Monday, April 16, 2012

ከዋሽንግተን ኢትዮጵያውያን ለዳላስ ፎርት ውርዝ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ወገን እና አገር የእናድን የሕብረት ጥሪ!

ለወገኖቻችን ስቃይ እኛ ካልጮህን ማን?
ዛሬ ካልጮህንስ መቼ?
አዎ! የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለውን በደልና ስቃይ የእንግልቱ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን
በእየዕለቱ ከሚያሰሙን የድረሱልኝ ጥሪ በተጨማሪ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ይህንኑ የወገን ያለህ ጥሪ እየዘገቡት ይገኛሉ። ይህ
የህዝባችን ሲቃ እንዲያበቃ ደግሞ ዛሬ ልናደርግ ከሚገባን በርካታ ተግባራት መካከል በተባበረ ድምፅ ስቃዩና ማፈናቀሉ በኢትዮጵያውያኑ ላይ
በአስቸኳይ እንዲቆም ተባብረን የቁጣ ድምጻችንን ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ማሰማት አንዱ ጉዳያችን ነው ብለን እናምናለን። ስለዚህም
የአገዛዙ ደጋፊዎችና ቀለብ ሠፋሪዎች የሆኑ መንግስታት ለወያኔ እየሰጡት ባለው ድጋፍ በህዝባችን ላይ ምን እየተፈጸመ መሆኑን እንዲገነዘቡት
ለማድረግና ተቃውሞአችንንም ለመግለጽ፣ ለየተወካዮቻቸውም ማስረዳት አስፈላጊ ስለሆነ የመጀመሪያውን የተቃውሞ ድምፃችንን በዓለም
አቀፍ ደረጃ ልናሰማ ቀጠሮይዘናል። ዋሽንግተንም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ /ስቴት ዲፓርትመንት / በር ላይ ተቃውሟችንን እናደርጋለን።
በዚህም የተቃውሞ ሰልፍ ላይ፤

ህገውጥ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም፣
ከ 78 000 በላይ አራሽ ገበሬዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ የሃገራችን ክፍል አማራ በመሆናቸው ብቻ በጎሳ ፅዳት እየተፈናቀሉ ስለሆነ ይህ

ማፈናቀሉ ዛሬም ቀጥሎ በአፋር ህዝብ ላይ ያለው አዲስ ማፈናቀል በአስቸኳይ ቆሞ ነዋሪው ህዝብ ዋስትና እንዲያገኝ ለመጠየቅ፣
በተመሳሳይ ጥቃት ከ 70 000 በላይ የጋምቤላ ነዋሪዎች ተፈናቅለው መሬታቸው ለሳውዲ ቱጃሮች የመሸጡን ተግባር ለማውገዝና
የዓለም አብያተ ክርስቲያናትና ቅርስ ተንከባካቢ ድርጅቶች ጉዳዩን አውቀውት የመፍትሄ ርምጃ እንዲወስዱም ለመጠየቅ፣
ክርስትናን ከኢትዮጵያ ለመንቀል በዝቋላ፣ በአሰቦት ገዳማትና በሌሎቹም ላይ ሆን ተብሎ የሚለቀቀው እሳት በአስቸኳይ እንዲቆምና
ለማስገንዘብና ድርጊቱም በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፣
ያለፈቃዳቸው እንዲቀበሉ በአገዛዙ በተፈጠረባቸው ጫና እየተሰቃዩ መሆናቸውን ማጋለጥና ድርጊቱም እንዲቆም ለመጠየቅ፣
በዋልድባና በሌሎቹም ገዳማቶቻችን ላይ በልማት ስም ሃይማኖትና ቅርስ እንዴት እየተናደ እንደሆነ ለሚመለከተው ሁሉየእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን የራሴ የሚሉትን እምነታቸውን በሰላም እንዳያራምዱ፣ ይልቁንም መጤ ሃይማኖትን
የመቸብቸቡ ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፣
የህዝባችን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሀገራችን የነገ እጣ ፋንታ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፤ ጎሳ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ
እንዲሁም የቡድን ስሜት ሳያጥራችሁ፥ የመለየትን አጥርን አፍርሳችሁ፥ ስለወገኖቻችን መከራ ጊዜ አጣን ሳትሉ ለሁለትና ሦስት ሰዓት
ሁላችንም ወጥተን በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀመው ሰቆቃ እንዲያበቃ በአንድነት እንድንጮህላቸው ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቦታ ፤ ስቴት ዲፓርትመንት አድራሻ፤ 22ተኛውና (ሲ) ስትሪት ኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ዲሲ
ቀን፤ ሰኞ ሜይ 7 ቀን 2012 (እ.አ.አ) ሰዓት፤ ከጠዋቱ 9፡00 ኤ ኤም
የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ
በህዝባችን ላይ በአጠቃላይ እየተፈጸመ ያለውን ህገ ወጥ የመሬት ነጠቃ፣ የዘረፋ ሊዝ ፖሊሲና ኢትዮጵያን ለባዳን ኢንቬስተሮች ቁጥራቸው ከ35 ሺህ በላይ የሚሆኑት በወያኔ እሥር ቤቶች የሚማቅቁት ኢትዮጵያዊያንን ዓለም እንዲታደጋቸው ለማስገንዘብ፣ እና በየሃገራቱ ያለውን ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን የማንገላታት ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል።
የፓለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፡ ከ78,ኢትዮጵይውያን መፈናቀል፡ የዋልድባ ገዳም መጥፋት፡ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ችግር፤

ሚያዚያ 1 ቀን 2004 ዓ.ም