Monday, April 18, 2011

Thank you ESFANA! Yeharerwerk Gashaw

ሰዎች ጥሩ ሲሰሩም መመስግን ይገባቸዋል።

ይድረስ  ለመላው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም አውታሮች። ሰዎች ሲሳሳቱ ብቻ ሳይህን ሲሳሳቱ ብቻ ሳይሆን ስለ ስህተታቸው እየተጠቀስ መውቀስ : ጥሩም ሲሰሩ ማመስገን ተገቢና የዴሞክራሲም አስተስሰብ ነው። ስለሆነም ታዲያ ኢስፋና ባንድ ድምጽ ዳኛ ብርቱካንን ለመጋበዝ ሲወስን ምነው ዝም አላችሁ? ይሄ የዴሞክራሲ አሰራርን የተከተለ ስለሆነ ውሳኔው ልናመሰግናቸው ይገባል ወንድሞቻችንን።

ይድረስ ለኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን ምስጋና ወይዘሮ/ዳኛ ብርትኩዋንን የዚህ አመት የክብር እንግዳ አድርጋችሁ ስለመረጣችሁዋቸው። dfwethiopiancommunity.blogspot.com  የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ድህረ ገጽና በራሴም ስም እግዚአብሄር ይስጣችሁ በሚል ምስጋናዬን ዳኛ ብርቱካንን ስለጋበዛችሁ አቀርባለሁ። ልጃቸውን እንደምትጋብዝዋትም እተማመናለሁ። እንዲሁም አዲስ ቡድን ዳላስና ዳላስ ቡድንም የከተማችን ልጆች አበጃችሁ! እላለሁ።
የሐረርወርቅ ጋሻው።

ዛሪ ኤፕሪል አስራ ዘጠኝ የታከለ።
በዚህ አጋጣሚ በአትላንታ ላለፈው አስራ ሁለት አመት የተዋህዶ ድምጽ በሚል በየሳምንት የሬዲዮ ስርጭትና ዝግጅት የሚያቀርቡትን መላአከ ስላም ኤፍሬምን በጣም አመሰግናለሁ። ይሄውም አንደኛ ስለ ፈደሬሽኑ በማሰብ እንዳይፈርስና ወይም ግለስቦች እንዳይወስዱት እንደዚሁም በሰላማዊ መንገድ የፈደሬሽኑን ቦርድ ማነጋገር ሲገባ "ፈደሬሽኑ ይፍረስ!" የሚሉትን ሳይፈሩ በሬዲዮ ስርጭታቸው በመቁዋቁዋም ያደረጉትና ለዚህም እንደረዳ እኔንም በ ዲሴምበር አስራ ዘጠኝ አቅርበውኝ ከዳላስ ስለ ፈደሬሽኑ መኖርና ስለ ዳኛ ብርቱካንም መጋበዝ ቦታ ሰጥተው እንዲጋበዙና  ፈደሬሽኑንም አደጋ እንዳይድርስበት ሕብረተሰቡን ያሳሰቡ በመሆናቸው ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።
የሐረርወርቅ ጋሻው።



ከዚህ በታች ያለው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ለኢስፋና ወደ ስድስት ወር ገደማ የተላከናለቦርድና ለቡድን ተወካዮች በሙሉ የደረሳቸው ደብዳቤ ነበር።

Sent: Mon, Nov 22, 2010 7:22 pm


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ከግልጥቅም ነጻ ሆኖ በቴክሳስ የተመዘገበና ሕጋዊ የስዴት መንግስት ነው። በበለጠ ለመረዳት ከዚህ በታች ያለውን ዌብ ሳይት እንዲጉብኙ እንጋብዝዎታለን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ዳላስ ቴክሳስ አሜሪካ።  
(http://www.ethiopiannationalgovernmentinexile.org/)








ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የ2011 በኢስፋና የክብር እንግዳ ሆነው መጋበዝ ትክክለኛና ሕጋዊም ነው።
ግልጽ ደብዳቤ።
Nov 22, 2010 በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት የከበረ ስላምታ ለኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ አመራር (board) አባላት፡ የቡድን ተወካዮችና ቡድኖች ከነሙሉ ተጫዋቾቻው በሙሉ ሲያቀርብ ከልብ በኢትዮጵያዊነት አክብሮት ነው።
የተከበራችሁ ወንዴሞች ሆይ፡ ይችን አጭር ደብዳቤ ለመላክ ያስደገደንና የኛንም ጊዜ ውስደን የእናንተንም ወርቅማ ጌዜ ልንሻማ ያነሳሳን ዋና መክኒያት፡ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። ይሄውም በመጀመሪያ የሁላችንም እህት የሆኑትን ወይዘሮ (ት) ብርቱካን ሚደቅሳን ለሁለት ሺ አስረሃንድ (2011) የክብር እንግዳ አድርጋችሁ ለመጋብዝ የኢስፋና ቦርደ በድምጽ ብልጫ ዴሞክራቲካል በሆነ በሰለጠነው አሰራር የወሰናችሁትን ውሳኔ ስንሰማ በጣም ትልቅ ደስታ ነበር የተሰማን። ብዙም ሳይቆይ ሃሳባችሁ መቀልብሱን ስንሰማ ደግሞ ሃሳባችሁን የለወጣችሁበትን መክኒያት ማጣራት ግዴታ ስለሆነና ትክክለኛም አሰራር በመሆኑ ማጣራት ጀመርን። በመጨረሻም ወይዘሮ ብርቱካንን እንዳይጋበዙ መክኒያት የሆነው ስህተት እንዳለው ስንረዳ፡ መጀመሪያ ወደ ተስማማችሁበት ውሳኔ እንድትመለሱ ልናሳስባችሁ ወሰንን። ስለ ዚህ በትህትና የምናሳስባችሁና የምንጠይቃችሁ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን ቢቻል ከእነ አራት አመት ልጃቸውና እናታቸው ጭምር እንድትጋብዙ እያሳሰብን አለዚያም ወይዘሮ ብርቱካንን ብቻ በመጋበዝ መጀመሪያ እንደተነገረው  የኢትዮጵያ ሕዝብ የክብር እንግድነቱ ቦታ ለማንም ሳይሰጥ ፡ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን የ2011 የኢስፋና የክብር እንግዳ ማለትም የዲያስፓራው ኢትዮጵያዊ እንግዳ አድርጋችሁ ከኢትዮጵያ እንድታመጥዋቸው በትልቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ውይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን መጋበዝ በክብር እንግድነት ከኢስፋና ባይሎ መተዳደሪያ ጋር ይጋጫል  ለምትሉት ወንድሞቻችን ማለትና ማካፈል የምንፈልገው ፡ ያሳሰባችሁን ሕጋዊ ጥያቄ አስመልክቶ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። እህታችን ወጣትዋ ወይዘሮ ብርቱካን በክብር እንግዳነት ሊጋበዙ፡ ይገባቸዋልም በሚል ጥያቂያችንን ስናቀርብ ከላይ እንደገለጽነው፡ በኛም በኩል ማለትም በኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስትም (በኢትዮጵያ ሴቶች የተቁዋቁዋመ) የፓለቲካ ጥያቄ ሳይሆን ሕግን የአሜሪካንን ከግል ጥቅም ነጻ ድርጅቶችን ስርአት በመከተል በትክክለ ሕግ ተከተለን ሲሆን፡ በመሆኑም ከፓለቲክ ጋር ጥያቄያችንን እንደማታይይዙትም በመተማመን ነው። የወይዘሮ ብርቱካን በክብር እንግድነት በኢስፋና መጋበዝ ፈጽሞ በአሜሪካን ከ501 (c)(3) ጋር የሚጋጭ አይደለም። ለዚህም ብዙ ማስረጃና ገለጻ ከጠየቃችሁን ልናቀርብ ዝግጁነን። ሆኖም ለዛሬ ባጭሩ ለመግለጽ ያህል ማለት የምንወደው፡ የእስፓርት በአል ላይ ማንኛውም ገለሰብ ወይም የመንግስት አካል ብሎም የፓለቲካ ፓርቲ መሪ ቢጋበዝ 501 (c)(3) ፈጽሞ አይከለክልም። እንደዚህም አይነት የሕግ ድንግጋት የለውም። ማንም ሰው እንዲጋበዝ ይፈቀዳል እንደውም በፓለቲካ፡ በጾታ፡ በብሄር ወይም ጎሳና ሃይማኖት ልዩነት እንዳይኖር ነው የሚለው። የፓለቲካ ፓርቲ መሪናቸው ወይዘሮ ብርቱካን ስለዚህ በክብር እንግድነት ከአዲስ አበባ ጋብዘን በግልጽ ልናመጣ አንችልም የሚለው መክኒያት፡ ከናካቴው እህታችንን ድስክርሚኔት አደረጋችሁ ማለት ነው። ኢስፋናን የሚያስጠይቅ ይሆናልማለት ነው። የምትጋብዝዋቸው ፓለቲክ ሊያወሩ ሳይሆን የእስፓርት በአላችሁ የሕዝብም በመሆኑ በቦታው በታዋቂነታቸው ብዙም ሕዝብ ስለሚወዳቸው በሕዝብ መሃል ተገኝተው የበአሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ብቻ ነው። መረሳትም የሌለበት ኢስፋናን ሕዝባዊና ከግል ጥቅምና ከጾታ፡ ከሃይማኖት፡ ከፓለቲካ ልዩነት የሌለው ድርጅት እንዲሆንና ግለሰቦች የግል መጠቀሚያ አድርገውት የጥቂቶች አድርገው በሚሰሩበት ጊዜ የዚህን አይነት ችግር በመፈጠሩ ነበር ከግል ጥቅም ነጻና በሕጋዊ ሕዝባዊ እውቅና እንዲኖረው ታግለን የሕዝብ ያደረግነው ሴቶቹ። ምን ማለት እንደፈለግን http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ ግቡና ትናንትና የወጣውን ብታዩት እንዴት ኢስፋና ሕዝባዊ ዴርጅት ሊሆን እንደ ቻለ በግልጽ ያሳያችሁዋል። ወዲያውም ታሪኩን መማር ነው ሴቶች  ለኢስፋና ያደረግነውን አስተዋጽኦና የከፈልነውን መሰዋእትነት። ሆኖም የኢትዮጵያ ሴቶች በመሆናችን የሕዝባዊ እንዲይሆን የታገሉት ወንድች ጀግኖች ተለው እውቅና ሲሰጣቸው የኢስፋና የ501 (c)(3)ባለቤት እንዲሆንና ሕዝቡን ኢስፋና የኔነው የሚለውን ባለቤትነት ያጎናጸፍነውን ፡ የታገልነው ግን አሁንም እንደወንጀለኛ እንቆጠራለን የግል አድርገው ለመኖር አላማቸው በሆኑት። ስለዚህ ኢስፋናንምን ያህል እንዲኖር እንጂ እንዲፈርስ የማንፍልግም መሆናችንን በዚሁ እንድትረዱልን እናሳስባለን። የወይዘሮ ብርቱካንን መጋበዝ በኢስፋና ድርጅቱን የሚያፈርስና በሕግ የሚያስጠይቅ ቢሆን እኛም ስለሕግ የተሰለፍን በመሆናችን ጣታችንን አንስተን ይችን ደብዳቤ ባልጻፍን ነበር። የወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን መጋበዝ በእንግድነት ኢስፋናን ሕገ ወጥ እንደማያደርገው ማስረጃና ማሳመኛ ከዚህ በታች እንዳለው በተጨባጭ ልንገልጽ እንወዳለን። በሁለት ሺ ሰባት ዳላስ ላይ ባደረጋችሁት በአል በጣም የምንወዳቸው እንደ ወንድማችን፡ አብረናቸው በከተማው የሰውልጅ መብትን በማስከበር በምናደርገው ትግል የምናውቃቸው ሴኔተር ሮይስ ዌስት ከወይዝሮ ብርቱካን ጋር ሲነጻጸሩ በፓለቲኩ መድረክ ከመጣን ምንም አይገናኙም ሰውየው ያደጉበት ነው በዚህ የማያውቃቸው የለም። ከጥብቅናው ይልቅ በፓለቲካው አለም ይታወቃለ። እህታችን ወየሮ ብሩቱካን ወደፓለቲክ የገቡት በ2005 ነው፡ ከዛ በፊት ዳኛ ነበሩ ቀሎም በተነገርን የፓለቲካ ፓርቲ ጠበቃ ሆነው ነበር። ከሴኔተር ሮይስ ጋር የሚያመሳስል ነገር አላቸው በሞያቸው ይሄውም፡ ሴኔተር ሮይስም ጠበቃም ናቸው። ሮይስ ከተጋበዙ ብሩትካን የማይጋበዙበት መክኒያት የለምለማለትና ያሳሰባችሁ ሕገ ወጥ የማያደርጋችሁ ላይ ያተኮረ ነው ለማለት ነው። ሴነተር ሮይስ በኢስፋና በአል ላይ ንግግር እንዲያደረጉ መጋበዝና መናገራቸውና የጋርለንድ ሜርም እንደዚሁ ንግግር አድርገዋል። ከናካቴው በኢትዮጵያ ቀን ለጸሎት ሰአት ለእኛ ለሴቶቹ ድርጅት የተሰጠንን ፕሮግራም ለፓለቲካ መሪዎች ተሰጥትዋል በጊዜው። የሚናገሩት ፓለቲክ ነክ ሳይሆን ሕዝባዊ በመሆኑ ሕገ ወጥ አልነበረም።

 ልናስታውሳችሁ የምንፈሌገው ነገር ከዚሁ ጋር የተያያዘ በኢስፋና ቦርዴ ስለተወሰነ ውሳኔ ነው። ካለፈው ሃቅ አዲስ በቦርድ ውስጥ ያላችሁ ሊረዳችሁ ስለሚችል በተጨማሪ በማሰብ የምንወደው ተጨባጭ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። ይሄውም፡ በኢስፋና በራሱ ቦርድ ስለተወሰነ ሃቅ ነው። ኢስፋና በ2007 በዳላስ-ጋርለንድ ላይ በቴክሳስ ባደረገው በአለ ላይ ዝግጅት ይዘን በመቅረብ የቦርደ በአለ ከመድረሱ ሶስት ወር በፊት "እስረኞች በኢትዮጵያ ስለአገራቸው ጉዲይ የታሰሩት በሙሉ ለኢትዮጵያ ሚሉንየም ይለቀቁ ያአቶ መለስ ዜናዊንም ልብ አምላክ ያራራልን" በሚሌና ሰላም በኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል እንዲሰፍን የጸሎት ፕሮግራም ልናደርግ ስለምንፈልግ የአምስት ደቂቃ ጊዜ ይፈቀዴልን ብለን በ"የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላምና ለዴሞክራሲ" ስም ጠይቀን እንደነበረ ነው። የኢስፋና ቦርድ ስብሰባ አድርጎ በጹሁፍ ያቀረብነውን ሁለም ተመልክቶ አጽድቆት የፈቀልን ሲሆን ጉዳዩ አሁን ከምትነጋገሩበት ወይም ግማሾች ይጋበዙ ስትሉ ግማሾቻችሁ ፓለቲካዊ ነው በሚል። የምትከራከሩበት ከወይዘሮ ብርቱካን ይጋበዙ ከሚሌው ጥያቄ ጋር የተመሳሰለና እንደውም እሳቸውንም ጭምር ለማስፈታት በጸሎት የተደረገና የተፈቀደልን ትልቁ ምስክር ነው ። ይሄውም ሕገ ወጥ ያለ መሆኑን የፓለቲካ ሰዎችን በኢስፋና መጋበዝ ወይም መድረክ ላይ የፓለቲካ መልክት ያልሆነ ንግግር ሕብረተሰብን የሚደግፍ ማቅረብ ። ይሄውም በድጋሚ ለዚህ ማስረጃ፡ "በጸሎት እስረኞች ይፈቱ!" በሚል ካቀረብነው ሴቶች መሃል፡ የመጀመሪያ ሴት በኢትዮጵያ ታሪክ ለአገር መሪነት እወዳደራለሁ በሚሌ የቀረብን፡ የመጀመሪያ አፍሪካዊ ሴት የፓለቲካ ፓርቲ በሰማኒያ ስድስት በነጮች አቆጣጠር ዳላስ ውስጥ የመሰረትን፡ ከአለም የመጀመሪያ ሴት ከአገርዋ ውጪ የስዴት መንግስት ያቁዋቁዋመች በሚል በአለም ታሪክ ውስጥ ለአገራቸው አስተዋጽኦ ያደረጉ ታጋዮች ሴቶች ማህደር ውስጥ የመዘገቡን እንገኛለን። ይሄ ሃቅ ሁሉ እየታወቀ ነው ጸሎት እንድናደርግ የተፈቀለን በኢስፋና መክኒያቱም ጥያቄያችን ፓለቲካል ሳይሆን የሰው ልጅ መብትን አስመልክቶ ስለሆነ። ww.ethiopiannationalgovernmentinexile.org ብትጎበኙ ምን ማለት እንደፈለግን ትረዳላችሁ። ይሄውም፡ ወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋሻው ከዳላስ፡ ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ ከአትላንታና ወይዘሪት ልእልት ሳሙኤል ከዳላስ በጊዜው አስራ አምስት አመት እድሜ  ጭምር የጸሎቱ አቅራቢዎች ሆነን ተፈቅዶልን ነበር። በጊዜው ከዳላስ ዘውገ ቃኘው ኪሮስ ወልደስላሴ የተባለት የኢስፋና ቦርድ ውስጥ ከነበሩት ሁለት ሰዎችን አስተባብረው ጽሎቱን እንዳለ ለማደናቀፍና ከናካቴው እንዲቁዋረጥ ያላረጉት አልነበረም። አሁንም እያደረጉት እንዳሉት  ማለት ነው ብርቱካን እንዳይጋበዙ።  ነገር ግን በአምላክና በቦታው በተሰበሰበው ሕዝብ ብርታት በኛም በሴቶቹ ጥንካሬ ጸሎቱን ሕዝቡን አስተባብረን ከወጣንበት መድረክ ሳንወርድ ባደረግነው፡ ስታድየሙ ጸጥብሎ ጸሎቱን ልንጨርስ ችለናል በጊዜው። የሚገርመውም ለብዙ ሰው እስከዛሬ፡ የተደረገው ጸሎት "ሜራክል" በሚል የተሰየመው፡ አርብ ጁላይ ስድስት በጋርልለንድ በኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ላይ ሲሆን ፡ በሳምንቱ አርብ እስረኛቹን እነ ወይዘሮ ብርቱኩዋንን፡ ወይዘሮ ንግስትና ወይዘሮ መሰበወርቅ እንጂነር ሃይሉና ድክተር ብርሃኑ ነጋን፡ ጭምር ሲፈቱ ያልተገረመ ሰው አልነበረም ከአምላክ ሌላ ማን ይሄንን ሊያደርግ ይችላል በሚል። ሃቅም ነው አምላክን በጠየቅነው መሰረት ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም ከቤተሰባቸው ጋር አውላቸው ብለን በአንድ ድምጽ ከአስር ሺያላነሰ ኢትዮጵያዊ ሁሉም ያለ ጾታ፡ ያለ ሃይማኖት፡ ያለ ጎሳ፡ ያለፓለቲካልዩነት በሕብረት በጸለይነው መሰረት ሁላችንንም ሰምቶናል። ባጭሩ ጋብዝዋቸው ብለን ልናቆም ስንችል በዝርዝር መጻፉን የመረጥንበት መክኒያትና ማለት የፈለግነው እኛ በፓለቲካው፡ ሳይሆን በሰው ልጅ የእኩለነትና የሰው ልጅ መብት ታጋይነት የጠየቅነውን የጸሎት ጊዜ ፓለቲክ ያለመሆኑን በዚሁ መልክ በማስረዳት በጻፍነው ሲሆን ለኛ የሚሰራው ሕግ ለወይዘሮ ብርቱካንም ይሰራል ለማለት ነው። አሁንም ምንም እንክዋን አንዳንድ ችግር የሚፈጥሩባችሁና ጫና እያደረጉ ያሉ ቢኖሩም ከራሳችሁ መሃል በቡድኖች የመጣም ጥያቄ በመሆኑ ፡ አምላክ የኢስፋናን ቦርድ አባላት በሙለ የቡድን ተወካዮችን፡ ተጫዋቾችን ጭምር ሃቁን ውነቱን ሕጉ 501 (c)(3) የሚፈቅደው ላይ ብቻ እንድታተኩሩ እንዲረዳችሁ አምላክን እንለምናለን፡፤ በ2007 እንደዚሁ በቦርድ አባላት መሃል ከወጪ ሆነው ጸሎት እንዳይደረግ ግፊት እየፈጠሩ ሲያስቸግርዋቸው ነበር ፓለቲካ ነው የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ናቸው በሚል  ። እኛንም አስመልክቶ፡ በትክክል በሕጉ በመሄድ ትክክለኛ እርምጃ  እንደወሰዳችሁ የኢትዮጵያ ሴቶች  ለሰላምና ለዴሞክራሲ አሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግት ጸሎቱን እንድናካሄድ እንደ ፈቀዳችሁልን ሁለ አሁን ደግሞ በሁለት ሺ አስረሃንድ እህታችንን ወጣትዋን ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን ከላይ እንዳልነው ቢቻል ከነልጃቸውና እናታቸው ካሌያም እራሳቸውን ብቻ ጋብዛችሁ በአትላንታ ስታዲየም የሚደረገው የኢስፋና በአል ከመቼውም የበለጠ የበራና ያሸበረቀ የደመቀ እንዲሆን እንድታደርጉ በትህትና እየጠየቅን  ደብዳቤያችንን እዚህ ላይ እንደመድማለን።

በመጨረሻም፡ በእኛ በኩል የምንተባበራችሁ ማንኛውም አይነት ጉዳይ ካለ የእስፓርት በአለንና የወይዘሮ ብርቱካንን መምጣት ስመልክቶ ልንተባበራችሁ ሙሉፍቃደኞች መሆናችንን ስናረጋገጥ ከልብ ነው። እግዚአብሄር ይስጥልን እያልን መልሳችሁን በቅርብ በዚሁ ኢሜል አድራሻችን እንድትልኩልን እንጠይቃለን።

ከአክብሮት ጋራ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ስም
የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው
ፕሬዘደንት።

Sunday, April 17, 2011

እ.አ.አ. ከAugust 29, 2007-September 15,2008 ድረስ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን እነ አምታታው አፍርሰው አለ እያሉ በሪዲዮ ሪዞሉሽን! እያሉ ሲያጭበረብሩ የነብረበት ጊዜ ነበር።

አምላክ ምስጋና ይግባህ ለዚች ቀን።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩና የሬዲዮ ስርጪቱን: የቅዱስ ሚካኤልን ደብር እናድን! የሚለው ጥሪ ወንጀል አልነበረም የተዘጋውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ብዙ መስዋት የተከፈለበትን የስዴተኛውን ማሕበር ከተቀበረበት መልሶ ለማስከፈትና የሕዝቡ ማሕበርነቱን ለማስከበር እንጂ። መስከረም 23 ቀን 2007 የካንጋሩ ፍርድ ቤት እኔን የመረዳጃ ማሕበሩና የሬዲዮ ዝግጅቱን ልታፈርስ ነው ያሉት ሃቁን ያኔም እንዳቀረብኩት በጹሁፍ ከእነ ማስረጃው ማሰራጨቴ ስሜንና ስልክ ቁጥሬን ጨምሮ የማይዘነጋ ነው። አሁን ደግሞ በብሎግ እነሆ። ይሄንን ውነት ነው በወንጀል የተባበሩት ግለሰቦች ለመረዳጃ ማሕበሩና ለሕብረተስቡ የቆሙ በማስመስል ሆነ ብለው ሶስት ውጥን ይዘው ነገር ግን ባንድ መልክና ስም እድር በሚል ሽፋን ማሕበሩን በስማቸው እንደ አዲስ ድርጅት  በማስመዝገብ ያፈረሱትን የጋራ መረዳጃ ማሕበር  በመውሰድ ሕብረተሰቡን አያገባችሁም ለማለት ነበር ባለቤትነቱን ወስደው። ይሄውም ባለቤት የሌለው በማስመሰልና ሕጉ የሚጠይቀውን perodic report ደብዳቤ ቢሰጣቸውም አልደረሰንም አላየንም በሚልለቅዱስ ሚካኤል ደብር የሕብረተሰቡ ባለውልታ በሆኑት ደግና ጨዋ ሰው በዶክተር ግርማ በቀለም ለማሳበብ ሞክረው ነበር። በበትሩ ገብርእግዝዚአብሄር እየተመራ በሃሰት በሬዲዮ ቱልቱላ እይታጀቡ እርስ በእርስቸው የሚደልቁትን በማጭበርበር መኖር ሞያ ብለው የሚሰሩትን የሚያስተውልና ሕጉን አውቆ የሚጠይቀን የለም በሚል የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር መልሶ እንዳይንሰራራ ያደረጉትን ስለደረስኩበት አላማቸውን  እግቡ ሳያደርሱ ቀድሜ ለሕዝቡ በማቅረቤ በሕብረት ማሕበሩን ለማዳን በመነሳቴ ነው ያንን ሁሉ ሁካታ ውሻ እንክዋን የማያስደነግጥ ወይም ዶሮ ብሎም ድመት በሬዲዮን ቀንና ማታ ሳይቀር ዘራፍ! ዘራፍ! ቡራ ከረዮ! ሃቀኞች ተነካን ድረሱልን ቴረሪስት ተብለን ተከሰን የፍርድ ቤት ጥሪ ወረቀት ደረሰን ኡ ኡ! ሬዲዮንም አዘጋችብን!! በኑሮዋችን መጣችብን ልጆቻችንን እንዳናሳድግ አደረገችን! ከመረዳጃ ማሕበር አግልለናታል ሕዝቡን አገልግሎት እንዳትስጥ እንዳትረዳ ፈርደናል! በተገኘችበት ትገደልልን!! በተገኘችበት እርምጃ ይወሰድባት!!! በሚል የለፈፉትና ያስለፈፉት በሃሰት ባቀነባበሩት ክስና የሬዲዮ ዝግጅት ተዘጋብን፡ በውሸት  በተቀነባበረ ሴራ ይሄውም ከዚህ ቀጥሎ የምታዩት ሃቅን ስለያዝኩ periodic report office of the Secretary of State ሞልተው እንዲልኩ በታገልክዋቸው ሳይወዱ እንዲልኩ ሆንዋል።

office of the Secretary of State  ስድስት ወር ጠብቆ መልስ ሲያጣ ኦገስት ሃያዘጠኝ (August 29, 2007) መረዳጃ ማሕበሩ ሕጋዊነቱን ማጣቱንና መፍረሱን ይፋ ያደረገበት ምስክር። በሕጉ በዚህን ጊዜ ማንም ሰው የመሃበሩን ስም እንዳለ እንዳዲስ በማስገንዘብ የመውሰድ መብት ስላለው በስሙ ፡ ማንም ያገባኛል ቢል ወይም ሕብረተሰባችን መብት አይኖረውም ነበር። ሆኖም ያሁሉ ውርጂብኝ ቢደርስብኝም የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብሩን ይመኑ ነጋና እኔ ከጥንሡ ጀምረን ያሳደግነውን የስዴተኛውን ድርጅት በአንድ አምላክ ፍቃድና እምነቴ ከቀማኞች ላድነው ችያለሁ።
































አስተውሉ ዲሴምበር  ሃያ ሶስት ማለትም 12-23-2007 ነው ካንጋሩ ፍርድ ቤት ተሰብስበው ሃሰት ነው መረዳጃ ማሕበሩ ምንም አልሆነም ብለው ከላይ ያስቀመጥክዋቸውን ሪዞሉሽን ብለው በሕዝቡ ስም  በሬዲዮን በትብብር ቦርድ ውስጥ በድብቅ ሳይምመረጡ የገቡት በሙሉ በሬዲዮ ሕገወጥነታቸውን ሲክዱ በገሃድ የመረዳጃ ማህበሩን ነብስ ሲጥ ካደረጉ በሁዋላ ነብስ ነው የዘራንበት ያልዋችሁ። Sep.15, 2008 periodic report የሞሉበት ነው። ስለዚህ
በእኔ ላይ በጊዚው ያደሙትና በአንድ ቀን አባልነት በመፈረም በወር አምስት ዶላር ለመክፈልና በእኔ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተስማምተናል ብለው ነገር ግን ስማቸው ይሰጣልብለው ያልገመቱት እነ ይልማ ዘርይሁን በሌለ መረዳጃ ማሕበር አባልነት የገቡ በመሆኑ የወንጀል ተባባሪነታቸውንና የመረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶ በእነሱ ጥቅም እንዲተካ መነሳታቸውን አረጋግጠዋል። ዛሬ ጅምራቸውን ለመፈጸም ሰው መስለውና ለመረዳጃ ማሕበሩ ያሰቡ በመምስል ለቦርድ ለእጩነት እራሳቸውን አቅርበዋል።



እድር ሲመዘግቡና ሲያስተዋውቁ ልክ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ በሕይወት እንዳለ በማስመስል ስሙን የፓስታሳጥኑን ቁጥር ጨምረው በዚህ መልኩ ያስቀመጡት ብዙ ማጭበርበር አለበት። የእድሩንመተዳደሪያ አስራ ሁለተኛ ገጽ ብታነቡት ቅድመ ዝግጁ በመምሰል መረዳጃውን ያላፈረሱ ለማስመስል የተጫወቱትን "Article-12 Disbanding"  ብትመለከቱ ቁልጭ ብሎ ይታያል መረዳጃ ማሕበሩ ፈርሶዋል ለማለት መወሰናቸውን።


Monday, April 4, 2011

የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው።

የዳላስ ንዋሪ ኢትዮጵያዊ በኤፕሪል ዘጠኝ የትግሬ ነጻ አውጪን በቦታው ተገኝቶ እንዳይቃወም ልክ በእውነት ለሕዝብ የቆሙ መስለው ትግሉን ለማኮላሸት የሚከንፉት ሌላ ሃይል መስልዋችሁ ቤታችሁ እንዳትቀመጡ። ያው የተለመዱት ሕዝቡ አንቅሮ የተፋቸው ተባብረን በቦታው በመገኝት መልእክታችንን እግቡ እንዳናደርስ ሚርውርዋጡት ከንቱዎች ናቸው። በሕብረት በቦታው በመገኘት የትግሬ ነጻ አውጭና መለስ ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ይውረዱ! ማለት ይጠበቅብናል። ለሚመጡትም ትምህርት መስጠት ይኖርብናል ይሄውም ከትግሬ ነጻ አውጪ የክልልና የጎሳ ዘቤ ተላቀው ስለ አንድ ኢትዮጵያና የሕዝብ እኩልነት መብት ካምፕ እንዲገቡ እዛው በአገር ውስጥ። ከታች የምታገኙት በራሪ ውረቀት በታኞቹ ባለ ጎስት ድርጅቶቹ ለሕዝቡ የፓለቲካ ፓርቲ ማህተም ያለው ድብዳቤ የሚሸጡት ናቸው። ከዚህ ቀደም እድር አይቁዋቁዋም በሚል ስማቸውንና ማንነታቸውን ደብቀው ወረቀት እንዲሁ በመበተን ብዙ ሰው እንዳጋጩ ታውቃላችሁ። አሁንም ወረቀት የበተኑት ኢትዮጵያ በሚል እነሱው መሆናቸውን ተረድተን እነሱን ወደ ታች ጥለን ለአግርችንና ለሕዝቡ መቆም ይገባናል። ስለዚህ ከሕዝብ የተውጣጣ ስብስብ ፈጥረን በቦታው እንገናኝ እያልን እነዚህ መሰሪዎች የሚሰሩትን ከዚህ በታች እንደተመለከቱ እንጋብዛችሁዋለን።

Racial segregation is the separation of humans into racial groups in daily life. It may apply to activities such as eating in a restaurant, drinking from a water fountain, using a bath ወዘተ በሚል የክልልን ምንነትና ፋሽስትነት ተግባር ግልጽ ያደርግልናል የእንግሊዘኛው አባባል። ታዲያ Racial segregation  the separation of humans into racial groups in daily life የሚለው ሊቢያን እያሰጋት ያለውና የትግሬም ነጻ አውጪ መሪ መለስ አረብ ነው ትውልዴ ብሎ  አረብነት ትውልዱን ሃረጉን ቆጥሮ ከጋዳፊ ጋር ሲዛመድ ከገንዘብ ጋር የተረከበው ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን በጎሳ ስም ብሎም ሕዝቡ በአንድ ሰንደቅ አላማው እንክውዋን እንዳይተሳሰር በክልል ባንዲራ ህግ ማለትም segregation flag laws ስራላይ በተግባር መለስና ድርጅቱ የትግራይ ነጻ አውጪ እውን እንዲያደርጉት ነበር። ይሄውም በስራ ላይ በአገራችን ሕዝብ ላይ ተጭኖበት ይገኛል። ይሄንን  በቁም  የቀበረንን የክልል መቃብር ድንጋይ ከላይችንና ከወገናችን ላይ እንዳናነሳ እንቅፋት የሆኑብን  የኢትዮጵያን ሕዝብ የቁም ስቅሉን ሸቀጥ አድርገው እንደ ጤፍ ፡ በርበሬ፡ ቡና በመቸርቸር የኑሮዋቸው ገቢና መዶጎሚያ አድርገው የሚኖሩት ከርሳሞች  በስም ሶስት ሲሆኑ በተግባር ግን አንድ የህኑት ናቸው። ጸረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና አንድነት ፍቅር ብልጽግና ነቀርሳ በመሆን በዳላስ ቴክሳስ  ያስቸገሩን መሰሎቻቸውና ተቀጥያዎቻቸው በዋሽንግተን ፡ በሚኒሶታ፡ በአትላንታና በስያትል ባጠቃላይ ከኢትዮጵያ ውጪ በየቦታው ስለሚኖሩ አርቆና ተረጋግቶ ላተኮረው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ድብቅ አይደለም ከፋፋይ ተግባራቸው። የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው። እንዚህም፡ የትግሬ ነጻ አውጪ፡ ደጋፊዎቹ ብሎም ተቃዋሚ ነን በሚል ሽፋን ለመለስም የሚሰሩ በደሞዝ ሲገኙበት ፡ከእነዚህ ጋር አብረው የሚያጫፍሩ ምን እንደሚፈልጉ የማያውቁ ከርስ መሙያ ወደ ነፈሰበት የሚወድቁና ጠላታቸውን ለይተው የማያውቁ ወረቀት ለመበተን መጠቀሚያ የተደረጉና ስምም ለማጉደፍ በስልክ ጭምር መጠቀሚያ የተደረጉ የዋህዎች ወንዶችና ሴቶችም ይገኙባቸዋል። ግማሾቹም ኢትዮጵያ ጉዳያቸውን እናስፈጽምላችሁዋለን ስለሚልዋቸው ደጅ ጠኝዎች መሆናቸው ነው።

ነጻነት ባለበት አሜሪካ ስም ደብቀው ማንነታቸውን ሳያስቀምጡ ከዚህ በታች የበተኑትን ወረቀትና መለክት ተመልከቱ። መልክቱ የእነሱንም ተግባር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ስለሆነ እነዚህ ትግሉን በዳላስ ከተማና በየቦታው ያኮላሹና እያኮላሹ ያሉ በመሆናቸው በሃቀኞች ለኢትዮጵያ አንድነት በታጋይነት ብዙ መስዋእትነትን በከፈልን ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው በተለይ ዳልስ ላይ ሊጋለጥ ችልዋል። እንደሚታወቀው የትግሬ ነጻ አውጬ መንግስትና ባለስልጣኖች በዳላስ ዝር አይሉም ነበር። ለከርሳቸውም በመለስ የተገዙት እንደ አይጥ የተደበቁ ነበሩ ሆኖም እነ ዚህ ዛሬ "የኢትይጵያን ህዝብ እውነትኛ የዲሞክራሲና የነጻነት ትግል እናግዝ" በሚል መለክት አስተላላፊዎች የመለስን ባለስልጣናት ድግስ ከደጋሾች ጋር አንድ በመሆን የሚሰሩና መለስንና ድርጅቱን ከሕዝባችን ትከሻ ላይ ለማውረድ የምንታገለውን ሲታገሉን የነበሩ አህንም ያልተኙልን ጸረ ኢትዮጵያና ሕዝብዋ ናቸው። ለትግሬ ነጻ አውጪ መንግስት ዳላስ መመላለስ የልብ ልብ ማግኘት እነዚሁ ዛሬ ከዚህ በታች የለጠፍነውን መልእክት የበተኑ ጥቂት ሁዋላ ቀሮችና  ከርሳሞች ለትግል አኮላሽነት የተቀጠሩ ናቸው። በዳላስ ለማትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመግለጽ ነው እንጂ እዚህማ እነዚህን ከንቱዎችና ማንነታቸውን የማያውቅ የለም። ለምሳሌ በዳላስ ማንኛውም ጥሩ ኢትዮጵያዊ ተነስቶሕዝቡንና ወጣቱን ሲያስተባብር ሲያዩ ዛሬ የመለስን ባለስልጣን ሊያመጡ ነው ብለው ወረቀት ከሚበትኑባቸው ጋር ባንድነት ይሆኑና ቡድን ፈጥረው  ስለሕብረታችን እያሰባሰቡ ያሉት መሃል ደጋፊ መስለው ይገቡና በደንብ ካጠኑ በሁዋላ አላማቸውን፡ ይሄንንማ አስመልክቶ ቀደም ሲል የጀመርነው ኮሚቲ ስላለ ለምን እኛ ኮሚቲ ውስጥ ገብታችሁ አብረን አንሰራም አንድ አይነት ሃሳብ ስለሆነ በሚል ኮሚቲውን ይውጡና በቁጥር ስራው የአንድነት ጥቅሙም ሰላሙም እንዳይሰራራ በማድረግ አኮላሽተው ግለስቦቹንም አስከፍተው አበሳጭተው አንድነትን ሰንሰለቱ እንዳይጠብቅ በዳላስ ትልቅ ሚና ለመለስ ሲጫወቱ የኖሩ ናቸው። ጥሩ ምስክር ሻለቃ ተፈራ ወርቅ የተባለውን ከተማውን ገና እንደረገጠ ካዲስ አበባ መጥቶ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብን አንድነት መበታተኛ ብይ አድርገው ለጥፋት ፊት አውራሪ አድርገው በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ውስጥ እንዲገባና ህዝብ ሳይመርጠው ስብሰባ ሳይደረግ ፕሬዘደንት እንዲሆን ያደረጉት የወያኔ ተቀጣሪ መሆኑን እያወቁ ነበር የተጫወቱት የትግል ማኮላሸትና ለወያኔ በር ማመቻቸት ሚና። የኢትዮጵያ አምላክ ትልቅ ነውና ተፈራ ወርቅና ሌሎቹ ወያኔን ታጋይ ነን በሃሰት ነው የወያኔ ቅጥረኞችና ደጋፊዎች የተባልነው ብለው የመሸታ ቤት ፍርድ ቤት ከፍተው እራሳቸውን ንጹህ አድርገው እንዳልቀረብ የዲያስፖራ ስብሰባ ብሎ መለስ በእያመቱ በሚያዘጋጀው የቅጥረኞቹ ድግስ በአል ላይ በድብቅ ገብተው በቪዲዮ ከተያዙት ከአሜሪካን አንዱ ተፈራ ወርቅ ነበር የሄደውም ከሌሎች ምስያዎቹ ጋር ለሁለት ሳምንት በተከፈለለት ትኬት መሆኑነው።

ሌላው ፡ የጸብም ይሁን የሰላም ድግስ ጥሪ ወረቀት ባለቤት አለው። ነጻነት ባለበት በአሜሪካ ለምንድነው ስም ሳይስቀምጡ ከዚህ በታች ያለውን መልእክት የሚያስተላልፉት? ኢንቪስት ያደረጉትና የሰሩት ቤታቸው እንዳይወረስ ይሁን ወይስ ሕዝቡ አሁንም ያላወቃቸው መስልዋቸው ይሆን? ስማቸውን ደብቀው በሌላ በኩል ስለ አረብ ወንዶች ጀግንነት ያወራሉ ምነው እነሱን ማን ከለከላቸው አረቡን ጭምር ካንበረከኩ ጅግኖች የአግሪቱን አንድነትና ነጻነት በሕይወታቸው ጠብቀው ካስረከቡን ጀግኖች አገር አይደል የተፈጠሩት? ማንነታቸውን ጽፈው የትግሬ ነጻ አውጪንና መለስን እሱን ወክለው የሚመጡትን ኤፕሪል ዘጠኝ እንቃወማለን በሚል በግልጽ መቆም ያልቻሉ አልጫዎች ከርሳሞች ነጋዴዎች ለዴሞክራሲ ቆመናል በሚል በመጻፍ በተለመደው ሕዝብ ሊያታልሉ አይችሉም። ቃሉን እውነተኛ ዲሞክራሲ ብለው የጻፉትን እንክዋን ትርጉሙንና ተግባሩን ገና ያልተረዱ ናቸው። ለዴሞክራሲና ነጻነት የሚታገል፡ ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገር ውስጥ አሜሪካን እየኖረ ስሙንና ድርጅቱን እየደበቀ እራሱን ነጻነት ነስቶ ጥሪ አይበትንም።  የአረብ ወንዶች ስለከፈሉትና እይየክፈሉ ስላሉት መስውእትነት ከማዳነቅ ከዶላር ተገዢነትና ካቅም በላይ በመኖር ከሚያስጨንቅ ወራዊ የቤት እዳክፍያ ተላቆ በአቅም እየኖሩ አገርን በገንዘብ ከለዋጭነት ተግባር መላቀቅና ሰርቶ በሃቅ በመኖር ለኢትዮጵያ ለጋራ ቤታችን ነጻነት መሰለፍ ይገባል።  ምን አለበት ስቸውንና የጎስት ድርጅታቸውን ስም በሙሉ ባይጠሩም ከውረቀት በታኞቻቸው መሃል እነ ደጀኔ ነን ቢሉ? ወይም እነ አበበ? እነዚህ ስም የሌለው ድግስ ጠሪዎች እንደሚታወሰው ገና በኦክቶበር ጀምረን የትግሬ ነጻ አውጪ ባለስልጣን ዳላስ ሊመጡ ስለሆነ ምን ማድረግ እንዳለብን ስናቀርብ ሃሰት ነው ብለው ሲያስተባብሉ እንደነበር የማይዘነጋ ነው። ዳላስ ኢኦቲሲ ብሎግም የእነዚህን ትግል አኮላሽ ቡድን ማንነት በየጊዜው የሚያወጣ ስለ ኤፕሪል ስብሰባ ሲያወጣና ከጀርባውም እነዚሁ ትግል አኮላሾቹም እንዳሉበት በገልጽ በማስቀመጡ ደስተኛ አልነበሩም። ለምን ቢባል የትግል ማኮላሸቱን ኮንትራት ስለአዛባባቸው። እነዚህ ግለሰቦች ቅንጅትን አሳርደው ደሙን ከአራጁ ጋር የጠጡና አሁንም ያንኑ ተግባራቸውን በውስኪና በሄንከን ቢራ በመታጀብ ስለ ኢትዮጵያ ግዳይ ታጋይ ነን በሚል የመሸታ ቤት ዲስኩር አድራጊዎችም ናቸው።  እነዚህ ግለሰቦች በሁሉም አቅጣጫ አንድነታችንን በማደፍረስ ተልኮዋቸው በአበመጨረሻም ጸሃፊዎቹ ተቃዋሚ ነን በሚል ስም የሚያጭበረቡትና የትግሬ ነጻ አውጪ የድብቅ ደጋፊዎች፡   የትግሬ ነጻ አውጭም የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው።

ከዚህ በታች ያለው ከላይ በሶስተኛ ያስቀመጥናቸው የበተኑት ሲሆን የእነሱንም ማንነትና ተግባር ከትግሬ ነጻ አውጪና ከግብረአበሮቹ ደጋፊዎቹ ድርጊት ጋር አንድ በመሆኑ ከድግስ አስተናጋጆቹ ተለየተው የማይታዩ ነገር ግን በስም እንጂ በድርጊት እነሱም ጸረ አንድ ኢትዮጵያ ናቸው። በትክክል ማንነታቸውን የሚገልጽ በመጻፋቸው ብዙ ስለ እነሱና የትግሬ ነጻ አውጪን እያነጻጸርን ከመጻፍ ጊዜአችንን ቆጥበውልናል። ስታነቡት ሶስቱም አንድ መሆናቸውን እንዳትረሱ እናሳስባለን። እነዚህ ግለሰቦች የሕብረተሰባችን አንድነት የጀርባው አጥንት ነቀርሳዎች መረዳጃ ማሕበራችን አስመልክቶ ትልቅ ብጥብጥ እየፈጠሩና መረዳጃ ማሕበሩን ለግል ጥቅማቸው ይዘው መከራ እያበሉ ሕዝቡን ያሉ ናቸው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጽሙ የማያስቡ አስመሳይ ነጋዲዎች እንጂ። የመረዳጃ ማሕበሩን ነጻ ለማውጣት አብረናችሁ ነን ብለው ከእውነተኛና ለግል ጥቅም አገራቸውን የማይለውጡ ኢትዮጵያውያን መሃል ገብተው እነማን አብረው እየተባበሩ መሆናቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ፡ ሕዝቡ አንድነትና ሰላሙን እየገነባ መሆንኑ ካረጋገጡ በሁዋላ ሚስጥሩን ውስደው የመረዳጃ ቦርዱን መልቀቅ ላለብቸው ለትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች የዶላር ተገዦዎች ጊዚያቸው ዲሲምበር አልፎ እሻፈረኝ ብለው ለተቀመጡት ወስደው ያስረክባሉ። አብረውም በመቆም ከቦታው እንዳይለቁ  አዲስ የእክል መንገድ ይቀይሳሉ። ይሄውም ድርጊታቸው  በሕዝቡ መሃልና ቦታውን አለቅም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ አቁዋቁሜ ካልመራሁ በሚለው ቦርድ ትልቅ አደገኛም ሊሆን የሚችል ችግረ የፈጠሩ ናቸው። እነዚህ መለስንና ደጋፊዎቹን ሳይህን አንድነቱን እያስተባበረ ያለውን የዳላስ ሕዝብ ነው በተቃዋሚ ነትሽፋን ስም እየታገሉን ያሉት።

በመጨረሻም ከኦክቶበር ጀምረን ስንሰራ የነበር ነው ኤፕሪል ዘጠኝ ተቃውሞዋችንን አስመልክቶ፡ የስልክ ስብሰባችን ነገም ይቀጥላል አዲስ ፒን ቁጥር ስለምንልክላችሁ በኢሜል ማየት አትርሱ ።

አስጀምሮ አስፈጻሚ አምላክ ምስጋና ይግባህ አሜን።