰነዱን መረዳጃው በኦገስት ሃያዘጠኝ ሁለትሺ ሰባት ፈርሶ መስከረም አስራ አምስት ቀን ሁለትሺ ስምንት ማለትም እኔላይ ያንን ሁሉ ወርጅብኝ ባወረዱና ፈረድንባት በጠቅላላ ጉባኤ ባሉ በዘጠንኛው ወር ወደው ሳይሆን ያሰቡትን አላማ እነሱም ይሁኑ የትግሬ ነጻ አውጪ ተፈጻሚ እንዳያደርጉት በማድረጌ ሳይወዱ በግድ ሪንስቴት ወይም መልሶ መረዳጃ ማሕበሩ ሕጋዊነቱና እንዲያገኝ በስቴት ኦፍ ቴክሳስ ያደረኩበትን በስብሰባው አዳራሽ በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለአዲሱ ቦርድ አባላት አስረክቤለሁ።
ፍሮድ ሰርቶ በመኖር የሚታወቁት ከእነ ደጋፊዎቻቸው ጭምር ባሉበት ሳስረክብ ጪጭ ከማለት ሌላ አንዲትም ቃል ያለመተንፈሳቸውን ከቦርዱና እራሳቸውን ሲክቡዋቸው ከነበሩት መስማት ይቻላል። የሬዲዮን ስርጭቱም እንዳላዘጋሁኝ ሽንጤን ገትሬ ተናግሬአለሁ። ተፍራወርቅንም የመረዳጃ ማሕብሩን ገንዘብ በፍሮድ እንደበላው ከእነ ግብረአበሮቹ ሕዝብ ፊት ለማንም አንገቴን ሳልደፋ ተናግሬአለሁ 
የታደረከው ገንዘቡን? ብዬም ጠይቄአለሁኝ።
በመጨረሻም ለዛሬ ለጥያቄያችሁ ይረዳ ዘንድ፡
እኔ ሳልሆን መረዳጃ ማሕበሩ ከእድሩ ጋር እንዳልሆነ መልስ የሰጠው
በስብሰባው ላይ በእድርተኛ ለቅረበልት ጥያቄ የእድሩ ሊቀመንበር ነው የተባለው ነው።  ስለ እድሩ ልጠየቅም ለመልስም አልችልም እድሩ ውስጥ የለሁበትም እስከዛሬ ስለ እድሩ ምንም አይነት ጥያቄ ኖሮኝም አላውቅም ስለመረዳጃ ማሕበሩ ብቻ እንጂ። እድሩ እንዲቁዋቁዋም ከመደገፍ ሌላ አይቁዋቁዋም ብዬም አላውቅም መክኒያቱም ማንም እድር ማቁዋቁዋም መብቱ ነው። እኔም እድር የማቋቁዋም መብት እንዳለኝ ሁሉ።
ሲበተን ስለነበረው ወረቀትና ለምን እድሩ እንዳይቁዋቁዋም እንደጣሩ በጊዜው፡ ከዛም  እንዴት እድሩን ለይስሙላ ብቻ በመረዳጃ ማሕበሩ ስር ነው እያሉ ፍሮድ እየሰሩ እድርተኛውም ሕብረተሰቡም ሳያውቅ እስከወጡ ድረስ እንደኖሩ ማለትም አንድም ሰው ሳይረዱበት ገንዘቡ ሙልጭ ብሎ ሃምሳ አራት ሺው የራሱ የመርዳጃ ማሕበሩ እድሩ ሳጀመር በፊት ያለውን ጭምሮ ገንዘብ ከካቶሊክ ቻሪቲ ተሰጠን ያሉት ጭምር ያለወጪ እንደጠፋና ከትግሬ ነጻ አውጪ መግስት ሃምሳ ሁለት ገጽ መመሪያ ይዘው በመሃላችን ኢንፎርሜሽናችንን እያወጡ ከእድሩ የሚገኘውን ጭምር አደጋ ላይ ሕዝቡን እንዳጋለጡት ሰፋ አድርጌ ስለምጽፍ ለዛሬ ግን እድርተኛው መሳሪያቸውና ማስፈራሪያቸው አድርገውት ሕዝቡን ሰላም እንዳያገኝ እየተጠቀሙበት ስለሆነ
እድርተኛው እንዲጠነቀቅ አሳስብለሁ። እድርተኛውም ለእድሩ ችግር ፈጣሪዎች ናቸው በሚል ስለሚነጋራቸው ሰዎች እየደወሉ ችግራችሁ ምንድነው? ብለው ቢጠይቁ አንድም ሰው እድሩን እንደማይቃወምና የማንም ጉዳይ እንዳልሆነም ይረዱታል። በዚህ አይነት መንገድ ብቻ ነው ሰላማቸውን ሊያገኙና ሁላችንም የእድሩ አባላት ልንሆን የምንችለው።
እድርተኛውን በዛሬው ስብሰባ በሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ለማበጣበጥና ሃሰትም ለማስተጋባት እንደተዘጋጁ ከላይ እንደገለጽኩት ጥያቄ የጠየቁኝ ወገኖቼ ባሰረዱኝ መሰረት ደርሼበታለሁ። እነዚህ ሰዎች አልቆላቸዋል መረዳጃ ማሕበሩን በሚመለከት ነገር ግን እድሩን ለመቆጣጣርና ግባቸውን ለመምታት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ስለሌለ እድርተኞቹ እድር ውስጥ ካልገባው ወደ ሰላሳሺ ከሚሆነውም ወገን ጋር መጋጨት እንዳይሆንባቸው እላለሁ።
 እኔን በሚመለከት እድርተኛው በማንኛውም ጊዜና ሰአት ቀደም ብሎ ነግሮኝ ስብሰባ ቢጠራኝ እራሳቸው ሌቦቹ ባሉበት ለማስረዳት ዝግጁ ስለሆንኩኝ ችግር የለውም። እድሩን የምደግፍ መሆኔን ደጋግሜ እንደገልጽኩት አሁንም በድጋሚ እደገና ማረጋገጥ እወዳለሁ። በጁን አምስት በዴኒስ ሬስቶራንት ለኢትዮጵያ ቀን ዝግጅትን አስመልክቶ በተጠራው ስብሰባ በተገኘሁበት የእድሩ ጸሃፊ እየሰማ እድሩን እስከ ሶስትሺ ብሎም አምስትሺ ድረስ ባጭር ጊዜ እንዴት ልናደርሰው እንደምንችልና ሕግን በማይንጻረር መንገድ ሕብረተሰቡንም አደጋ ላይ በማይጥል እድርተኛውንም መረዳጃ ማሕበሩንም በሚረዳ መልኩ ሊሰራ እንደሚቻል  በስብሰባ አነጋግሩኝ ማለቴም እድሩን ስለምደግፍ ነው። እድሩን የምቃወም ቢሆን እቃወማለሁ እላለሁ ስለማልቃወም ግን ትቃውማለች እያሉ አጀንዳ በእድር ለማስያዝ መርዋርዋጥ ግን የእኔን ስም እየተጠቀሙ እድሩን ልክ ባልፈው እሁድ መረዳጃ ማሕበሩን አዲስ ቦርድ በእድርተኞቹ በመጠቀም አውርዶ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ እንደጣሩትና እንደከሸፈባቸው እድሩን በቁጥጥራቸው ስር ለመመለስ የሚያደርጊት ጥረት ነው። እኔ ሳልጠየቅ መልስ ሳልሰጥ አንድ ቃል ይዞ መሳሪያ የሚሆኑ ሰዎች የሐረርወርቅ ይሄን አለች ያን አለች ፡
ወሬ አናፋሽነታቸውን እንጂ ወንድነታቸውን አይደለም የሚገልጹት እድሩን በሚገባ የምደግፍ መሆኔን በድጋሚ በተደጋጋሚ እገልጻለሁ። ጊዜ ወስዳችሁ መወናበድ ስልችቶዋቸው ለደወላችሁልኝ ትልቅ ምስጋና አቅርባለሁ። ወሬ አናፋሹም እንደእናንተ ልብ ኖሮት ጠይቆ መረዳትን እንዲማር እጸልይለታለሁ።

 ላንባቢያንም ከምስጋና ጋር ፡
የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
 ዘብሄረ አንድ ኢትዮጵያ አንድ ሰንደቅ አላማ አንድ ሕዝብ።

Tuesday, July 26, 2011

"የኢትዮጵያ ቀን 2011 በዳላስቴክሳስ አዘጋጅ ኮሚቲ"

"Ethiopian Day 2011 Organizing Committee"
     Yeharerwerk Gashaw
         Chairperson
  


        ይችን ጥሩ ቀን ለፈቀደልን ምስጋና ለሁሉም ስልጣንና ወሳኝነት ላለው ለልኡል እግዚአብሄር ይሁን። አሜን። 
 
ዛሬ የቅዱስ ገብረኤል ቀን ነው። መልካም የገብረኤልቀን ያድርግልን።

አንባቢያንና ለኢትዮጵያ ቀን እንድናገለግል የመረጣችሁን በጠየቃችሁን መሰረት ባጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወንናቸውን እነሆ።
በጁን አምስት ማለትም አንድ ወር ሃያአንድ ቀን ሆነው ማለት ነው የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ በይፋ ለዚህ አመት የኢትዮጵያ ቀን በአል አዘጋጅ ኮሚቲ  ለማስመረጥ በጠራው ስብሰባ ላይ ጥሪ አክብረን በቦታው ተገኝተን በመጨረሻም ሰባት ሰዎች ተመርጠን ሁለቱ ወንድሞች በስብሰባ ባይሳተፉም አምስት የቀረንው የሰራንውን ኢሜል እያደረግንላቸው ካስታወቅን በሁዋላ አንዱ የስብሰባው ቀን ይቀየርልኝ ባሉት መሰረት ብንቀይርም ከተመረጥን በሁዋላ አንድም ስብሰባ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል። ሌላው ቀደም ሲል በደረሰባቸው አደጋ መክኒያት ከኮሚቲው ጋር ለመስራት በየጊዜው በስብሰባ ለመገኘት  እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሁለቱም ከኮሚቲው ለቀናል የሚል ደብድቤ ግን አልጻፉልንም። ሆኖም አምስት የኮሚቲ አባል ስራውን ስራውን ባጭር ጊዜ ለቦርዱ አቅርበናል። ተጨማሪ አስራ አምስት ሰዎችና ሰላሳ ልጆችም መዝግበን ለመጨመርም እየስራን ነው።

-----Original Message-----
From: yehar9 <yehar9@aim.com>
To: sesaxy <sesaxy@gmail.com>
Sent: Mon, Jun 13, 2011 6:16 pm
Subject: Ethiopian Day 2011 Organizing Committee meeting out come report to MAAEC

የዚህ አመት የኢትዮጵያ ቀን "የኢትዮጵያ ወጣቶች በአል" ብለንዋል። ወጣቱ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን አዘጋጅ ኮሚቲውን በሙሉ የሚመራው አድርገን አዘጋጅተንዋል። ፊልም ፕሮዲስሮችና ዳሬክተሮች "ዳላስ" የሚለውን በአለም የታወቀውን የቴሌቪዢን ሾው የሰሩ ሳይቀሩ ልጆቹን እድል ይሰጣሉ ለሁለት ሳምንት ኦገስት ውስጥ። ልጆቻችን ከእኛ ሕብረተሰብ ወጣ ብለው ብዙ ነገሮች ላይ ሊያሳትፍቸው የሚችል በር ልንከፍትላቸው ይገባል!
Ethiopian Day 2011 Organizing Committee
Dallas, Texas
በአቶ ስዩም የሕዝብ ግንኙነት አማካኝነት
ይድረስ ለኢትዮጵያ መረዳጃ ማሕበር በዳላስ ፎርት ወርዝ።

June13,2011

Subjec፡ meeting and out come report. ስብሰባችንና ውጤቱ ከአጭር ማሳሰቢያ ጋር በማጣመር.

በመጀመሪያ ትልቅ ሰላምታና ምስጋና ለኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር አስተዳደር ስናቀርብ ከአክብሮት ጋር ነው። እኛንም አስመርጣችሁ ሃልፊነቱና ይሰራሉ ብላችሁ እምነቱንም ስለጣላችሁበን ስለ እምንታችሁ በጣም እናመሰግናለን። ስራውንም እራሳችን ሰርተን ማንም ከሁዋላ ልብሳችንን ይዞ በዚህ ሂዱ በዛ ስሩ ሳይለን ችሎታችንንና አስተዋጽዎቻችንንም ታማኝነትን ለሕዝቡ ጥቅም ብቻ የተራብን መሆናችንን ጭምር የምናሳይበት በነጻነት የምንሰራበት መድረክ ስለሰጣችሁን በዚህ በዳላስ ፎርት ወርዝ አንድነቱንና ሰላምን አጥቶ በየት የአንድነት ሜዳ እንደሚገናኝ ግራ የገባው ወገን ስምና በራሳችንም እያመሰገነን ይሂንን ቀጥተኛ አሰራራችሁን በማጠናከር ቀጥላችሁ ወደ ፊትም በከተማው ለሚኖረው ሕዝባችን ጥሩ አራአያ ሆናችሁ የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት የጨዋ ጸባይን የጠፋውን በተለያየ መልኩ የክብር ችቦ አብርታችሁ በዳላስ ከተማ ላለው ወጣት እንደምታስረክቡ ተስፋ ጥለንባችሁዋል።
  የትናንትናው ጁን አስራ ሁለት ስብሰባና ውጤቱ ባጭሩ፡
ትናንትና ባደረግንው ስብሰባ በጣም ጥሩ ውጤት አምጥተናል። ተነድፈው በቀረቡት አሳራ ሃንድ የተግባር ኮሚቲ ላይ ስለ እያንዳንዱ የኮሚቲ ተግባርና ምን ያህል ሰው ለእያንዳንዱ ተግባር ማከናወኛ እንደሚያስፈልግ ጭምር ተነጋግረን ቀጥሎም በሻለቃ ሱራፌል የቀረበውን የሽልማት ኮሚቲ በአስራ ሁለተኛ ኮሚቲነት አስቀምጠንዋል። ለእያንዳንዱም የተግባር ስራ አምስት አምስት ሰው ልንመድብ ተስማምተናል። ለዚሁም እያንዳንዳችን አስር አስር ሰው መልምለን በሚቀጥለው ስብሰባ ካሳተፍን በሁዋላ እያንዳንዱ በበጎ ፍቃድ ተሳታፊ ምን ያህል ሰአት በቦታው ላይ እንደሚቆይ እና በእየ ሁለት ሰአቱ ወይም መቀያየር እንዳለበት ጭምር ወስነናል። አምስት ሰው ጠዋት አምስት ሰው ከሰአት አምስት ሰው ማታ እንደ ማለት ነው። ይሄውም ሁሉም የበአሉ ደስታ ተቁዋዳሽ እንዲሆን ሲሆን ከእነ ቤተሰቡ በአስተናጋጅነት ብቻ አይሰማውም በነገራችን ላይ ፡ የዚህ አይነት አስራር የተለምደ አልነበረም በመረዳጃ ማሕበሩ።የበአሉን ዝግጅት በተራ ተከተል ይሄውም ከመጀመሪያው ቀን መክፈቻ እስከ መዝጊያው ያለውን በዝርዝር በተራ ተከተል ለማቅረብ የእናነተ ሃሳብ መጨመር ስላለበት ከዚህ በታች ባስቀመጥነው ኮሚቶዎች ላይ የሚጨመር ኮሚቲ ካለ ጨምራችሁ እንድትልኩልን በኢሜል ወይም፡ ባለው እኛ የዝግጅቱ ኮሚ የተስማማንበትን ኮሚቲ ተስማምተናል ካልችሁም መልሳችሁን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ማለትም በጁን አስራ ስምንትና አስራ ዘጠኝ ድረስ ካስታወቃችሁን በኛ በኩል የኢትዮጵያን ቀን አስረኛ አመት ዝግጅት አጠናቀን ስራውን ለመጀመር በተግባር ይረዳ ዘንድ ልናቀርብላችሁ ዝግጁነን። ይሄንን ስንል የበአሉ አዘጋጅ ኮሚቲ እንደሚያስበውና እንደተዘጋጀ ከሆነ በጁን መጨረሻ ለእስፓንሰር ደብዳቤ መላክና በነብስም በቦታው በመገኘት እርዳታ የሚያበረክቱ ድርጅቶችን ጭምር ማነጋገር የምንጀምርበት ይሆናል። ማለትም ጁላይ ገንዘብና እርዳታ የምናገኝበት መጀመሪያው ሲሆን ከዛም ጎን በአሉንና ተሳታፊዎችንም ሕዝቡንም የምናነጋግረበት ይሆናል።
ቦታ ቶሎ መያዙ እስፓንሰር ለማብዛት ስለሚያስችለን በተለይ ፌር ፓርክ ቢደረግ በአሉ ይሄ ለአስራ አምስት አመት ከአሜሪካን ሕብረተሰብና ከውጪው እንዳይገናኝ ተደርጎ የኖረው የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ልቆ የሚታይበትና ለምሳሌ ታክሲ ነጂዎቹን ብንወስድ ሕብረተሰባችን በመረዳጃ ማሕበሩ ስም በብዙ መልኩ በከተማው ከመንግስት መስሪያ ቤት እከ እያንዳንዱ የዳላስ ፎርት ወርዝ ህብረተሰብ እንዲሳተፍ በማድረግ ትልቅ ስም ይሰጠን የነበረውን አጥቶ ታክሲ ነጂው ሲቸገር አንድ የመረዳጃ ማሕበር የታወቀ ባለመኖሩ ነበር በአሜሪካን ጋዜጠኞችና በሕዝብ ተመርጠው ስልጣን በጨበጡት በኩል ድምጽ ልናሰማ ሃይል የምንሆን ኢትዮጵያውያን ተፈልገን የተጠራንውና ያስተጋባንው። ታዲያ አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊት ይልቅ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርና ታዋቂ ቢሆን በበለጠ ክብር የለውም? ይሄን ለማድረግ እጃችሁ ላይ ነው ውሳኔው ወገኖች። ስለዚህ በየስርቻው በቀን አምስት ሺ እየተከፈለ ምንም ለውጥ ለሕብረተሰቡ በማያመጣ ስርቻ ሲደረግ የነበርው የኢትዮጵያ ቀን መንግስት በሚያስተዳድረው ፌር ፓርክ ቢደረግ ብዙ ጥቅም አለው። ለምን ታንክስ ጊቪንግ ይደረጋል የሚሉት እራስ ወዳዶችንም ቢሆኑ ያልደፈሩት ለኢትዮጵያውያን አኩሪ ቦታና ባንዴ ስማችንን ክብራችንን የምናስመዘግብበት ቦታና በአል ነው ፌር ፓርክ ማድረጉ። ቶሎ ከወሰናችሁ በዛሪና በነገው ውስጥ እስፓንሰር ላይ ብቻ ነው ሁላችንም የምናቶክረው ፌር ፓርክ ከሆነ ማንም ኮርፓሬሽን እስፓንሰር ያደርጋል። የበአል ዝግጅት ቦታና የሕብረተሰቡን ብዛት ስለሆነ የምንሸጠው ለእስፓንሰሮች በድጋሚ በተደጋጋሚ ፊር ፓርክ የኢትዮጵያ ቀን የአስረኛው  በአል ቦታ ቢሆን ይመረጣል። ለምሳሌ የከተማውን ከንቲባና አማካሪ፡ የአሜሪካን ምክር ቤት አባላትንና ዳኞችን የኢሚግሬሽን ዳሬክተርንና ታዋቂ የሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎችን ጭምር ብሎም እንደ ጄሪ ጆንስ የዳላስ ካው ቦይ ባለቤትን ብሎም ተጫዋቾቹን ለመጋበዝ ቦታው የመጀመሪያው ጥያቄ ይሆናል። አስቡበት በዚህ ዝግጅት ገንዘብ ከውጪው ድርጅቶች ለማግኘት መሆን ይኖርበታል አላማችን። መልሳችሁን የምንጠብቀው በቅርብ የኢትይጵያ ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ።
ከአክብሮት ጋር በኮሚቲው ስም፣
የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
ሊቀመንበር።
ከሕብረተሰቡ ገንቢ አስተያያት ከተሰጡት ሁለቱን ብቻ፡
ለብዙ አመት የኢትዮጵያ ቀን በአል ቀኑ ሲደርስ ኑና ስሩ በሚል ብቻ እየተጠሩ ሲያገለግሉና እንደ ቆሻሻ ወረቀት ሲጣሉ ተረስተው ነገር ግን አመቱ እንደገና ሲመጣ ብቻ የሚታወሱት ከዚህ በታች የሰጡትን አስተያየት እነሆ፡
በቀኑ ከእኛ ጋር ከተሰበሰቡት "አሁን በስብሰባው ተገኝቼ ካገኘሁት በተግባር መምጣቴን ተደሰትኩበት። መክኒያቱም ምንም እንክዋን ለብዙ አመት ለኢትዮጵያ ቀን በበጎ ፍቃድ ሳገለግል ብቆይም አንድም ቀን እንደዚህ እንደዛሬው ስብሰባ ተጠርቼ ገንቢ ሃሳብንና ለሕብረተሰቡ የሚጠቅመውንና የማያስፈልጉና የማያስፈልጉ ተግባሮች ላይ ህሳብ ስጥቼ የእኔም ሃሳብ በበአሉ ዝግጅት ውስጥ ገብቶ ስራ ላይ ውሎ ላይ ይቅርና ምን ታሰባለህ ብሎ እንክዋን አክብሮ ጠይቆኝ የሚያውቅ አንድም የመረዳጃ ማሕበሩ አባል አልነበረም። ዛሬ ግን በተሰጠኝ ያገባህልና ምከርበት በዝግጅቱ ተብዬ ሃሳቤን ለመስጠት በመቻሌ የኢትዮጵያ ቀን በአል አዘጋጅና የመረዳጃው ማሕበርም ባለቤትነት ስሜት እንዲኖረኝ አድርጋችሁኛል ስለሆነም ለመረጡዋችሁና ላስመረጣችሁ ለመረዳጃ ማሕበራችን አዲስ ተመራጮች ንገሩልኝ" ብለው ላለፈው ስድስት አመት ከተካፈሉት የኢትዮጵያ ቀን በመነሳት መታረም ስላለባቸውና ሌላው ቢቀር ቲኒሽ የምስጋና ደብዳቤ ወይም ሰርተፍኬት እንዲዘጋጅ ጭምር መደረግ ያለበትን በተግባር ኮሚቴ አሰራር ውስጥ እንዲገባ ባቀረቡት የነጻ ሃሳብ መግለጽ በደስታ ተቀብለን መዝግበንዋል።
ሁለት ወጣት ሴቶች ለብዙ አመት በኢትዮጵያ ቀን የተካፈሉት ለቦርዱ እንዲተላለፍ ከጠየቁን፡
እኛ በጣም የሚያሳዝነና በዚህ አመት መካፈል የማንፈልገው አንድ ነገር አለ ይሄውም፡ ልክ የኢትዮጵያ ቀን ሲዳረስ ሁለት ሳምንት ሲቀረው መጥታችሁ ደንሱ እንባላለን በቤተክርስቲያን በኩል። ነገር ግን ምን እኛን እና ጉዋደኞቻችንን እንደሚያስደስተንና ሊሰበስበን እንደሚችል የሚጠይቀን አንድም አላይየም ከእነ ቤተሰቦቻችን ጭምር ሄዱና ተካፈሉ የኢትዮጵያን ቀን በአል ዝግጅት ከመባል ሌላ።  ለምሳሌ ባለፈው አመት የተደረገበት ቦታ እንክዋን መንገድ በደንብ ለማያውቅ ኢትዮጵያዊ ይቅርና ለእኛ ለወጣቶቹ እንክዋን የነበረው ችግር በጣም አሳዝኖናል። እልም ያለ ይሄ ነው ሊባል የማይችል ቦታ አንዴ ስህተት ተደርጎ ከታለፈ ለመመለስ አስቸጋሪ የነበረበት ነው።
አንደኛ ቀረብ ያለና ወጣቱን ድግሞ የሚያሳትፍ ካልሆነ በዛ ላይ ልጆች ሁሉ በሃይማኖት ስም እንድንከፋፈል አድርገዋል ቤተሰቦቻችን ጭምር የመረዳጃውም ተጠሪዎች ፈጽሞ ከወጣቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውና እዛም ስንሄድ ክብር አይሰጡንም ፓሊስም ይጠርብናል አንዳንዲም። እንደዚያ ሳይሆን በደንብ የምታሰባስቡን ከሆነ እንሳተፋለን በተለይ ለሞደሊንግን ኮሜርሻል ፊልም ለመስራትም ስለምንፈልግ እድሉን የሐረርወርቅ እንደምትከፍትልን ካለፈው አፎሚያን ኒኮሎዲያን ላይ ስላየናት እየጉዋጉዋን ነው። እድሉን ያገኘችው በየሐረርውርቅ በተዘጋጀው ሾው መሆኑንና እስኮላርሺም እንዳገኘችው ሁሉ፡በሚል ደመደሙ ገንቢ ሃሳባቸውንና ምኞታቸውን ። 

Ethiopian Day 2011 Organizing Committee
Steering Committees

1.Sponsors/Support Committee
2.Venders/ID Committee

3.Silent Auction

4.Finance/Membership drive Committees

5.Entertainment Committees

6.Souvenir Booklet/Programs

7.Media/Public Relations/Community Relations

8.Children Village

9.Schedule & Super Vising Committee

10.Volunteer & Hospitality Committees Security

11.Guest Coordinating and Feed Back-Task as needed Committee

12. Honoring Committee

Monday, July 11, 2011

Oriental Orthodox Youth Confrerence


By Lielt Samuel,

For those who don’t know, a three day Oriental Orthodox Youth Conference, organized by our own Deacon Andualem, took place at St. Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Debre Meheret St. Michael Church in Garland, Texas this past week (July 7th-9th). Visitors from other oriental orthodox churches around the Dallas area that attended the event included those from St. Thomas Indian Orthodox Church, St. Mary Syrian Orthodox Church, St. Philopateer Coptic Orthodox Church, and St. Mary Ethiopian Orthodox Church. Guest speakers including priests and professors came to preach to the youth from these churches as well as St. Mary Ethiopian Orthodox Church in Los Angeles, and the University of Toronto in Canada.

The first two days of the conference were divided into three sessions daily (according to age) which were composed of lessons, prayer and mezmur, icebreakers and activities for the youth to get to know one another and enjoy, and a grand dinner to finish off the day. On the third day of the conference, for the first time at St. Michael, the divine liturgy was given in English so that all youth attending could understand and take part in the mass.

The youth conference was a great experience! It was refreshing to have an event at church that was centered around the youth, as well as one in which we could meet brothers and sisters in Christ from other Orthodox churches. We learned a lot about the importance of our tradition and religion as well as the similarities in our churches from the wonderful speakers that came to talk to us. The Diving Liturgy being given in English was an outstanding part of the conference that allowed us to really understand the significance and importance of the Kidasse that takes place at our church every Sunday.

I thank Ethiopian Orthodox Tewahedo Debre Meheret St. Michael Church for their great support of the event as well as Deacon Andualem for organizing the conference and always thinking of the youth. I look forward to the youth conference next year being even bigger and even better event!