Tuesday, April 16, 2013

የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዳላስና አመሰራረቱ (ዛሬ በጋርላንድ የቅዱስ ሚካኤል ደብር)



በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

በየሐረርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)
ዳላስ ቴክሳስ።

ቁጥር አንድ።

ከዚህ በታች ያለውን ዘገባ ሊያስነሳ የቻለው ከአንዱ ከቀድሞ የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበርና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ተገዝቶ እዳውን ከጨረሰ በሁዋላ በመጣ ግለሰብ ጭምር የተሰነዘረው አወዛጋቢ አባባል ከዚህ በታች እንደሚነበበው ነው። ይሄውም በቀኑ አሁን ባለው የቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ አማካኝነት፡ ሁለት አርእት የያዘ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር። በገለልተኛ ወይስ አባት ይኑረን? ማለትም በሲኖዶስ ወይስ ያለ ሲኖዶስ ማልት ሲሆን ጉዳዩን ለማታውቁት አንባቢዎች ግልጽ እንዲሆን፡ በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘት የቀድሞው የቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት የነበረው በበኩሉ ተነስቶ በስብሰባው ላይ አዲስ ወደ ዳላስ የመጣችሁትም ሁኑ በዳላስ የቆያችሁት በጊዜው ብትኖሩም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲቁዋቁዋም ምንም የምታውቁት ነገር የላችሁም በሚል ቁጣና ክህደት የተሞላበት አስተያየቱን ተናገረ።  

ሁለተኛ ግለሰብና ሌላው የቅዱስ ሚካኤል ደብር በሂሳብ ክፍል ተቀጥሮ በደሞዝ የሚሰራ ነው ተብሎ የተነገረን በበጎ ፍቃድ የሚያገለግል ነበር ብዙዎቻችን የሚመስለን እናም በቀኑ በስብሰባው ቦታ የተገኘበትን ዋና መክኒያት ሲያስተጋባው ለማመን ብዙዎቻችን እንደተቸገርን በመገረም የማያጠያይቅ ሃቅ ነው። ከተናገራቸው ሁለቱንና ዋና ዋና አስገራሚዎችን ብቻ ሃሳቦቹን ብቻ ለመጥቀስ ግልጽ እንዲሆን በቦታ ላልነበራችሁት ይረዳ ዘንድ፡ ግለሰቡ እጁን አውጥቶ የመናገሪያ ጊዜ እንደማንኛውም የቤተክርስቲያኑ አባል ጊዜ ጠይቆ ሲሰጠው የተናገራቸው ከባድና አሳዛኝ ከፋፋይ መርዝ የሆኑ ከእውነት የራቁ የምስክርንት ቃል ነበር። ይሄውም "እኔ የመጣሁት ምስክርነት ልሰጥ ነው !!!" ሲል፡ በበኩሌ አምላክ ላደረገለት ደግ ነገር እንደማንኛውም አማኝ ስለ ፈጣሪያችን እየሱስ ክርስቶስ ደግነት ሊመሰክር ነው የመሰለኝ እንጂ ስለ ግለሰቦች አልነበረም ። ቀጥሎም የቅዱስ ሚካኤል ደብር የአስራ ሁለት ሰዎች መሆኑንና ከአዲስ አበባ ለእረፍት ወደ ዳላስ በመጣበት ጊዜ ቀደም ሲል አመተምህረቱን ጠቅሦ በደንብ አንከባክበው ያስተናገዱት በጊዜው የነበሩት የቦርድ አባሎች ስለነበሩ ቤተክርስቲያኑም ግለሰቦቹም ለሱ ባለውለታ ስለሆኑ፡ ቀጥሎም ቤተሰቡንም ጠቅልሎም ሲመጣ ወደዚሁ ወደ ዳላስ ብዙ የረዱት በመሆናቸው የቤተክርስቲያኑ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ባለቤቶች እነዚህ የኔ ባለውለታዎች ናቸው አለን። ስብሰባውን በሙሉ ተጀምሮ እስኪጨረስ ቤተክርስቲያኑ በቪዲዮ እየቀዳን ነው ስላሉን በስብሰባው እለት ያልተገኛችሁ በሰፊው መረጃ ለማግኘት ትችሉ ዘንድ የቤተክርስቲያኑን ቦርድ ብትጠይቁና ተጨባጭ መረጃውን ብታዩ ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ። ለዛሬ ግን ሌሎች ጥያቄዎቻችሁን ወደ ጎን አስቀምጬ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሁዋላ ደብር እንዴት ተመሰረተ ወደ ሚለው ብቻ እወስዳችሁዋለሁ።  

ከዚህ በታች አቶ ታደሰ ግዛው ነብሳቸውን ይማረውና ፈጣሪያችን ፤ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን መመስረትን አስመልክቶ በስልክ ጥሪ አድርገውልኝ ሴት ልጃቸው ቤት አለን ቴክሳስ ይኖሩ ወደ ነበረው ቤት ሄጄ የቁርስ መብያው ጠረቤዛ ዙሪያ ተቀምጠን ተንትነው በሳቸው በኩል ያለውን በሙሉ ልጽፍ ችያለሁ።

የሐረርወርቅ ጥያቄ፡
ጋሼ ታደሰ እኔ እስከማውቅ ማለትም አቶ ታደሰ ጸሃዬን አስመልክቶ የዛሬውን አያድርገው እንጂ ለሁሉም ኢትዮጵያዊና ለአንድ ኢትዮጵያ ተቆርቁዋሪ እንጂ የአንድ ጎሳ ድምጽና አጋር አልነበረም እኔ እስከገባኝ ድረስ በጊዜው። ይሄንን ስል በወሬ ሳይሆን እራሴ ከማውቀው በተግባር ከማውቀው ነው ይሄውም፡ አቶ ታደሰ ጸሃዬ በየጊዜው እየደወለልኝ ኢትዮጵያውያን ላይ አደጋ ሲጣል በእየሱቁ ፡ ድምጽ እንድሆን ወይም እንድቆምላቸው እንደሚደውለው ሁሉ አዲስ ከተለመደው የተለየ ሌላ ትልቅ ቁም ነገር ይዞ ይደውልልኛል። ይሄውም ከተናገራቸውም መሃል ለእርሶ ለማስረዳት "ቤተክርስቲያን መግዛት አለብን ለዚህም ገንዘብ ባስቸክዋይ አስፈላጊ ነው ባንች በኩል ለሕብረተሰቡ ለምታውቂው ጭምር የዚህን ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት አድርገሽ የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርጉ አስተባብሪ ቤተክርስቲያን አግኝቻለሁ ገንዘብ ነው የሚያስፈልገው" አለኝ። እኔም ሃሳቡን ተቀብዬ ወዲያው በተግባር እንዳለው ማድረግ ጀመርኩኝ ማለት ነው። በበኩሌ ቤተክርስቲያን እንግዛ ብሎ እናንተን ያሰባሰበው ይሄው ታደሰ ጸሃዬ ነው። በእርሶ በኩል ከዚህ የተለየ አለ?

መልስ፡ አቶ ታደሰ ግዛው
"አዎን ሃሳቡን ያመጣው እንዳልሽው ታደሰ ጸሃዬ ነው ይሄውም የራሺያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ልጆቻችንን ቄሱ ሲያመናጭቃቸው ስላዬ ተናዶ እዛው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ወዲያው ሰውዬው አይወደንም ለምን የራሳችንን ቤተክርስቲያን አንገዛም በሚል በቁጪት የተነሳው። በዚህ መልክ እኔም ተስማማሁ ዮሴፍንም አነጋገርን ሌሎችንም አሰባሰብን ማለት ነው።

የሐረርወርቅ ጥያቄ፡
በገንዘብ በኩል እናንተስ ያዋጣችሁትን አልሰማሁም ገንዘብ እርሶስ ስንት አወጡ?

መልስ አቶ ታደሰ ግዛው፡
ሳቅ ብለው "እረ የለም! ቤተክርስቲያን ሲገኝ ቦታው መጥፎ ነው በሚል ያስቸገሩ ነበሩ በተለይ ወይዘሮ--- ሆኖም አቅማችን አልፈቀደም ሌላ ቦታ በመጨረሻ ታደሰ ጸሃዬ ኪንግ ስትሪት ላይ ያገኘንውን ቤተክርስቲያን ገዝተን ለማደስና ለማጽዳት ወሰንን። አደገኛ ነው የጥቁር ሰፈር ነው በሚል ብዙ ውጣ ውረድ ደረሰብን ሆኖም ይሄንን ለመግዛት መጀመሪያ አየንውና አንዳንድ ሺ ዶላር እንሰጣለን ብለን ነበር። ሆኖም እኛም ሳናዋጣ ሕዝቡ ባዋጣው በአንድ ቀን አባ ፍቅረማሪያምን ይዘን በመዞር በእየነጋዴው ሱቅ ጭምር የመነኩሴው መኖር እምነትም በሁሉም ሰላሳደረ ሁሉም ተባበረን በዚህ መልክ ተገዛ እንጂ ከመሃላችን አውጦ ገንዘብ የሰጠ አልነበረም"

የሐረርወርቅ ጋሻው ጥያቄ፡
ዮሴፍ ሚካኤል ይባል ቤተክርስቲያን ያለው ማነው?

መልስ አቶ ዮሴፍ ረታ፡
ስሙን አሁን አላስታውስም ነገር ግን እሱንና አቡነ ጳውሎስን ይዤ መኪና ውስጥ እየሄድን እያለን፡ እሱ ነው ለምን ሚካኤል አትሉትም የሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚል በሌላም ከተሞች የለም ያለው ከዚሁ ሰው ነው ሃሳቡ ሚካኤል ይባል የሚለው የመጣው። አቡነ ጳውሎስም ጥሩ ሃሳብ ነው ብለው ሚካኤል በሉት የምትገዙትን ቤተክርስቲያን አሉ እዛው መኪና ውስጥ።"

በሚቀጥለው በዙሁ መልክ ቀንጨብ አድርጌ እካስነብባችሁ በተከታታይ እንዳስፈላጊነቱ አንደኛ ቤተክርስቲያኑ የክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን እስልምና ሃያማኖት ተከታዮች ሳይቀሩ ባዋጡት ገንዘብ የተገዛ ነው።

በእርግጥ የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ባለቤት ሕዝቡ አዋጥቶ የገዛው መሆኑ ሃቅ ቢሆንም ዝም ብሎ የተገዛ ያለመሆኑንም በመረዳት የቤተክርስቲያን ባለቤቶች ያደረጉንን የምስጋና ቀን በማዘጋጀት እግዚአብሄር ይስጥልን ልንል ይገባል ይሄንን ለማድረግ ሰው ሲሞት መጠብቅ የለበትም አሁን ነው ጊዜ። የሰሩ ሰዎችን በሰሩት ቦታ ተቀምጠን ውለታቸውንም መብላት መካድ ስለሚሆንብን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባላትን ሁሉ ማሳሰብ እወዳለሁ።

አሰቃቂ ነገር። የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሕይወቱ ታሪክ ማህድር ምን በላው?

የሕይወት ታሪክ ያልኩት አማርኛው ጠፍቶኝ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ለሕይወታችን በመንፈስ ሕይወታችንን ውሃ የምታጠጣ እራስዋ ሕይወት ነች ብዬ ስለማምን ነው።

ከትክክለና የቦርድ አመራረጥና መረካከብ ልጀምር። በድምጽ ብልጫ መመረጥ እንዳለ ሁሉ ለተመረጠበት ቦታ አንድ ሰው ወይም ስብስብ ከስራው ሃላፊነት ጋር ይሚረከበውም አለ በተለይ፡ መተዳደሪያ፡ እስከተረከበበት ጊዜድረስ አስረካቢው የሰራቸውና ከዛም በፊት ካስረከቡት የተረከበው፡ የተግባርና የድርጅቱ ታሪክ ወይም የቤተክርስቲያኑ ብሎም ገንዘብን ይጨምራል ባጭሩ። ይሄ በተለይ በኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን የተለመደ አይደለም። ይሄውም በመረዳጃ ማህበርም የታየ ነው ስቆ መቶ ምረጡኝ ብሎ ወይም ተግደርድሮ ቦርድ ውስጥ ከገባ በሁዋላ ቦታውላይ ላስቀመጠው ሕዝብ ሳይነግር በስነስርዓት እንዳላደገ ልጅ ከተቀሩት የቦርድ አባላት ካልተስማማ ወይም ሕዝብ ጎጂ መሆናቸውን ሲያውቅ አኩርፎ ቦታውን ጥሎ የመንደር ወሬ በድብቅ እያወራና እያስወራ በሃላፊነት የተረከበውን ሳያስረክብ ለጎጂዎች ቦታ ትሎ ይቀራል። ሕብረተሰቡም እምነት የማይታልብህ ከንቱ አይለውም አይ ጥሎ ወጣ ለምን? ከማለት በስተቀር። ይሄ የተለመደ አሰቃቂ አሰራር ሲሆን መቆም አለበት። በማኩረፍ ወይም መቁዋቁዋም ለተመረጠበት ሰው በቂ ካልሆነና የተረከበውን የማያስረክብ መጠየቅ ይኖርበታል ብቃት የሌላቸውም ሰዎች ቦርድ ውስጥ ባአፈጮሌኔትም ማስገባት አይገባም። የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንም ችግር ከዚህ የተለየ አይደለም ባብዛኛው።

የቅዱስ ሚካኤልን ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለውን ታሪኩንና በየጊዜውም ለቤተክርስቲያኑና ለምእመናኑ ይጠቅማል በሚል ያቀረብናቸው ደብዳቤዎች ሳይቀሩ መወሰድም ይሁን ወይም መሰረቅ የሌለባቸው የዋይት ሃውስ ዶኩመንቶች ሳይቀሩ ውሃ እንደበላቸው ነው የተረዳሁት። እንዴት? ቢባል ሌላውን ልተወውና አባት ይኑረን ወይስ ገለልተኛ ሆነን እንቀጥል በሚል ስብሰባ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ስበሰባ አባላትን ጠርቶን በቦታው ተገኝቼ ስለነበር ከሰማሁዋቸው አሰቃቂ መልሶች አንዱ ከዚህ እንደሚከተለው ነበር።

አንድ ወንድም ተነስተው ቤተክርስቲያኑ በገለልተኛነት እንዲሆን በጊዜው የነበረው ቦርድ ሕዝቡን አማክሮ ወይም ስብሰባ ተጠርቶ በስብሰባ ተወስኖ ነው ወይስ እንዴት ሆኖ ነው በማን ውሳኔ ነው ኢንዲፔንደንት ሊሆን የቻለው? የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። የጠያቂውን ስም ወይም ማን እንደሆኑ አላውቅም በአይን ባያቸው እንጂ ለዚህ ነው አንድ ወንድም ያልክዋቸው።

የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ ቀጥተኛ መልስ ሰጠ። ይሄውም፡ በበኩሉ ቦርዱም ይሁን እሱ የተረከቡት ምንም ማስረጃ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንደሌለና በገለልተኛነት የቅዱስ ሚካኤል ደብር እንዲሆን ማን እንደወሰነ ወይም እነማን ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ነው። ይሄንን መልስ ሙሉጌታ ሲሰጥ ቦቦታው የቀድሞው ሊቀመንበር በገለልተኛነት ቤተክርስቲያኑን ለማድረግ የተስማማው እዛው ነበር። ከያዘው ደብተር ላይ መልስ ለመስጠት ሲሞክር ነበር። ጉዳዩ አሰቃቂ ነው። ታዲያ ቤተክርስቲያኑን እነ ሻለቃ ክፍሌ ሙላትና አቶ ምስክር ሲመሩት የአመታዊ የስራ ተግባር ሳይቀር ገና ወደ ቤተክርስቲያኑ ጽፈት ቤት ሲገባ ግድግዳ ላይ ፊትለፊት ይታይ ነበር ብዙ መስሪያ ቤት ውስጥ እንደሚታየው። ያሁሉ አሰራር የትደረሰ?

ያም ሆነ ይህ የቤተክርስቲያኑ የአስተዳደር ሄደትና የወጣ የወረደበት በእርግጠኛ የትነው ያለው? ለምን አሁን ላለው ቦርድ የቤተክርስቲያኑን የታሪክና የተግባር ማህደር ሲጀመር ጀምሮ ያለውን ያለፉት አላስረከቡም ውይም አያስረክቡም? የቤተክርስቲያኑ አካል አይደለም ወይ ታሪኩ? ማን ወሰደው? የት ነው? ምን ሲጥ አደረገው?

ምክር፡
አሁን ያለው ቦርድ በሚገባ ቅደም ተከተሉን የተግባርም ይሁን ታሪካዊ ማህደርን ለሚቀጥለው ቦርድ ማለትም ለወጣቱ ትውልድ ጭምር ጥያቄ ቢቀርብለት የተረከብኩት የለም ብሎ የሚያልፈው ሳይሆን የተላለፈልኝ አኩሪ ስራና ታሪክ ብሎ ቤተክርስቲያኑ ገና ሲገዛ ጀምሮ እስከዛሬ ያለውን ታሪክ ትፈረው ቀጥተኛ አሰራር ማለትም ሁሉንም በተግባር መመዝገብ ልምዱ እንዲሆን ይረዳው ዘንድ የቦርድ አስተዳደር ትክክለኛ የሙያ አሰራርና የመረከብና የማስረከብ ባህሉን ግዴታንም በመቸመር አስተማሪ ለሚቀጠለው ተረካቢ እንዲሆን አሳስባለሁ። በትክክሉ ስራዎች እንዲሰሩ ምክር መስጠትም ትልቅ አስተዋጽዎ መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል። መረከብ እናዳለ ማስረከብም መለመድ ይኖርበታል ግዴታም ነው።

ከዚህ በላይ ያሰፈርኩት ፍቃድህ በመሆኑ ዛሬ አሜን!!!







     

Saturday, April 13, 2013

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

Press Release Credit: Ginbot7 Popular Force (GPF) 
For more information visit GPF's website.

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

Apr 13, 13 • by •           

ቀን ሚያዝያ 5 2005/ጋዜጣዊ መግለጫ 0002

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

ዛሬ ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።
 
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ይህን በእብሪትና በጥላቻ የተሞላ በወያኔ የሚፈጸም በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የባላጌዎች ጥቃት ማስቆም የሚቻለው የወያኔን እብሪት በጠመንጃ እና በተባበረ የህዝብ አመጽ ማስተንፈስ እስከተቻለ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። እስካሁን ወያኔ በከንቱ ያፈሰሰውን የንጹሃን አማሮች ደም መፋረድ የሚቻለው ከጠምንጃ አፈሙዝ በሚወጣ እሳት ብቻ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። ከንፈር መምጠጥ፣ ዋይታ፣ ኡኡታ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰላማዊ ሰልፍና በየፈረንጅ በር ደጅ መጽናት ወያኔ የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር የወያኔ እንጨት ሰባሪና ውሃ ተሸካሚ አድርጎ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ገፎ አዋርዶ ለመግዛት የዘረጋውን መርሃ ግብር እንዲያጥፍ አያደርገውም።
 
ወያኔ ይሉኝታ ያልዘራበት፣ ትእግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ ሳቢነትን እንደሞኝነት የሚቆጥር በአማራው ላይ ቂምና ጥላቻን ሰንቆ የተነሳ ጨካኝ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ስለጀግንነቱና ስለወርቅ ዘርነቱ እጅግ የተሳሳተና የተጋነነ ግምት ያለው፣ ማንም ምንም አያደርገኝም በሚል ትምክህት ተወጥሮ የሚኖር ድርጅት ነው። ከእንዲህ አይነቱ በራሱ ፕሮፓጋንዳና ከንቱ ውዳሴ ከሰከረ ድርጅት ጋር የሚደረግ ትግል ያለምንም መወላወል በከፍተኛ እልህና ጭካኔ የሚካሄድ ብቻ ነው። የአማራውን ሰቆቃ ለማስቆም ወያኔ “እዩኝ እዩኝ” እንዳለለ “ደብቁኝ ደብቁኝ” እስከሚል የሚዘምቱበት እና ክንዳቸውን የሚያሳዩት ጀግኖችን ይሻል። ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው ገድለው ለመሞ ት የቆረጡ የወገን ደምመላሾችን ይጠይቃል። ቤታቸውን ዱርና ገደሉን አድርገው፣ “ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል” የሚሉ ቁጡዎችን ይፈልጋል። የአማራውን ህዝብ እልቂት ለማቆም፣ የወንድ ልጅ እናት በገመድ የምትታጠቅበት፣ ልጇን አሞራ እንጂ ሰው የማይቀብርበት ሌላ ታሪካዊ ዘመን መምጣቱን ሁላችንም መቀበል ይኖርብናል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል አባላት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያሳየው እብሪት ተቃጥለናል። በግነናል። የእዚህ እብሪት ማርከሻ ጠመንጃ ነው፡ እሳትና አርር ብቻ ነው ብለናል። ሌላው ሁሉ አማራጭ ተፈትሿል፣ተሞክሯል፣ታይቷል ሌላ አማራጭ የለም ብለናል። የቀረው አንድ ምርጫ ነው፦:መሞ ት ወይም መግደል ። እኛ ይህን አውቀን ከያለንበት ተጠራርተን የአማራን ህዝብ በቀላሉ ልንደርስበት በምንችልበት ምድር እየተሰባሰብን ነው። የከፋህ፣ የመረረህ፣የተበደልክ በቃኝ ያልክ ና ተቀላቀለን፣ የወገናችንን የአሳርና የመከራ ዘመን ማብቃት በወያኔ ቀብር ላይ እናረጋግጥ ።

ውድመት ለአማራ ህዝብ ጠላት ለዘረኛው ወያኔ!!!!!!!!!
ድል በወያኔ ለሚረገጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!!!!!!!!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል
                    

Friday, April 12, 2013

Yeharerwerk Gashaw, while student has contributed to the development of Dallas Community Colleges' popular program known for some times now as "Multicultural Center-ESL"

  The Center was developed to provide advisement, assessment, degree planning and transfer information for all foreign nationals and second-language English speakers this includes refugees from Ethiopia in the 80s. In the picture, Yeharerwerk Gashaw wearing her Ethiopian native dress with Brookhaven newly international students program founders Brookhaven faculty and Dallas Chapter of Links.

News paper and photo credit: Brookhaven College- The Courier Staff Reporter Tracy Frye.  






Thursday, April 4, 2013

Listen to Dr. Fikre Tolossa by calling 218-862-1300 code 126285 on "Menyeshalal?" radio on April 7, 2013.

በየሐረርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)

My e-mail? yehar9@aol.com

ከዚህ በታች ባለፈው እሁድ በእየሳምንቱ እሁድ ከዋሽንግተን ዲሲ በአቢሲኒያ ሬዲዮ ላይ "ምንይሻላል?” በሚል በሚቀርበው ሬዲዮ ላይ ዛሬ ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ላጋጠመን ችግር ከብዙ ትግል በሁዋላ መድሃኒት ሆኖ ያገኘሁት ታሪኩን ግልጽ አድርጎ ጎልጉሎ የሚያስተምረው፡ የሚያስረዳው፡ የሚያስነብበው እና ለታሪኩም በመቆም የሚታወቅ ሙሁርን በሰፊው በተገኘው መድረክ ሁሉ ሕዝብ ጆሮ እንዲገባ ማድረግ ነው በመረጃ:: አንድን ሕዝብ በመከፋፈል ነጻ አውጪህ ነኝ እያሉ አማራ ኦሮሞ፡ ትግሬ ፡ ጉራጌ ፡ ወላይታ፡ ከንባታ ወይም ደቡብ ሰሜን እያሉ ሕዝቡን ለሚያወናብዱት ሁሉ ማሸነፊያው ታሪካችንን ማወቅና ለማያውቀው ከላይ እንዳስቀመጥኩት ማሳወቅ ነው በመረጃ። ስለሆነም ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ የታሪካችን መድሃኒት በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በጎሳ በሽታ ያልተነደፈና የጎሳን በሽታ ወይም ቫይረስ መከላከያ በእጁ ያለውን በሬዲዮ ቀርቦ እንዲያክመን በጠየኩት መሰረት የምንይሻላል የሬዲዮ ስርጭትም ባለቤት አቶ አያሌው ብሩም እንደኔው የአንድነት ጉዳይ የሚያንገበግበው በመሆኑ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን አቅርቦ ነበር። አሁንም በሚቀጥለው  ሳምንት እሁድ ኤፕሪል ሰባት (April 7, 2013)በዋሽንግ 
7: PM ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን እናቀርባለን፡፤  እናቀርባልን ስል ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ንገር አለ ይሄውም የምንይሻላል የሬዲዮን ስርጭት በአስተያየት በጣም የተለያየን ሰዎችን ማለትም የወያኔ መንግስትን ስርዓት ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎቹን ብሎም ልንገጠል የሚለውን ጭምር በስልክ  በጠረቤዛ ዙሪያ መልክ እያቀረበ አገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቡ ካለው ችግር ለመውጣት የሚያስችለው መፍትሄ ለማግኘት "ምንይሻላል?" በሚል በሃሳብ እርስ በእርሳችን የምንታገልበት የሬዲዮ ስርጪት ሲሆን፡ የሚተላለፈውም  "ሬዲዮ አቢሲኒያ" ላይ ማልት ነው። እኔም ከተሰብሳቢዎቹ መሃል ነኝ።  ዶክተር ፍቅሬን ለማዳመጥ ከዲሲና አካባቢዎ ውጪ ለምትኖሩ በስልክ ቁጥር 218-862-1300 code 126285 በመደውል  ጥያቄም መጠየቅ ትችላላችሁ። ከአካባቢያችሁ ስልኩ ይሰራላችሁ እንደሆነ ለማውቅ በማንኛውም ቀን በመደውል ስልኩን ከእነ ኮዱ እንድትሙክሩት አሳስባለሁ።  

በምንይሻላል ላይ የቀረበ ማስትዋወቂያ።
ዛሬ ቀኑ በአሜሪካን አቆጣጠር፡ ማርች ሰላሳ አንድ ሁለትሺ አስራ ሶስት ነው።
የአንድ አገር ሕዝብ ያለፈውን ታሪኩን በደንብ ካላወቀ አንድነቱን ለመነደል ከሚመታበትና ከሚያጋጥመው የውጪም ይሁን የውስጥ ተቀጣሪ ጠላት መቁዋቁዋም አይችልም። በተለይም ኤትኒክ ሰግሪጌሽን ወይም የጎሳ ብሎም የብሄር ክልልን ለማጥፋት መድሃኒቱ ታሪክን ማወቅ ማለትም እራስን ማንነትን ማወቅ ነው። ስለሆነም የዛሬ የምንይሻላል ሬዲዮ ስርጭት በዚህ በኢትዮጵያውያን ማንነትና ታሪክ ላይ በተመሰረተ ትምህርታዊ ገለጻ በተጨባጭ ሊያበረክቱልን ይረዳን ዘንድ እንግዳ የጋበዝነው። ይሄም እንግዳ በብዙ ዘርፉ አይምሮውን በተግባር ላይ የማዋል ችሎታ ያለው፡ የመጀመሪያው በአሜሪካን አገር በአማርኛ የቴሌቪዥን ስርጭት የጀመረና ዋና አዘጋጅና አቅራቢ፡ ፊልምና ቲያትር ደራሲ፡ ተዋንያን ወይም አክተር፡ ፕሮዱሰርና ዳይሬክተርና ክራር እየመታ የአገሩን ታሪክ በሲዲ በሙሁር አቀራረብ ያቀረበ፡ የታሪክና የቁዋንቁዋ ምርምር  ብሎም የደራሲዎች ምርምር ፕሮፌሰርንና በተለያየ ቦታ በኢትዮጵያውያንም ይሁን በውጪ ሰዎች እየተጋበዘ በብዙ መድረክና አርእስት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና የሕዝብዋ ማንነት በመናገር ተሳታፊነቱን ያጠቃልላል። ስለሆነም በበኩሌ ባለ ሁለገብ አይምሮ በዚህ አገር አነጋገር መልቲ ፐርፐዝ ማይንድድ ብዬዋለሁ። 

በዛሬው እለት የምናቀርብላችሁ የቀኑ እንግዳችን "ቲኒሹ ልጅ ደራሲ" በሚል የኢትዮጵያ ቴሌቪዢንና ሬዲዮ የዛሬይቱ ኢትዮጵያና እነ አቶ በሁዋላ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እነ አቶ ከበደ እና ሌሎቹም ያደነቁት፡ በልጅነቱ በተፈጥሮ ችሎታው የተደነቀና በድርሰት በደራሲነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይምሮ ውስጥ ተቀርጾ የኖረና አሁንም ቀጥሎበ በመሃላችን የሚገኘውን፡ የአገሩን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያቆሽሽና የሚያዋርድ ሲነሳ ብሎም ሲመጣ በሙህርንት ጦር እየተዋጋ የኢትዮጵያን አንድነት በማስጠበቅ የታወቀው የታሪካችን አባትም ወንድማችንን ነው። በሌላ በኩል የሶቭየት ሙሁራን እሱን በሕይወት ሳያዩት ነገር ግን ድርሰቱን አንብበውና አይተው "የዛሬ አሌክሳንደር ፑሽኪን አገኘን" በሚል ስራዎቹን ወደ ሞስኮ ለላከው የኢትዮጵያና የሶቪየት ሕብረት ደራሲዎች መሃበር በመጻፍ "ወደ ሶቪየት ላኩልን በጣም ተስፋ ያለው ወጣት ስለሆነ ነጻ ትምህርት ልንሰጠው ወስነናል" በሚል በጠየቁት መሰረት፡ በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ጊዜ መሆኑ ነው እድሉ ተሰጥቶት ወደ ሞስኮው በመሄድ ሶስት ሺ ደራሲዎች ተወዳድረው አርባ አምስት ተማሪ ብቻ በመቀበል በሚታወቀው ትምህርት ቤት (ዩንቨርስቲ) ከአርባዎቹም አንደኛ በመሆን የከፍተኛውን ትምህርት ሊቀናጅ ችልዋል። መሬት ላራሹ በሚል ለሕዝቡ በቀዳምዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከሚታገሉት አንዱ እንደነበረ ቢታወቅም፡ የደርግ ስርዓት እሱ እንዳሰበው ሆኖ ባለማግኘት ወደ ጀርመን በመሄድ ዶክትሬት ድግሬዎን በእናት አገሩ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቁዋንቁዋ በአማርኛ አጥንቶ የዶክትሬት ማእረግ ደርስዋል። ይህ ወንድማችን ብዙ ኢትዮጵያዊ የታሪካችን ጠበቃና ወታደር በሚል የሚጠራው ብዙ ኢትዮጵያዊ በአገር ቤትም በውጪም በአለም ላይ በሚኖርበት ሁሉ ባያየው በነብስ ነገር ግን ስለአገሩ ታሪክ ጥብቅናና አስተማሪነት ስሙን የማያውቅ ብዙም የለም። ይሄውም ወንድማችን ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ይባላል። ስለ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ በዚህች አጭር የማስተዋወቂያ በተሰጠኝ ጊዜ ተናግሬ ልጨርሰው የምችለው አይደለም ልሞክረው ብል እንክዋን አዳጋች ነው ጥቂት ባለመሆኑ ባጭሩ መጸሃፍ ማንበብ ስለሚሆንብኝ ለዛሬ ለማስተውዋወቅ ያህል ለምንይሻላል ሬዲዮ አድማጮች ፡ ነደፍ ነደፍ በማድረግ ከተለያየ ማስረጃዎች የወሰድክዋቸውን ወይም ያገኘሁዋቸውን ፈልጌ ላቀርብ እወዳለሁ። እኔም የቀሰምኩትን ከሱ መጸሃፎችና ብዙ ጊዜ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ተሰምቶ የማናውቀው ታሪክ ጭምር እናንተም እንትጠቀሙ አድማጮች ስለጉዋጉዋሁ ጊዜውን ለአድማጮች ብቆጥብ እወዳለሁ። ሁኑም ከዚህ በታች በብእር የሻይ ማንክያ ያህል ጨልፍ አድርጌ የወሰድኩትን እነሆ።

በሶቪየት ሕብረት በአስራ ሰባት ዘጠኛ ዘጠኝ ተወልዶ በሰው እጅ በአስራ ስምንት መቶ ሰላሳ ሰባት ሕይወቱን ያጣው የኢትዮጵያዊነት ደም ያለው በኢትዮጵያዊነቱም የኮራ የነበረው ትልቁ የሶቪየት ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽክን በጊዜው ከደረሳቸው አንደኛ፡ ዘቴል ኦፍ ቤልኪን አስራ ስምንት ሰላሳ፡ ሶሻል ሳይኮሎጅካል ስቶርይ ና። ሁለተኛ፡ ኩዊን ኦፍ ስፓድስ አስራ ሰምንትመቶ ሰላሳ ሶስት፡፡ ሶስተኛ፡ ዘካፕቴንስ ዶውተር አስራ ሰምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ከደረሳቸው ጋር የሚወዳደርና እንደውም የሚበልጥ በሚል እራሳቸው የፑሽክንን ታሪክና አስተዋጽዎ ታሪኩ ያደረገው ሶቪየት የዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳንም የተፈጥሮ ችሎታና ጉብዝና ንቃትና ደፋርነት ሳይቀር በማህደራቸው አስቀምጠውት ይገኛል።

ዶክተር ፍቅሬ ድሬ ደዋ ከተማ ተወልዶ እዛው ከአንድ እስከ አስራሁለተኛ ክፍል እድሜው ገና ለሁለተኛ ደረጃ መጨረሻ ሳይደርስ በጠዋቱ ጨርሶ በጊዜው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በመግባት ትምህርቱን እየተከታተለ እያለ በድርሰት መጀመሪያ ድሬደዋ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ሁሉ ማለትም አገር አቀፍ በሚወዳደሩበት የድርሰት ውድድር ተወዳድሮ በአንደኝነት አሸንፋል። የሚደርሳቸው ሁሉ በጋዜጣ ላይ ለሕዝብ ከመቅረባቸውም በተጨማሪ ከእነ አቶ ከበደና አቶ ጸጋዬ ገብረመድህን እኩል በቴለቪዢን እየቀረበ ችሎታውን ለሕዝብ እንደገልጽ እየተጋበዘ በእድሜው ቲኒሽ ነገር ግን በችሎታው ትልቅ የነበረና ታሪኩን ኢትዮጵያ መዝግባለታለች በጊዜው በነበሩት ጎብዝ ኢትዮጵያዊያን ታዳጋ ወጣቶችን ወደ ሁዋላ ሳይሆን ወደ ፊት እንዲያድጉ ባህሪያቸው አድርገው በሚታወቁ ጥሩ ዜጎች። ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ በጀርመን አገር በሚማርበት ጊዜ ለአማርኛ ምርምር የሚረዱት የታሪክ ጥረዛ ወይም ማህደር በጊዜው እንብዛም ባይኖርም ኢትዮጵያ የሌላትንና በእያንዳንዱ የዓለም የታሪክ ክፍል ወይም መጽሃፍ መገኘት የነበረበትን ባለማግኘቱ ፡ ብዙ ይቆጭ ስለነበር ከሱ በሁዋላ ለሚመጣው ተማሪም ይሁን መርማሪ ወይም ታሪክ ጸሃፍ መንገዱን አቅልልዋል። ይሄውም አስፈላጊውን ሁሉ ከተደበቀበት ታሪካችንን እየበረበረ እያወጣ በሚገባ በማስቀመጥ።

ከላይ እንዳልኩት የዶክተር ፍቅሬን ታሪክና በቲንሽ እድሜው በደራሲነት ወደ ራሺያ የደራሲዎች አገርና የታሪክ ቤት ወደ ሆነችው ተመርጦ ከሶስሽ ሰዎች መሃል አሸንፎ ያውም በሰው ቁዋንቁዋ እዛው ሄዶ ተምሮ በሁዋላም እስከ ፔኤች ዲ መድረስ ማለት ብዙ የአማርኛ ቁዋንቁዋ መመርመሪያ ለፒኤች ዲመስሪያ በሌለበት በማይገኘብት ታሪካችንን እንደይገኝ ተደርጎ በሌላ በኩል የራሳችን አገር ሰዎችም ቢሆኑ በማወቅም ይሁን ባላማወቅ ታሪካችንን ከያለበት ፈልገው በአግባቡ ባለማስቀመጣቸው ያንን ሁሉ አርሞና ስረመሰረት አስቀምጦ በእራስ ቁዋንቁዋ ዶክትሬት ድግሪ መስራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትምህርቱ ውጣ ወርድ ውስጥ ያለፈው ሁሉ የሚያውቀው ነው አንደኛ ከጊዜው በፊት የነቃ ለመባል ያውም በአሮፓውያን።

ስለሆነም በቅርብ በታሪክ ብእሩ ከታገልው ብናስታውስ ፡ ኢትዮጵያና ሕዝብዋ ባጋጠመን የታሪክ ከዳተኞች እራሱ ሕዝቡና አገሪቱ ያስተማርዋችው፡ ከነዚህም መሃል ለገሰ ዜናዊ ወይም መልስ ዜናዊ የፋሲል ግንብ ለኦሮሞ ምኑ ነው እና የአክሱም ሃውልት ለጉራጌ ምኑነው? ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ ናሽናሊስት አይደለም ማለትም ብሄራዊ ስሜት አለው የሚባለው ውሸት ነው ለግሉ የቆመነው ለሚለው የመለስ አነጋገር ለውጪ ሰዎች በሰጠው የጥያቄ መልስ፡ አብዛኛው ከንፈሩን ሲመጥ በተለመደው ነገር ግን ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ይሄንን ሲረዳ ማንም ሳይሆን በጊዜው ግንባር ቀደም ሆኖ በማስረጃ ለመለስ ለራሱ ታሪኩን እንዲያውቅና ሕዝቡንም በመዳፈሩ ይቅርታ እንዲጠይቅ በግልጽ የጻፈለትና ደብዳቤውንም ብዙ ኢትዮጵያው ያነበበው ነው።

ዶክተር ፍቅሬ ከአርባ የበለጡ መጽሃፎችና ድርሰቶች በስራ ላይ ያዋለና አሁንም ለእትም የደረሱ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ ቀደም አግኝተንው የማናው ለማሳተም እየተዘጋጀ ነው እንደታተመ ግልጽ ያደርገዋል። ሆኖም ሁለት መጽሃፎች ይቺናት የኔ ምድር the Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians የሚለውን በኢሜል አድራሻቸው በመጻፍ ልታገኙ ስለምትችሉ ትልቅ ታሪክና ከተለመደው የብዙ ገጽ የተለየ ባጭሩ በሃምሳ ሶስት ገጽ የተጻፈ ነገር ግን ከአንድሺ ገጽ ያላነሰ መጽሃፍ ሊወጣው የሚችል ታሪክ በልዩ መልኩ ቶሎ ሕዝቡ ታሪኩን ማንበብ ሳይሰለቸው እንዲረዳና እንደገነዘብ አውቆም ለማያውቅ ታሪኩን አስተማሪ እንዲሆን በማሰብ የጻፈው በመሆኑ ሁላችንም እድለኞች ነን። ስለሆነም ገዝታችሁ ታሪካችሁን እንድታዳብሩ አሳስባለሁ። የሃሰት ታሪክ ለሚደቅኑብን ሁሉ አንድነታችንን ለማፍረስ መድሃኒቱ ሃቁን ይዞ መገኘት ብቻ ነው ከእነ ማስረጃው። ዶክተር ፍቅሬ በኢሜል አድራሻው ftolossa@aol.com በመጻፍ ብዙ ለማሳተምና ወደ ሕዝባችን እጅ እንዲገባ ለማድርግ ይረዳው ዘንድ ብሎም ወጪውን ያሳተመበትን እስካሁን ይሸፍንለት ዘንድ ይቺነች የኔምድር የሚለውን ግጥም አዘልዋን ድርሰት አስር ዶላርና the Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians አስራ አምስት ዶላር በመላክ በድምሩ በሃያአምስት የአሜሪካን ዶላር መጸሃፎቹን ታገኛላችሁ።

ዶክተር ፍቅሬን ልዩ ከሚያደርገው ነገሮች ባጭሩ። 
ዶክተር ፍቅሬ ወደ አሜሪካን አገር ከመጣ በሁዋላ ትዳር መስርቶ የልጅም አባት ነው። ባለቤቱ ዶክተር ማርታ አባተ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለአባቶች እርቅና ሰላም በጣም የምትጥርና በአቡነ መልከጻዲቅ የሚመራውንም ቤተክርስቲያንና ለአባታችን ለአቡነ መልከጻዲቅም ጭምር ታዛኝና አገልጋይ ነች። ወደ ፊት ስለእስዋና ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰላም እርቅን አስመልክቶ በግንባር ቀደምትነው የርቁ ኮሚቲ ጀማሪዎች በመሆናችን በዚህ ጉዳይ ተባባሪዎች ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ፡ ወይዘሮ ዶክተር ማርታ አባተንና ወይዘሮ ኤልሳቤት አብዲሳን በዚሁ ይሬዲዮ ስርጭት በእንግድነት የሚቀርቡበት እድል ይኖራል ብዬ አምናለሁ ይሄንን አስመልክቶ ለአዘጋጅና አቀራቢው ለአቶ አያሌው ብሩ በመተው ውሳኔውን፡ ዶክተር ፍቅሬን ማስተዋወቁን እዚህ ላይ እደመድምና በመጨረሻም ከዚህ በታች እንዳለው በእኔ በኩል በማቀርባቸው ጥያቂዎች አጠቃልላለውሁ።

በመጀመሪያ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ የምንይሻላላን ሳምታዊ የሬዲዮ ስርጭት ግብዣ ተቀብለህ ላለን የጎሳ ችግር መፍትሄ ይሆን ዘንድ ስለታሪካችን እንድታስረዳን ፍቃደኛ ሆነህ በሬዲዮ ዝግጅቱ ላይ ዛሬ በመቅረብህ በሁላችን ስም ሆኜ አመሰግናለሁ። ጥያቄዎቼ አንደኛ እስቲ ስለ ማራ ፡ ማጂ፡ ጅማና ዛሬ አማራ ኦሮሞ ትግሬ ጉራጌ ወዘተ ክልል የሚለው ጋር ግንኙነቱን ለሚወድህ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንድታብራራ እጠይቃለሁ።

ሁለተኛ፡ ኦሮሙኛ በጎጃምና በፋሲል ቤተመንግስት የነበረውን የስራ ቁዋንቁዋነት ላይ ገለጻ ብታደርግልን?
ወንድም አያሌው ቦታውን ላንተ እለቃለሁ አመሰግናለሁ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን የማስተዋወቁን እድል ስለሰጠህኝ።

Who Is Ethiop? Who is Melketsadik? Where do all ethnic names in Ethiopia including the name Amhara and Oromo came from? Dr. Fikre has all the answer for you. Know who you are and what your history is for real.

The following is copied from Ethiopia.org
"Tolossa, Ph. D., is a poet-playwright, critic, essayist and educator. His latest book entitled,The Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians, as well as his original songs that he himself has composed and plays on the Kirar, will be released soon to the public at large. His film in English, “Multi-colored Flowers” was featured with great resonance in the USA, Canada, Europe and Ethiopia. He has written extensively on Ethiopian history and culture for the past 20 years upholding the banner of Ethiopiansim high, finding common factors that united the peoples of Ethiopia at a time of identity crisis, historical confusion and denial. Dr.FikreTolossa has authored over forty published and unpublished articles and books in Amharic, German, English and Russian. He could be reached at: ftolossa@aol.com"

 





 
 

 





 
 


























































 

 


 





  
 

 


Monday, April 1, 2013

"የውጪው ሲኖዶስ ዋና መስሪያ ቤትና የፓትሪያርኩ መኖሪያን ያጠቃለለ ባስቸኩዋይ መሰራት አለብን"

የስዴተኛው ሲኖዶስ ዋና ጽሕፈት ቤትና የፓትሪያርካችን የብጹህ አቡነ መርቆሪዮስ መኖሪያን ለመስራት እንተባበር!!!!

ከየሐርርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)
ትክክለኛውን በስዴት የሚገኘውን በብጹህ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውን
ሲኖዶስ ፡ ሲኖዶሴ ብለው ምርጫቸው ካደረጉት ምእመናን
አንድዋና በዳላስ የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባል።
ፕሌኖ ቴክሳስ።

የውጪው ሲኖዶስና ፓትሪያርካችን ቁዋሚ ቦታ ስለሚያስፈልጋቸው ባስቸክዋይ እየተደረገ ላለው የገንዘብ መዋጮና ድጋፍ የዳላስ ፎርት ውርዝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ገነዘብ በማዋጣት እንደአቅማችን የግንባታው ገንቢ መሆን ይጠበቅብናል። ስለሆነም በተለይ ዳላስ ፎርት ውርዝ ለምትኖሩና በቅዱስ ሚካኤል ደብር የምታስቀድሱ  ታስታውሱ እንደሆነ አንድ ሚሊዮን ዶላር የቤተክርሲያኑን እዳ ከፈልን ተብሎ በመድረክ ላይ በጊዜው የነበረው የቤተክርስቲያኑ ሊቀምንበር ሲያስረዳን ያላጨበጨብን አልነበረንም። ቀጠልም አድርጎ በግራማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ተሹመው የሃያማኖታችን አባት በመሆን በውጪ ብዙ የኖሩት ብጹህ አቡነ ይስሃቅን የቤተክርስቲያኑ ሰገነት ላይ ተቀምጠው እንዳለ ለሳቸው የቤት ክራይ የሚከፍሉላቸው ጃማይካውያን ወገኖቻችንነንደሆኑና አቡኑ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረን። ሆኖም በተለመደው ዝም ከማለት ሌላ የቦርዱን መልክት ሰምቶ ለሃያማኖት አባታችንና ቤተክርስቲያኑም ቢሆን በሳቸው አባትነት ስር እንደነበረ የማይካድ ነው። ይሄውም የሃያማኖት አዋቂዎች የተባሉት በእንግድነት የመጡት በጥቅሉ እነ ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ ሳይቀሩ የሰሞት ነው ከእነም እመናኑ ማለት ነው ያየማይረሳ ሃቅ ነው። ሆኖም ብዙዎች ዝም ቢሉም ከዚህ በታች ያለውን እዛው ከምእመናኑ መሃል ተነስቼ ያልኩትንና ውጤቱን ልገልጽ እወዳለሁ ለሁሉም ጊዜ አለው እንደተባለው ዛሬ ደግሞ ካለፈው በመነሳት ለአሁኑ መልካም ስራ ይጠቅማል በሚል ነው ያለፈውን የማሳስባችሁ። ይሄውም ለእኔ ሳይሆን ለሁላችንም ስለምናምንበት ስለፈጠረን አምላክ ነው።

"ሻለቃ ክፍሌ፡ በጣም ያሳዝናል የሃይማኖታችንን አባት ሰገነት ላይ አስቀምጣችሁ ስለ አንድ ሚሊዮን ቤተክርስቲያን መግዛትና መክፈል ታወራላችሁ? ለመሆኑ ዋናው የሃይማኖታችን አስተማሪ አቡኑ ለቤት ኪራይ የሚከፍሉት አጥተው ጃማይካውያን እየከፈሉላቸው ነው ስትሉን ዛሬ ያሳዝናል። ጃማይካዎያን እየከፈሉላቸው እየተቸገሩ እንዴት ይኖራሉ እኛ ሁሉ እያለን? ለምን ይሄ ጉዳይ አልተነገረንም? ምንድነው ለቤተክርስቲያን ግንብ መግዛት የሃያማኖት አባቱ ያለሃሳብ የሚያገለግሉበት የሚኖሩበት መኖሪያ ሳይኖራቸው? አሁኑኑ ዛሬውኑ እዚህ ሁላችን ባለንበት ለአባታችን (አቡነ ይስሃቅ) ወራዊ ውጪ ከሕዝብ ሳይሆን በቀጥታ ከቤተክርስቲያኑ ከሚካኤልና ከሌሎችም ከተሞች ወጪ ተወስኖ እንዲላክላቸው እንዲወሰን አሳስባለሁ!!! ሕዝቡም ለቤተክርስቲያኑ ገንዘብ በመስጠት የአቡናችን በውጪ አገር ተወካያችን በመሆናቸው ጭምር ይሄን ተገንዘቦ አቡን ይስሃቅ በምድር ላይ ስለገንዘብ ፈጽሞ ስለ ቤትኪራይም ይሁንሌላ ወጪ ማሰብ አይገባቸውም!!"

ከላይ ያለውን ከእንባ ጋር ተናገርኩኝ። ያጥያቄ ነበር ለሃይማኖት አባታችን ለብጹህ አቡነ ይስሃቅ ደሞዝ ያስወሰነላቸውና ሌሎቹም የሃይማኖት አባቶች ደሞዝ አስፈላጊነቱ ልማድ ሆኖ ያስቀጠለው።

 አሁንም ዝም ብሎ መቀመጥ ሳይሆን ከሁላችንም የሚጠበቀው፡ ወይም ጥቂቶች በሚያዋጡትና በሚረዱት እሁድ እሁድ ቤተክርሲያን ተጠቃሚ መሆን ሳይሆን፡ ልክ ሞርጌጅ ወይም የቤት እዳ በእየወሩ ወይም መኪና እዳ በየወሩ እንደሚከፈለው ሁሉ ቅድሚያውን ለቤተክርስቲያን በመስጠት እንደእያቅማችን በምንችለው የፓትሪያርካችንን ወጪና ዋና የውጪው ሲኖዶስ መኖሪያ ከእነ ጽሕፈት ቤቱ ማሰራት ይገባናል። ለዚሁም እስክንጠራ መጠበቅ የለብንም እንዴት እራዳታ እንስጥ? ለማን ወዴት? የሚለውንና ቤተክርስቲያን በአካባቢያችን ያለን ደግሞ ለምሳሌ ለቅዱስ ሚካኤል ደብር ዳላስ ቦርድ የገንዘብ መዋጪ ዝግጅት የሚያዘጋጅ ኮሚቲ ባስቸክዋይ እንዲመርጡና ሁላችንም ተሳታፊ በመሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የስዴተኛው ሲኖዶስ ዋና ጽሕፈት ቤት ግንባታ ሃይል እንደንሆን አሳስባለሁ ። አሜን!!!