Wednesday, January 19, 2011

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ባስቸክዋይ የቦርድ አባል ምርጫ ስብሰባ እንዲጠራ ሕዝቡ መልእክቱን ያስተላልፋል! ቁጥር አንድ።

የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ ቁጥር አስራ ሶስት።

መግቢያ፡ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን ከጃቸው ላለማጣትና ገንዘቡስ ሁሉ የትደረሰ? ገንዘብ የወሰዳችሁትን አምጡም  እንዳይባሉና በእድርም ስም አስገባን ያሉት ገንዘብንም አስመልክቶ፡ ከኢትዮጵያ ቀን የተገኘውን ገቢም አስመልክቶ ባጠቃላይ በገንዘብ እንዳይጠየቁ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በተለመደው ቦርድ በድብቅ የማቁዋቁዋምና በመረዳጃ ማሕበሩ በሬዲዮ እየወጡ ማውጅ ባላቸው የማናለብን ልምድ ፡ አሁን ደግሞ  እነፍቅረማሪያምና በትሩ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በሚል በድብቅ የምያቁዋቁሙት ቦርድና ኮሚቴ ውስጥ ሁሉ እንደ ጨው ሲያስገብዋቸው የሚተባበርዋቸውን ይዘው ቦርድ ኦፍ ትረስቲ እያቁዋቁዋሙ ስለሆነ መቆም አለበት።

ከቤተክርስትያን በስትጀርባ ሆኖ አማካሪ ምስሎ ቀርቦ ደብሩን ለበትሩና ለግብረአበሮቹ ሊያስረክብ ነው ተው! ሲባሉ ባይሰሙም ነገር ግን ውነት አይቀሬ ነውና በትሮቹን ተፈራ ወርቅን፡ በትሩን፡ ኪዳኔ አለማየሁን የቅዱስ ሚካኤልን ደብርና የከተማውን ሕዝብ አንድነት አፈራራሾች በቦርዱ ካላስገባችሁልኝ በሚል ባቀረበውመሰረት ፍቅረማርያም ማንነቱንና አላማውን ሊረዱ ችለዋል። ፍቅረ? የቤተክርስቲያኑ ቦርድ አባላት ባለመስማማታቸው ምርጫ እንዳይካሄድ ፔቲሽን ያስፍረመው ማንነቱን የደብሩ ቦርድ አባላት ሲገነዘቡና ጥያቄው ያለመውን መልስ አዝሎ ግቡን ስላልመታ  ነው፡፡ እኔ ያልክዋችሁን ስዎች ቦርድ ውስጥ አይገቡም ስላላችሁኝ ምርጫው እንዳይካሄድ አደርግባችሁዋለሁ ብሎ መዛቱምና ማስፈራራቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የአንድ ሕብረተስሰ ተከብሮ መኖር በሚኖርብት እንደ አሜሪካን አገር ለሕብረተሰቡ ክብርና ተሰሚነትም ድምጹ ሊኖረው የሚችለው እራሱን በጋራ አስተባብሮና ተከባብሮ በግለሰቦች ወይም በቡድን ሳይሆን በሕብረተሰቡ ለምሳሌ በብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዳላስ ፎርት ወርዝ በችሎታው፡ በታማኝነቱና በፈሪሃ እግዚአብሄር ተግባሩ ፊት ለፊት መርጦ ያስቀመጣቸው ለክብሩና ለጋራ ጥቅሙ መርጦ ያስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ስሙን ወክለው በየቦታው በመገኘት ድምጹ የሚሆኑ እንደራሴ ብሎ ሲያስተዋውቅ ብቻ ነው።

ላሁን ጊዜ ስለሌለ በዛሬውና በነገው ቀን እንዴት የጋራ መረዳጃው በልዋጭ መልክ ለእነ መለስ ዜናዊ ማገልገያ እንደገባ፡

እንዴት የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ስድስት ወንዶች ከሕዝብ የተረከቡትን ሳያስርክቡ ሜዳላይ ጥልውት ሊሄዱ እንደቻሉና

 የኢትዮጵያ ቀን እንጀምር በአል እናዘጋጅ ሲባል ምን ይዘው መጡ የቦርድ አባላቱ? ለምንስ  የኢትዮጵያ ካርታ ቦርዱ ከለከለ?

እንዴት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ በዳላስ ፎርት ወርዝ በተለይ በመዘጋጃ ቤቱ የተተከለውን የሕብረተሰቡን ታላቅቅነት አፍርሰው እራሳቸውን ግለሰቦች ሊክቡበትቻሉ?

ለሰላሳ ደቂቃ በሰለጠነው ስርአት በደብዳቤ ብጽፍም መላልሼ፡ አንድ አመት ስላለፈው ደጅ ጥናት ለምን?

የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ከጃቸው ፈልቅቆ መለአኩ እራሱ ቤቱን ነጻ ስላወጣ የዚህ ሁሉ ችግር ሸማኔና ደዋሪ የመበጣበጥ ጥበብ አቀነባባሪ ግብረአበሮቹን ከእነ ሴት ልጆቻችው፡ጭምር ይዞ ከዚህ ቀደም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ይመረጥ ብለን ስንጠይቅ አሻፈረኝ ይገለሉልኝ በሚል ያስቆምትን አሁን ግን የወሰዱት ገንዘብ ከካቶሊክ ቻሪትም ጭምር ከኢንሹራንስም ከዌልፋርጎም ባንክ እንዳይጠየቅ ስለእድርም ገንዘብ ቦርድዶፍ ትረስቲ እያቁዋቁዋሙ ስለሆነ፡

የመርዳጃ ማሕበሩ አዳራሽ ፕሮጄክት ባለቤትና ማን ፈጠረው? ኮሚቴውስ ወዴት ደርሶ በላዩ ላይ አዲስ ተፈጠረ? ገንዘቡስ የት አደረሱት? እንደቀድሞው ሕብረተሰባችን ስላምን የመተሳሰብ ፍቅሩንና አንድነቱን መልሶ ለማጎናጽፍ ምንድነው መፍትሄው? በሚል የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብሩን አስመልክቶ ስለሚተነተን ከእነማስረጃው፡ ከላይ ባለው አረስት ቁጥር ሁለት በሚል ይቀርባል ተከታተሉት።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ምርጫ ባስቸክዋይ እንዲደረግ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል። መረዳጃ ማሕበሩ ለሕዝቡ መመልስና በሕዝብ በሚመረጡ ለሕዝብ አገልጋዮች ማስረከብ አለብን! አምላክ አንድነታችንን እየመለሰልን ነው እንበርታ እናመስግነው። እራሳችንን ካከበርን ካስከበርን የዳላስ ተመራጮች ሁሉ በመዘጋጃ ቤቱም ያጣነውን ክብር ባጭር ጊዜ እናስመልሳለን አሁንም ተጀምርዋልና!

እንክዋን ለጥምቀት በአል የአለም ፈጣሪ አደረሰን ሁላችንንም!

እንክዋን ለጥምቀቱ በአል አለመንና በውስጥዋ ያለንውን ሁሉ የፈጠረና ሰማይና ምድርን የዘረጋና የፈጠረ አምልክ አደረሰን ሁላችንንም! ሰላም ከጤናና ከደግነት ጋር ለሁላችንም እንዲያበዛልንና የታመሙትን ሁሉ በየቤቱ ያሉትን ስለሚያውቅ እንዲያድንቸውና በአዳኝነቱ፡ በፈዋሽነቱ ሃይል ያለው በእጁ ስለሆነ ልጁንም አዋቂውንም እንዲፈውስ እማጸነዋለሁ። በሃዘንም በተለይ ሳይኖሩ ከፊታቸው የትቀጠፉባቸውን ልጆቻቸውን ላጡት ቤተሰቦች አምላክ ምንም ስለማይሳነው ጽናቱን ባስቸክዋይ እንዲለግሳቸው እለምነዋለሁ። ቤተሰቦቻቸውንም ላጡት አምላክ ብርታቱን እንዲሰጣቸው እለምናለሁ።

እግዚአብሄር ብዙ ጥምቀት ያሳየን ደግ ስራ እንድንሰራና ለግላችን ብቻ ሳይህን ለሚቸገረው ሁሉ ምንም ይሁን ምንም ችግሩ የመከራው ቀራፊ እንድንሆን። ለራስ መኖር ግዴታ እንደሆነ ሁሉ ወገን ወይም ማንኛውም የሰውል ልጅ ብሎም እንሰሳን ከችግር ማዳንና መከራ ውስጥ ያለውን ቅድሚያ በመስጠት ማገዝ አንዱ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ትእዛዝና የሚያስደስትም ትግባር እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። እሩህሩህ መሆን የሚያሳየው አምላክን በልብ ውስጥ ይዞ መጉዋዝን ነው። ክፉና ጨካኝ ለራስ እንጂ ስለሌላው ወገኑም የማራራ አዋቂነት ሳይሆን፡ አምላክን ያልተከተለ ልብን ይዞ በንፋስ የሚሄድ ብቻ ነው። ደግ እንሁን፡ ጥሩ እንስራ፡ አንቀናቀን፡ አንንገብገብ፡ በውለታ ውለታ ወለታን አንጠብቅ። ለምንሰራ ደግ ስራ ሁሉ በአምላክ ፊት ቢታፈስና ቢዛቅ የማያልቅ የተባረከ ሃብት እናጠራቅማለን። ፈጣሪያችን ይከፍለናል ለኛ በመድረስ። ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው ልጅ ምንም አንጠብቅ ማሰብ እንክዋን ሃጢያት ነው። ቸር እንሁን አምላክ ይጨምርልናል። በመጨረሻም፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሃሰት አማኞችን አንካብ ፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸብ አንጠንስስ አንደግስ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚያጋጥመን በግልጽ እንነጋገር ይሄም ቦርድ ውስጥ አገልጋዩንም ጭምር ማለት ነው። የቦርድ አባላት
ምእመናንን ጠርተው በግልጽ ማናገር እንጂ በጎዋሮ ማውራት ማቆም ይኖርባቸዋል ችግር እንዲታረም ስለሚረዳ። ምእመናንም በግልጽና በጹሁፍ ስማችንን ከእነስልክ ቁጥራችን ጭምር ጽፈን እርማት መደረግ ስላለበትና ስለሚያሳስብን ጉዳይ በግልጽ መነጋገር ይገባናል። ስለ ቤተክርስቲያን ፈራጅ አምላክ ስለሆነ ፍርድ ቤት መካሰስ መቆም አለበት። ክስም ላይ ያለውን ጉዳይ በቅርብ ተነጋግሮ ከፍርድ ቤት ውጪ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተነጋግሮ በግለሰቦች የተጀመረውን የእርስ በእርስ ግጭት ከቤተክርስቲያኑ ደህንነት ጋርም የተያያዘ ባለመሆኑ በመነጋገር ማቆም ነው ውጊያውን። ቤተክርስትያኑ ማለትም ደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አደጋ ላይ ቢሆንኖሮ ወይም እንደተባለው ጴንጤ ወይም ባፕቲስት ሊያደርጉት ነው የተባለውና ብሮሹር እንደተላለፈው ውነት ቢሆን ኖሮ ምእመናኑ የደብር አባላት ቦርድ ውስጥ ያሉትን በሙሉ መንጥረን ባስወጣን ነበር። ዲሲ ላሉት ፓትሪያርክ ሊያስረክብ ነው ተባለ ያውም ገደብ ተሰጥቶት "በሚቀጥለው ሳምንት የሚካኤልን ደብር ቦርድ ዲሲ ላለው ሲኖዶስ ሊያስረክቡት ነው!" ሳምንቱ አለፈ ወራትም። ምነው ወንድሜ የታል ያስረከቡት ሃሰት ነው አላልክህም? ብዬ አበቃ። አንድ ሰው አንድ ጥፋት ካለው ብዙ የውሸት ጥፋት በሚጨመርበት ጊዜ አንድ ጥፋትን ለማክበድና ሕዝብን ለማነሳሳት ተብሎ አንዱን የውነቱን ጥፋት ወይም ወንጀል ከማቃለሉም ይበልጥ፡ ስለ አንዱ ጥፋትም ምን ያህል ውነተኛነት አለው ይሄ ሰው? የሚለው ጥያቄ ውስጥም ይከታል። አይዋሽ! ውሸትን ተባብረን እንግደለው ሴጣን ስለሆነ። ውነተኛ እንሁን እውነት እግዚአብሄር ስለሆነ!

አምላኬ ባንተ ፍቃድ ስለህነ ከዚህ በላይ ያለቺውን መል እክት በሃቅዋ ያስቀመጥኩት ለሚያነብዋት ሁሉ መጠቀሚያ አድርጋት። አስጀምረህ ስላስጨረስከኝ እንደስፍም ይችን መልእክት ፍቃድህ ስለሆነች ተመስገን።

Friday, January 14, 2011

ፍቅረማሪያም ደረስ የተባለው በዳላስ ቴክሳስ ለምን እኔና ግብረአበሮቼ ቦርዱን አልተቆጣጠርንም በሚል በመለአኩ በቁዱስ ሚካኤል ላይ petition drive እያስፈረመበት ነው በሰው ልጅ ላይ ሲያደርግ እነደነበረው!

ቤተ ክርስቲይኑንና መረዳጃ ማሕበሩን በቅጥጥሩ ስር ለማድረግ ሲያለም ይኖረው የሚፈልጋቸውን እራስ ወዳዶች ለገንዘብ ሕሌናቸውን የሸጡ፡ የሚሸጡ ቦታ እያመቻቸ እሱ ብቻውን በግል ማድረግ የማይችለውን ጥፋትና ተንኮል እንዲሰሩለት ሳይመረጢ ተመረጡ፡ ዶክተር ሳይሆኑ ዶክተር ናቸው፡ የአይን ክልኒክ ሳይኖር አይን ያበራሉ፡ የከብት ሃኪም መሆን ለአንድ ኢትዮጵያው አዲስ ባይሆንም ፡ የከበት ሃኪም ሆኖ የማይስራውን በግልጽ እየታየ እየታወቅ በማስረጃ ሃኪም ነው፡ ከአርባ ያላነሰ የጎስት ድርጅት በኢትዮጵያውያን በዳላስ ንዋሪ ስም እየፈጠረ በሕብረት ጥፋት ለማጥፋት አንድነታችንን ለማፍረስ ፡ በመጨረሻም የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ውስጥ በግባት ሲያቅተው ያዘጋጃቸውን የጥፋት ፊት አውራሪዎቹን ይዞ፡ ፓሊስ ተጠርቶ በአቶ እዮኤል ዳቆን አለማየሁን እንዲያስወጣ ወይም ሲያስወጣ የጸቡን ድግስ ደጋሽ ፍቅረማሪያም የሚባለው ነው አቶ መላኩ ታደሰ፡ ልኡል ሰገድ አበሻውና ዶክተር ሰለሞን ደጀን አበበ በትሩና ተፈራ ወርቅ፡ ኪዳኔ አለማየሁ፡ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን የተንኮሉ ድግስ ደብዳቤ አቅራቢና አጃቢናቸው በሚል በጽሁፍ ያቀረብኩላችሁ ለዳላስ ሕዝብ ያቀረብኩላችሁ ሃቁን? አዎ ያቀረብኩላችሁ አስርምስት  ገጽ። እነሆ ፍቅረማርያም ፊታውራሪዎቹም በመሸነፋቸው በራሱ በሚካኤል የተንኮሉም ፈጻሚና አስፈጻሚ በከተማው ባለመኖሩ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ስሙን ጽፎ ደብሩን ለመውረስ በሰው ልጅ ላይ የለመደውን petition drive እግዚአብሄር ባርኮ የመላእኮች አለቃ ባደረገው የቅዱስ ሚካኤል ደብር ላይም እያስፈረመበት ይገኛል። የምትተባበሩት ሰዎች ባለፈውም እንዳደረጋችሁት ልብ ብላችሁ ካያችሁ ተቀስፋችሁዋል አሁንም እንዳትቀሰፉ። ቤተክርስቲያኑ የግለሰቦች ወይም የአንድ የሁለት የሶስት ቡድን መሆኑ ቀርቶ የመላው ምእመናን የእኔ ብሎ አምኖበት እየጸለየበት ስለሆነ ግለሰቦች አርፋችሁ ስራችሁን እየሰራች አምላክን እያመሰገናችሁ ብትኖሩ ለራሳችሁ ሰላም ታገኛላችሁ ከሰው ሳይሆን ከአምላክ። ዋ! ሚካኤል ስንቱን ነው ያሳይን። እራሱ ፍቀረማሪያም ተንኮሉን የሚሰሩለት ሁሉ አንገታቸውን በመድፋታቸውና ማንነታቸው ስለታወቀ ውነተኛ ማንነታቸውም በተንኮል ተግባራቸው ስላስመሰከሩ ፈቅረማሪያም ተሸንፍዋል በሚካኤል ስሙን ጽፎ ያስግባውም ምርጫው ይቁም ቦርዱም ሕጋዊ አይደለም በሚል ለመሆኑ በመረዳጃ ማሕበሩ ያደረገውን  ይቀጥላል።

Wednesday, January 5, 2011

ተፈራ ወርቅ አሰፋ የተባለው ሻለቃ ማንነት ብዙ ጊዜ ፈጅቶባችሁ ነበር አንዳንድ ሰዎች። አሁንስ ከዳላስ ቴክሳስ አዲስ አበባ ይታያችሁዋል?? ትግል አኮላሽን ታጋይ ስትሉ፡ ደም ያፈሰሰውን ታጋይ ስትሉ፡ ታዲያ አሁን አያችሁት ወደ አለቆቹ ፊቱን በግልጽ ያዞረውን?

ያልክዋችሁ ደረሰ በግላጭ አንድም ሳይቀር እግዚአብሄር የውነት አምላክ ምስጋና ይግባው።

የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ ቁጥር አስራሁለት።

 በቅድሚያ የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራልን አስመልክቶ ቦርድ ውስጥ ገብተው የድብቅ አላማቸውን እግቡ ለማድረስ ላለፈው ስምንት አመታት በተለያየ መልኩ በሕብረተሰቡ መሃል ገብተው ሲበጠብጡት ማንነታቸው ስልተደረሰበት ያው በተለመደው በድብቅ አዲስ አበይባ በመግባት ስራቸውን ያጠናክራሉ። ይቀጥላል።

Sunday, January 2, 2011

"New Year Gift"

ከየሐረርወርቅ ጋሻው።

የተከበራችሁ ወገኖቼ መልካም የአሜሪካን አዲስ አመት ይሁንልን ለሁላችንም። ብዙ አዲስ አመት አምላክ ያበርክትልን። በያለንበት በእውነት የታቀፈን ፍቅር ፈጣሪያችን ይስጠን።

ስጦታ ።

ለብዙ ወዳጆቼ እንደያመጣጡ የምሰጠውን ስጦታ ልለግስ እወዳለሁ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአሜሪካን አዲስ አመት። በሚቀጥለው አመት አይደለም ይችን ስጦታ ካነበባችህ ጀምሮ መጀመሪያ ሰላማችሁን የምታገኙት እራሳችሁን ስትጠይቁ ነው።  ይሄውም ባነጋገር ከራሳችንና ከዎዳጆች አብረን ከምንሰራቸው፡ ቤተሰብና ጉዋደኛ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ሳይቀር ሳናስተካክልና ግልጽ ባልሆነ ልምድ የምንናገረው ዘቤ፡ ኢትዮጵያውያንን ብዙ የምላስ ማዳለጥ ግጭት ስለሚያጋጥመን ከእርስ በእርስም አልፎ ከውጪውም አገር ሰው ጋር በአነጋገር ጠማማነትና ሽፍንፍን አባባል ልምድ መክንያት ጥላቻ እንቀርጻለን።  ይሄንን የማይገባ አነጋገርና ሳይገባን እንዲህ ማለቱ ነው እከሌ ወይኔ ምነው ልክልኩ በነገርኩት! ብሎ ከመቆጨት እዛው ፊት ለፊት ለምሳሌ፡ አንድ ወንድሜ ዛሬ ይሄ የፓለቲካ ጥያቄ አይደለም አለኝ።  በጥቅሉ በማስቀመጡ ሊገባኝ አልቻለም ስለዚህ ምንማለት ፈልገህ ነው አልገባኝም አስረዳኝ አልኩት። የመለስልኝ ግልጽና ገንቢ ነበር። እሱም ጨዋ ሰው በመሆኑ ለእኔም ትምህርት አስተማርሽኝ ብሎ ተለያየን። ባጭሩ "ምን ማለት ፈልገሽ ነው?" የሚለው ያብራሩልኝ ጥያቄ ዘላለማዊ ትልቅ ስጦታ በመሆኑ እንደምትደሰቱበት አልጠራጠርም። ይመስላል በሚል አንሄድ።

እግዚአብሄር ምስጋና ይግባህ ለሁሉም ስጦታህ የእኔ ንጉስ። ሰው ያሰበው በምንም መልክ ሊፈጸም አይችልም ያላንተ ፍቃድ ወገኖቻችንን እርዳቸው አሜን።