Monday, May 16, 2011

ይድረስ ለዳላስ ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር April 2011, አዲስ ተመራጮች በሙሉ።

መግቢያ፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል ባልደረቦችና በሲቪልም ሲያገለግል የነበሩትን ጭምር ከየመን ወደ አሜሪካን ከአስራ ሶስት አመት ስቃይ በሁዋላ ከእነ ቤተሰቦቻቸው እንዲመጡ ስለተሰሩ ተግባሮችን አስመልክት የሚቀጥለውን ብሎግ እንዲጎበኙ እንጠይቃለን http://www.formerethiopiannavy.blogspot.com/


MAAEC: እህቶች ወንድሞች እንክዋን ደስ ያላችሁ!
አዲሱ ስራችሁ እንዲሳካ ይህ በህዝብ ጥያቄ የተመሰረተው የዳላስ ፍርት ወርዝ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የሃቅ ድምጽና ለሕዝቡ ጥቅም የሚያገለግል ብሎግ ትልቅ ምኞቱን በርቱ በማለት ይገልጻል።

ከዚህ በታች ያለውን ካላወቃችሁ በሰላም ስራ ችሁን ልትሰሩ አትችሉም ያስቸግርዋችሁዋል የለቀቁት በሌሎች ምላስ እየተናገሩና እየቀረቡ አንዱም ምላሳቸው መሃላችሁ ነው የእውነት ዶክተር ምላሱን እስካላከመለት ድረስ  ነው። ከዝህ በታች ያለውን ሃቅ እስካልተገነዘባችሁ ሕዝብ አስተባብራችሁ ውጤት ያለው ስራ ለመስራት አትችሉም ከማስረጃ ይልቅ ምላስ የሚያሳምናቸው በተነገራቸው ብዙ በሳሶቻቸው ሊያሰለችዋችሁና ሊያሳስትዋችሁም ስለተሰማሩ። ምልክቱ እነ እከሌ ተገለዋል እነ እክሌ ከቦርዱ ያስወጣናቸው ገንዘብ ወስደው ነው ወዘተ በሚል ጭምር ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ከመረዳጃ ማሕበሩ ለቀውልቸው የወጡት ሁለት ሰዎች አቶ ውድነህም ይሁን አቶ ንጉሴ ጋረድ አንድም ገንዘብ እንዳልወሰዱና ገንዘብ ወጪ ለክስ ፈርሙ በሚል እኔ ሳልከስ ከሳናላች ብለው የጠበቃ ወረቀት ለእኔ አጽፈው ልክ ፍርድ ቤት ጉዳይ እንዳለ በማስመሰል ለሕዝቡ በሬዲዮን ሊያነቡና  እያንዳንዳቸው ሚሊየነር ለመሆን ዘርግተውት የነበረውን ዘዴ ለመቀጠል እንዲያስችላቸው የፈለጉት ገንዘብ በሁለት ገንዝብ ወጪና ገቢ በሚመለከታችው በእነ አቶ ንጉሴ አስፈርመው ሊያውጡት ያቀዱት ለእነበትሩ ፡ ፍቅረማሪያምና ኪዳኔ አለማየሁ ለተባለው ስላልሆነ ብቻ ነው።

ሃቁን አንብባችሁ ስትረዱ አብዛው ሕዝብ በእጄ ይሄንን ሃቅ በጊዜው ያሳየሁውቸው እንዳሉኝ "ክሰሻቸው አሳስሪያቸው!" እንዳሉኝ እናንተም አይምሮ ተመሳሳይ ሃሰብ ሊመጣባችሁ ይችል ይሆናል በእኔ ላይና በመረዳጃ ማሕበሩ በደረሰው በመቆጨት ነገር ግን እኔ እነሱን መክሰሱን ጠፍቶኝ ሳይሆን በጊዜው ያውም አምስት ሳንትም ሳላወጣ ላደርግ የምችለውን እስከዛሬ ጉዳዩን እየታገልኩዋቸው የቆየሁብት መክኒያት በጊዜው ባስይዛቸው ኖሮ ከሁውላ የሰሩት ብዙ ወንጀል ስላለ ከሃያ አመት ያላነሰ እስር ሊፈረድባቸው ስለሚችል ለልጆቻቸውና ለሚስቶቻቸው በማሰብ ሲሆን ሌላው ከሰባሺ ዶላር የበለጠ በተፈራ ውርቅና በግብረአበሮቹ እጅ ስለነበረ ከሰሰችኝ ብለው ሊወስዱት ስለነበረ የመረዳጃ ማሕበሩን ገንዘብም ላለማባከን ጭምር ስለነበረ ይሄንን ክወዲሁ እንድትረድት አሳስባለሁ። በዚህ ምልኩ ይህንን ከሕዝቡ ጋር የምትጋሩትን ግልጽ ምልእክት በዚህ መልክ የማስተላልፍላችሁ የመረዳጃው ሬዲዮኑ የአማርኛው ዝግጅት በዝወገና በግብረ አበሮቹ ብእነሱው እጅ በመሆኑ አሁንም እስክትረከቡ ድረስ አማራጩ ይሄው ሆኖ ስለተገኘ ነው። ደብዳቤ በጋሻ-ኒያላ ኢንሹራንስ አድራሻ እድር በሚል ባስቀመጥዋት ተወካያቸው ለመስጠት ተሞክሮ ነበር ያም አልሆነም።


ከጅቦች መንጋጋ መረዳጃ ማሕበሩን ነጻ ለማውጣትና ሕብረተሰቡም በትብብር የራሱን ማሕበር አስከብሮ በትክክል በሚሰራ አመራር ለመተካት የተደረገውንም ጥረት ብሎም በመሃበሩ ስም ብዙ የከብሩና ለመክብርም የሚርዋርዋጡ ችግረኛም ኢትዮጵያዊ  እርዳታ ሲጠይቃቸው እያባረሩ ላለፈው አስራሃንድ አመት በተለይ እንደኖሩት ሳይሆን፡  እናንተን ያስመረጠው  አስመራጭ ኮሚቴ ለማስመረጥ ስራው እንዴት እንደተሰራና እስከ መጨረሻ ግለሰቦች ተጠቁማችሁ ምርጫው ተጠናቆ እናንተም እንዴት ልትረከቡ እንደቻላችሁ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን ወደ ፊት ለሁሉም ጊዜ ስላለው የሚቀርብና ግልጽ የሚሆንብት ጊዜ ይመጣል። ሆኖም እንድትገነዘቡት የሚያስፈልገው ለአሁን እነዚህ ግዜያቸው ባለፈ በአምስት ወር በጉልበታቸው የወሰዱትን ስልጣንና መረዳጃ ማሕበር እንዲያስርረቡ ትልቅ ቅስቀስና ጥሪ ለሕብረተሰቡ በማድረግ ይሄ ብሎግ ትልቅ ግንባር ቀደም በመሆን ላለፈው ስድስት አመት የተደረገውን ትግል ጭምር እያስገነዘበ በማስረጃ ጭምር በፊደል የማይለካ ግዙፍ ስራ ሰርትዋል። በዚህ አጋጣሚ የብልጉን ተጠሪዎች ማንነት ባላውቅም የዳላስ ኢኦቲሲ ብሎግም የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ሕዝቡ እንዲረከብ በተደረገው ዘመቻ ትልቅ አስተዋጽኦና ሚና ተጫውትዋል።

መረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶ እንደነበረ ታውቃላችሁ?
 ሆኖም አስመራጭ ኮሜቴም ለመምረጥም ይሁን ቦርድ አስመርጦ ለማስቀመጥ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ በመኖሩ ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብር  ተገድሎ ከተቀበረበት ለማውጣት   የተደረገውን ትግል በተጨባጭ ካሁኑ በመንግስት ማስረጃ ደረጃ መገንዘቡ፡ በሃሰት ለሚያስረክብዋችሁ የፈጠራ ወረቀቶች ማለትም በእርሳቸው በተለመደው የተቀነባበረ ከሕብረተሰቡ የሚያጋጭ ወረቀት መሳሪያ እንዳያደርጉዋችሁና ለምሳሌ ሶስት ግለሰቦች ከመረዳጃው ቦርድ በመረረ ሁኔታ እንዲ ወጡ አድርገዋል። እኔንም ቢሆን እርምጃ ወሰድንባት ብለዋል። በእርግጥ ሌቦችና አጭበርባሪዎች ዋና መኖሪያ ሙያቸው አድርገው የሚኖሩ ይቅርና ፕሬዘደንት ኦባም አንድን ሰው ከመንግስታዊ በሕግ ከታወቀ መረዳጃ እንደ የግል ቤት ወይም ምግብ ቤት አትምጣ ብለው የመወሰንም ይሁን የማግለልም መብት የላቸውም።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩና የሬዲዮ ስርጪቱን: የቅዱስ ሚካኤልን ደብር እናድን! የሚለው ጥሪ ወንጀል አልነበረም የተዘጋውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ብዙ መስዋት የተከፈለበትን የስዴተኛውን ማሕበር ከተቀበረበት መልሶ ለማስከፈትና የሕዝብ ማሕበርነቱን ለማስከበር እንጂ።

መረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶ የነበረበት ማስረጃ፡

office of the Secretary of State  ስድስት ወር ጠብቆ መልስ ሲያጣ ኦገስት ሃያዘጠኝ (August 29, 2007) መረዳጃ ማሕበሩ ሕጋዊነቱን ማጣቱንና መፍረሱን ይፋ ያደረገበት ምስክር። በሕጉ በዚህን ጊዜ ማንም ሰው የመሃበሩን ስም እንዳለ እንደ አዲስ በማስመዝገብ የመውሰድ መብት ስላለው በማቸው አዛውረው ማንም ያገባኛል ቢል ወይም ሕብረተሰባችን መብት አይኖረውም ነበር። ሆኖም ያሁሉ ውርጂብኝ ቢደርስብኝም የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብሩን ይመኑ ነጋና እኔ ከጥንሥሡ ጀምረን ያሳደግነውን የስዴተኛውን ድርጅት በአንድ አምላክ ፍቃድና በጸናው እምነቴ ከቀማኞች ጉሮሮ አውጥቼ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን የሕዝብ መረዳጃ ማሕበርነቱን በማስከበሬ ሕዝቡ ደግሞ መረዳጃዬ ብሎ ሲነግዱበትና ደሙን ሲጠቡት ከኖሩት መዳፍ አውጥቶ ለእናንተ ወገኔ ትሰራላችሁ በሃቅ አንድነትም በዳላስ ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ታሰፍናላችሁ ብሎ ያመነባችሁን  የሃላፊነቱ ስገነት ላይ ሊያስቀምጣችሁ ችልዋል።

































  ታግ ያቸው ሕዝቡም በእኔ ላይ በሬዲዮ ያስተላለፉት ሁሉ የረጂም ጊዜ ሃብት መሰብስቢያቸውን መረብ ስላጠፍክባቸው መሆኑን ተረድቶ፡ የታለ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ቴረሪስት ብላ ከሰሰች የምትሉበት የፍርድ ቤት ወረቀት? የታለ እናንተንስ ቴረሪስት ብላ ክሳናለች ለአሜሪካን መንግስት ጭምር የምትሉት ማስረጃችሁ? የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ልታፈርስ ነው ያላችሁት ማስረጃ አምጡ? የሚልና ሌላም ሌላም ጥያቄ እያየለ ሲሄድ እኔም ወደ ሁዋላ ሳልል አምላክን ይዤ በመጉዋዜ በመጨረሻም መረዳጃ ማሕበሩ ሕጋዊነቱን ሆነ ብለው ባፈረሱት ከአንድ አምት ከአንድ ወር ከአስራ አራት  ቀን በሁዋል ነበር በ Sep.15, 2008 መልሶ ሕጋዊነቱን የተጎናጸፈው።




የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ በሕይወት እንዳለ በማስመስል ስሙን የፓስታሳጥኑን ቁጥር ጨምረው በዚህ መልኩ እድር ሲያስተዋውቁና ሲሸጡ  መረዳጃው አልነበረም ገለው ቀብረውት ነበር። የእድሩንመተዳደሪያ አስራ ሁለተኛ ገጽ ብታነቡት ቅድመ ዝግጁ በመምሰል መረዳጃውን ያላፈረሱ ለማስመስል የተጫወቱትን "Article-12 Disbanding"  ብትመለከቱ ቁልጭ ብሎ ይታያል መረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶዋል ለማለት መወሰናቸውን ግባቸውን ከመቱ በሁዋላ።
ዲሲምበር ሃያሶስት ሁለትሺ ሰባት በአሜሪካን አቆጣጠር መረዳጃ ማሕበሩ ሕጋዊ አልነበረም በሌለ ማህበር ስም ነበር ባለ ማህበር ብለው ስማቸውን ያስቀመጡት።                                                                                                                       
አፍራሾች ዘውገ ቃኘውና የጥቅም ተካፋዮቹ የመሕበሩ ገንቢ መስለው የቀረቡበት ይውሸት ድግስ።
ከዚህ በታች ስማችውን በዲሴምበር ሃያ ሶስት ሁለትሺ ሰባት በማስቀመጥ፡ የወንጀለኞቹ ተባባሪ በመሆን፡ የጋራ  መረዳጃ ማሕበሩ እንደፈረሰ እንዲቀርና በእድር ስም ነገር ግን በጋሻ ኢንሹራንስ ዋና ስሙ ኒያላ አዲስ አበባ ንዋሪ ኢንሹራንስ በአሜሪካን በማንኛውም ከተማ ፍቃድ በሌለው እንዲተካ ከግል ጥቅማቸው አንጻር ብቻ በማየት መሃበሩን ለማዳን የተደረገውን ትግል ለማኮላሸት ትልቅ ወንጀል ፈጽመዋል። በአሜሪካን አገር ቁጭ ብለው በእኔም ላይ "በተገኙበት!" በሚል ማህበሩን በማዳኔ በሬዲዮን ያስተላለፉት የግድያ መልእክት በሕግ የሚያስጠይቃቸው ነው። እኔስ ስህተታቸውና ወንጅላቸውን በማስረጃ አቅሬባለሁ የአሜሪካን ምንግስት እጅ ከሚገኘው፡ ለመሆኑ እነሱ ምን ማስረጃ ይዘው ነው ይሄንን ሁሉ በሃሰት የትብብር ስም ማጥፋት ላይ ቆመው በጠቅላላ ጎባ ውሳኔ ከዚህ በታች ስማችን አስቀምጠው በውሳኔው ተባብረናል ያሉት?
የኢትዮጵያ የጋራ መርዳጃ ማሕበርንና የሬዲዮን ስርጭቱን በማዳኔና ዘውገ ቃኘው የወንጀል ስራ ቁንጮና ሌላው ከፊት ሆኖ ከሁዋላ ያሉትን ስራ አስፈጻሚው ሻለቃ ተፈራ ወርቅ የተባለው ከቦታቸው ይልቀቁ በማለቴ በሃሰት የአብዬን ወደ እምዬ እንደተባለው ወንጅለኞቹና አጋሮቻቸው ፈረድን ያሉት ማስረጃ ከዚህ በታች እነሆ።

መረዳጃ ማሕበሩን ባፈረሱት በአምስተኛ ወሩ ልክ እንዳለ አስመስለው እሬዲዮንም ጭምር ተጠቅመው እራሳቸውን የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ መሪዎች ብለው በሕዝብ ያልተመረጡ በጴንጤናዊው  ኮልኔል የትናንቱ የሌለ መረዳጃ ማሕበር ምክትል ፕሬዘደንት፡ ዛሬ የእድር ፕሬዘደንት ተብዬው በሃሰት ስድስት ውሳኔ በእሱና በተፈራ ወርቅ አሰፋ፡ በትሩ ገብርእግዚአብሄር፡ ኪዳኔ አለማየሁ፡  ዘውገ ቃኘው፡ ፍቅረማሪያም ደረስ፡ አመሃ ገብረሚካኤል (ታምሩ) እራሄል የ. ታደሰ፡ ስጦታው በላይ ተቀነባብሮል የፈረመውን ተመልከቱ። ይህ የካንግሩ ፍርድ ቤትና ካንጋሩዎች የፈረዱት ከላይ እስከታች በሃሰት የተቀነባበረ በአሜሪካን አቆጣጠር በ12-23-2007 ሲሆን መረዳጃ ማሕበሩን ባፈረሱት በአምስተኛው ወር ነው በሌለ መረዳጃ ማሕበር ሕጋዊነቱን ባፈረሱት መሆኑ ነው። ስማቸውን ከላይ አስፍረው  ውስኔ ላይ ተስማማን ያሉት መህል ብዙ ወንጀለኞች በስዴተኛው ስም ወደ ዳላስ የገቡና ዘመዶቻቸውን ያስመጡ፡ በስዴተኛው የሚነግድና ስማግል እያደርጉም በደላላነት ጭምር የሚሰሩ ጭምር ይገኙበታል። ያም ሚስጥር ሊጋፈጥ ነው ብለው እነዘውገ ደጋፊ ለማብዛት በፈጠሩት ዘዴ በማስተባበር ያዘጋጁዋቸው መሆናቸው ነው። አስታውሱ የእኔ ጥያቄ ተፈራ ወርቅ ከጋራ መረዳጃ ማሕበሩ ዘወገ ቃኘው ከመረዳጃውር ኤዲዮን ከእነ ተሳቢዎቹ ይልቀቁ መረዳጃ ማሕበሩን፡ የሪዲዮ ስርጭቱንና የቅዱስ ሚካኤል ደብርን እናድን ነበር ጥያቄዬ። ሆኖም ከእንዘውገ ቃኘው ጋር የተባበሩት በእኔ ላይ ሳይጠሩ ያገባናል ብለው በወንጀልና በማጭበርበር ስራቸው ድምጽ እየጮሁ ባደረጉት ትብብር መክንያት ምነው ቀፎ የሌለው ንብ ሆነው ጥዝዝዝዝዝዝዝ!! ሲሉ ሥሰማቸው ገርሞኝ ስለእነሱ ሳጣራ ባሁን ጊዚ መጻፍ የማልፈልገው ቢሆንም ባጭሩ ሴቶቹም ወንዶቹም የሚያባንን፡ እንቅልፍ የሚነሳና የሚያሳቅቅ ታሪክና ስራም ብለው በጎን የሚትዳደሩበት ዘግናኝ በምድርም በእግዚአብሄርም ፊት ከሞቱም በሁዋላ ገና ገሃነም እሳት የሚያገባቸውን ጉድጉዋድ በራሳቸው ላይ ቆፍረው ተሸክመው የሚሄዱ መሆኑን ልረዳ ችያለሁ። በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ የተባልውም በነሱ ላይ በሚገባ ሰርትዋል። በበኩሊ ሰርተው የሚኖሩ እንደአብዛኛዎቻችን የሚኖሩ ኔው በሃቅ በልባቸው የምላቸው ሁሉ ሰርተው ሳይሆን በወንጀል የሚኖሩ መሆናቸውንም በመረዳቴ በጣም በጣም አዝኛለሁ። እንግዲህ ስራ ፈት እያሉ ሲሳደቡና ሬዲዮ ተዘጋብን፡ ቴረሪስት ተብሎ የኢትዮጵያ የጋራ ምረዳጃ ማሕበር ተከሰሰ በሚል በሳምንት እሁድ እሁድ በተከታታይ ቀንና ማታ የፍየል ወጠጤ ያወረዱት ውሸት መረዳጃ ማሕበሩን ገድለውት ቀብረውት መቃብሩ ላይ  በኢንሹራንስ ስም እድር ብለው ዛፍ ሊተክሉበት ሲሉ ስላቆምኩዋቸው ብቻ ነው።

እድሩን ሁላችንም እንደግፋለን እንደማንኛውም እድር ነገር ግን ከመረዳጃ ማሕበሩ ጋር በሕግ ያልተገናኘ መሆኑንንና ሕጋዊ የሆነ ማስረጃ ፈጽሞ በማንኛውም መልክ የለውም የተባለውንም ሃቅ በመሆኑ ግልጹን ተናግሮ እድሩ እንዳለ ሆኖ በበለጠም የሚያድግበት መንገድም ስላለ ባመቻችሁ ጊዜ በስብሰባ መነጋገር ይቻላል። እዱርን በትብብር በትክክለኛው መንግድ አሳድገን ለመረዳጃው ማሕበርም የሚጠቅምበት ሕጋዊ መንገድ ስላለ ችግር የለም በጠረቤዛ ዙሪያ የሚገለጽ ይሁናል።

ከዚህ በላይ እንዳያችሁት ስድስት ነጥብ የያዘ ውሳኔ በመረዳጃ ማሕበሩ ስም ያስተላለፉት ተስማምተናል ያሉትም ጭምር የእነሱን ስራ በተግባር የሚያሳይ የማሕበራችንን አፍራሽነታቸውን ስለሆነ፡ በሙሉ ዘውገ ቃኘው፡ ይልማ ዘር ይሁን የተባለው ጭምር በሬዲዮን ሬዲዮ አዘጋች፡ መረዳጃ ማሕበሩን ልታፈርስ ነው፡ ቴረሪስት ብላ ከሳለች ማሕበሩን እኛንም በሚል ጭምር አቀነባብረው ያቀረቡት ሃሰት በመሆኑና ያስተላለፉት ሁሉ ፈጽሞ ሃሰትና የእነሱን አፍራሽንት ስራ እንጂ የእኔን የማህብሩን የገንቢዋን ስላልሆነ ይቅራ ሕብረተሰቡን እንዲጠይቁ።

አቤቱ አምላክ ሆይ፡ አትስረቅ፡ በሃሰት አትመስክር ያልከውን ትእዛዝህን ተከታዮችና አፍቃሪ እንጂ፡ ለግል ጥቅም ሕዝብን በማጋጨት በሃሰት ወገንን ከመከፋፈል በሃሰት ከመመስክርና አጨበርብሮ ከመኖር ሱሰኝነት ጠብቀን። እያጭበረበሩ የገንዘብ ተገዢ ሆነው የተካለበና የተደናገጠ ሳይተኙ በህልማቸው መጥቶ ፓሊስ የያዛቸው ወይም ኤፍ ቢአይ ብሎም ሆምላንድ ሴኩሪቲ እየመሰላቸው ከወገናቸው ጋር የሚጋጩትን የሃቅ ስራ ሰርተው እንዲኖሩና የሰላም እንቅልፍ ህልም ባለቤትነትን አውርሳቸው። ኢትዮጵያዊ ባዩ ቁጥርም አንገታቸውን ከመድፋትና ባለቤቶቻቸውንና ልጆቻቸውንም ከማሳፈር ነጻ አድርጋቸው። አሜን!!!