Monday, July 25, 2016

የአማራውን ብሄር ነብስ የማጥፋት ጭፍጨፋን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስደት መንግስት በጥብቅ ያወግዛል

Ethiopian National Government In Exile (ENGIE)


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የስደት መንግስት
በወያኔ ላይ ይፋ መግለጫ።

ዳላስ ቴክሳስ ዩኤስኤ።
July 23, 2016

ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ምድር እና ተበታትንህ በምትገኝበት አገር እና ምድር ሁሉ።

በሰሜን ኢትዮጵያ በጎንደር በወልቃይት ጠገኔ እናም በጠለምት ሕዝብ ወገናችን ላይ ሰሞኑን ከመቼውም የበለጠ ሆነ ተብሎ በገፍ እና በግፍ የአማርኛ ተናጋሪው (አማራው) ላይ የተፈጸመውን ግድያ የአማራውን ብሄር ነብስ የማጥፋት ጭፍጨፋን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስደት መንግስት በጥብቅ ያወግዛል።

በመጨረሻም ወያኔ  በጎንደር ወልቃይት ጠገኔ እና በመላው የሰሜን ኢትዮጵያ እና በመላው በተቀረው የኢትዮጵያ ምድር በእየእስር ቤቱ አስሮ የሚያሰቃያቸውን ለእናት አገር ኢትዮጵያ አንድነት እና ዴሞክራሲ ለፍትህ በሰላማዊ መንገድ እየታገለ ሳለ እንደወንጀለኛ እያደነ ያሰራቸውን ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በሙሉ ባስቸኩይ እንዲለቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስደት መንግስት በጥብቅ ያሳስባል።

ኢትዮጵያ በነጻነትዋ ታፍራ እና ተከብራ እራሳቸውን ለፈረንጅ : ለአረብ ብሎም ለማንም የበላይነት ሰጥተው አገራቸውን እና እራሳቸውን ሕዝባቸውን ዝቅ በማያደርጉት ኢትዮጵያውያን ሴቶች እና ወንዶች ልጆችዋ ተከብራ እና ታፍራ ለዘለዓለም ትኑር!


                  

Email yehar9@aol.com Phone number 214-642-0394